የተጠናቀረ ክፍለ ጊዜ 1
መግባት
(1 min)
ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።
Or six.zume.training/checkin and use code: 1397
ፀልዩ
(5 min)
በጸሎት ጀምሩ። ያለ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ማስተዋል ማግኘትና መለወጥ አይቻልም። በዚህ ክፍለ ጊዜ ወቅት እንደ ቡድን መንፈስ ቅዱስን ለመጋበዝ ጊዜ ውሰዱ።
ማጠቃለያ
(1 min)
በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-
እና እነዚህን መሳሪያዎች ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን፡-
- እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
- የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
- መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
- የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
- S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
- የተጠያቂነት ቡድኖች
- እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል
- ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር
READ
(5 min)
እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
ወደ ዙሜ ሥልጠና እንኳን በደህና መጣችሁ! ዙሜ(Zume) የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "እርሾ" ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው የእግዚአብሔር መንግሥት ጥቂት "እርሾ" ወስዳ ብዙ ሊጥ ውስጥ የከተተችን ሴት ትመስላለች፡፡ ሴት የዋ እርሾውን በሊጡ ውስጥ ስታኖረውም፣ እርሾው ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካው ድረስ ይስፋፋል፡፡ በዚህም ንግግሩ ኢየሱስ ያስረዳው አንድ ተራ ሰው በጣም ትንሽ ነገር ወስዶ ታላቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነን ነገር ለመፍጠር ሊጠቀምበት እንደሚችል ነው! ሕልማችን ኢየሱስ ያለውን ለማድረግ ነው… በዓለም ሁሉ ያሉ "ተራ" የሚባሉ ሰዎች ታናናሽ መሣሪያዎችን ወስደው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታላቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ መርዳት! ኢየሱስ ለተከታዮቹ በመጨረሻ ጊዜ የሰጣቸው ትዕዛዝ ለመረዳት ቀላል ነበሩ፡፡ እንዲህ ነው ያላቸው፡- "ሥልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" የኢየሱስ ትዕዛዝ ቀላል ነው፤ "ደቀ መዛሙርት አድርጉ" የሚል ነው፡፡ ትዕዛዙን እንዴት እንደሚፈጽሙም የነገራቸው ነገር ቀላል ነው፤ በምትሄዱበት ሁሉ ደቀ መዛሙርትን አድርጉ፡- በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዘውን ሁሉ እንዲያከብሩ እነርሱን በማስተማር ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤ ሆኖም አንድን ሰው ደቀ መዝሙር ማድረግ ምን ምን ደረጃዎች አሉት? 1 - ደቀ መዛሙርት ማድረግ ያለብን ሁልጊዜ ነው፤ የትም ብንሄድ፤ 2 - አንድ ሰው ኢየሱስን ለመከተል ሲወስን - መጠመቅ አለበት፡፡ 3 - አንድ ሰው ኢየሱስን በመከተል እያደገ ሲሄድ፣ ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ እንዴት መታዘዝ እንዳለበት ማስተማር ይገባል፡፡ ኢየሱስ ካዘዛቸው ነገሮች አንዱ ደቀ መዝሙር ማድረግ እንደመሆኑ፣ ኢየሱስን የሚከተል ሁሉ ሰዎችን እንዴት ደቀ መዝሙር ማድረግ እንዳለበት መማር አለበት፡፡ ደቀ መዛሙርት ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ እነዚያ ደቀ መዛሙርት የሆኑትም ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ ደቀ መዛሙርትን ማብዛት አለባቸው፡፡ ዙሜ የሚሠራውም እንደዚህ ነው፡፡ ልክ እንደ እርሾ ነው፤ ሊጡ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሊጡ ውስጥ ይሠራል፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ደቀ መዛሙርትን እንዲፈሩ ሲያዛቸው፣ አንድ የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል፤ "እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሏቸዋል፡፡ የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ እርሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር የመሆኑን ነገር ሊያስበው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ እንዳለው ከእኛ ጋር ስለሆነ! ይህም ማለት የእርሱ ተከታይ የሆንን እኛ እያንዳንዳችን ደቀ መዛሙርትን እንድናፈራ ለሚፈልገው ለኢየሱስ ራሳችንን ማስገዛት አለብን ማለት ነው፡፡ እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "… ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ... ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" እኛን የላከን ኢየሱስ የተደገፈበት ሥልጣን … የራሱ ሥልጣን ነው፡፡ እርሱ እንዳለውም ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን የለም፡፡ ከእርሱም የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ትውፊት የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ባህልም የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ሕግም በምድር ላይ አልታየም፡፡ ኢየሱስ ያለው ይህንን ነው፡- "ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡" ሥራው ሁሉ ተሠርቶ እስኪያልቅ ድረስ፣ ልክ እንደ ዙሜ - ልክ እንደ እርሾ - መሄዳችንን እና ማደጋችንን እንቀጥላለን፡፡
ተወያዩ
(10 min)
- ኢየሱስ ሁሉም ተከታዮቹ ለታላቁ ተልዕኮ እንዲታዘዙ ካሰበ፣ ለምንድነው ጥቂቶቹ ብቻ ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉት?
READ
(5 min)
ደቀ መዛሙርት እና ቤተ ክርስቲያን
እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ - ጊዜ ስለደቀ መዛሙርት እና ስለቤተ ክርስቲያን እንነጋገራለን፡፡
ደቀ መዝሙር ምንድነው? ሰውን ደቀ መዝሙር የምታደርጉትስ እንዴት ነው?
አንድን የኢየሱስ ተከታይ የሆነን ሰው የእርሱን ትዕዛዛት ሁሉ እንዲታዘዝ የምታስተምሩት እንዴት ነው?
እንደ ዓለም እሥረኛ ይኖር የነበረን አንድን ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋ አድርጋችሁ የምታስታጥቁት እንዴት ነው?
ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል ትርጉሙ ተከታይ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ደቀ መዝሙር የእግዚአብሔር ተከታይ ነው፡፡
"ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።"
ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግሥት ኢየሱስ ንጉሣችን ነው፡፡ እኛም ዜጎቹ ነን፤ ፈቃዱን ለማገልገል የተሰጠን የእርሱ ዜጎች ነን፡፡ የእርሱ ፍላጎጎቶች፣ ዓላማዎች፣ የልብ ናፍቆቶች እርሱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እና እሴቶቹ በእኛ ዘንድ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውና የተመረጡ ናቸው፡፡
ቃሉ ሕጉ ነው፡፡ ስለዚህ የመንግሥቱ ሕግ ምንድነው? ዜጎቹ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የሚነግራቸው?
አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ፡፡" ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡"
ኢየሱስ እንዲህም ብሏል፡- "የእግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ትእዛዛት፣ ሕግ ሁሉ እና በነቢያት የተጻፉት በሁለት ነገሮች ተጠቃለዋል። እነርሱም፡- እግዚአብሔርን መውደድ እና ሰውን መውደድ ናቸው፡፡"
ኢየሱስ ያለው ይህን ነው፡- "ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡"
እርሱ አክሎ ያለውም ይህን ነው፡- "የነገርኳችሁን ሁሉ እንዲታዘዙ አስተምሯቸው፡፡"
ደቀ መዛሙርት ማድረግ የኢየሱስን ትዕዛዛት ማስተማርን የሚያጠቃልል በመሆኑ፣ አዲስ ኪዳን በአንድ ቃል ሲጠቃለል እንዲህ ሊባል ይችላል፡- "ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡"
ደቀ መዝሙር እግዚአብሔርን የሚወድ እና ሰዎችን የሚወድ፣ እንዲሁም ደቀ መዛሙርትን የሚያደርግ የኢየሱስ ተከታይ ነው፡፡
**ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነች? **
ምናልባትም ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንጻው ነው ብላችሁ ስታስቡ ኖራችኋል፤ አንድ የሆነ የምትሄዱበት ሥፍራ አድርጋችሁም ተረድታችሁታል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ግን ቤተ ክርስቲያን ማለት ስብስብ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ እናንተም እንደ ደቀ መዛሙርት አባል የሆናችሁበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡
"ቤተ ክርስቲያን" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሦስት የተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ውሏል፡-
- ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ፣ የነበሩ እና ገናም የሚሆኑ ሰዎች ሁሉ አባል የሆኑበት ማለት ነው፡፡
- የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ በዓለም ላይ በአንድ በተወሰነ ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ማለት ነው፡፡
- የቤት ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ስብስብ ሲሆን፣ ከተሰብሳቢዎቹ በአንዳቸው ወይም ከአንድ በላይ በሆኑት መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚሰባሰቡ ናቸው፡፡
አንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ፡- በአካባቢያቸው የሚገናኙ፣ እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ሰዎችን የሚወዱ እና ደቀ መዛሙርትን የሚያደርጉ እና በመጨረሻውን ዘመን ቤተ ክርስቲያንን የሚያንጹ የኢየሱስ ተከታዮች ናቸው፤ እንዲህ ያለችው ተቋም የቤት ወይም ያልተወሳሰበች - ቀላል ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
እንዲህ ያሉት ያልተወሳሰቡ ወይም ቀላል ቤተ ክርስቲያኖች ታላቅ ነገር ለመሥራት ሲሰባሰቡ፣ የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያንን ይፈጥራሉ፡፡
እነዚህ ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት በክልል ሲተሳሰሩም የታሪክን እና የሥፍራን አድማስ ተሻግረው ዓለም አቀፍ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ያንጻሉ፡፡
ቀላል የቤት ቤተ ክርስቲያን ይህች ናት፡፡
**ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስ ኢየሱስን ማዕከል እና ንጉሣቸው ያደረጉ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ **
ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ሰዎችን የሚወዱ እና ደቀ መዛሙርትን የሚያፈሩ እና የሚባዙ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው፡፡አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ህንጻዎች፣ መርሃ - ግብሮች እና በጀቶች እንዲሁም ቅጥር ሠራተኞች አሏቸው፡፡ ነገር ግን፣ ቀለል ያሉ የቤት ቤተ ክርስቲያናት እግዚአብሔርን ለመውደድ፣ ሰዎችን ለመውደድ እና ራሳቸውን የሚያባዙ ደቀ መዛሙርትን ለማባዛት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውስጥ ምንም አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንኛውም ተጨማሪ ነገር ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ የሚያወሳስባት እና ለመባዛቷ እንቅፋት የሚሆን በመሆኑ፣ ሥልጠናችን ውስጥ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎች፣ እንደ ቤተ ክስቲያን መርሃ-ግብሮች እና እንደ በጀት እንዲሁም እንደ ቅጥር ሠራተኞች ያሉትን ጉዳዮች በመባዛት መርህ ለታነጹት ለከተማ እና ለክልል አብያተ ክርስቲያናት እንተዋቸዋለን፡፡
ልብ አድርጉ፣ "ዙሜ" ማለት "እርሾ" ማለት ነው፤ ይህም ቅንጣት የሆነ አንድ የሴል ሕዋስ ሲሆን፣ ራሱን ግን በፍጥነት የሚያባዛ ወይም የሚያራባ ነው፡፡
በዙሜ ሥልጠና እኛም ልክ እንደዚያ እርሾው ቀላል እና የምንባዛ እንሆናለን፡፡ ከመባዛታችን አስቀድመን ግን እግዚአብሔር እንዲባዛ የሚፈልግው ምን እንደሆነ ስለማወቃችን እርግጠኛ እንሁን፡፡ ምክንያቱም መባዛት መልካም ነገር ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ግን መልካም ላይሆን ይችላል፡፡የካንሠር ሕመም የብዜት ውጤት ነው፡፡ ሆኖም ግን ገዳይ ነው፡፡ስለዚህ ሞትን ሳይሆን ሕይወትን የምናባዛው እንዴት ነው? ደቀ መዛሙርትን ማባዛት የተገባን ወይም ለዚህ የበቃን ደቀ መዛሙርት መሆናችንንስ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?
ተወያዩ
(10 min)
- ስለ ቤተ ክርስቲያን ስታስቡ ወደ አእምሮአችሁ የሚመጣው ምንድን ነው?
- በዚያ ስዕል እና በቪዲዮው ላይ እንደ ‹‹ቀላል ቤተ ክርስቲያን›› በተገለጸው መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
- የትኛውን ማባዛት ቀላል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ እና ምክኒያታችሁስ?
READ
(5 min)
እግዚአብሔርን መስማትና መታዘዝ
እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ከእግዚአብሔር ስለመስማት እና ለሰማነው ስለመታዘዝ እንማራለን፡፡ እስትንፋስ ሕይወት ነው፡፡ ዓየር ወደ ውስጥ እንስባለን፡፡ ወደ ውጪም እንተነፍሳለን፡፡ ሕይወት እንተነፍሳለን ማለት ነው፡ መተንፈስ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ያን ያክል በጣም አስፈላጊው ነገር ነው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን "እስትንፋስ" ብሎ ይጠራዋል፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከእግዚአብሔር ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በጸሎት ከእግዚአብሔር ስንሰማ እና ከእርሱ ጋር ስንነጋገርም እንዲሁ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በአካሉ፤ በቤተ ክርስቲያን ወይም በሌሎች የኢየሱስ ተከታዮች በኩልም የእግዚብሔርን ቃል ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በሥራዎቹ በኩል እርሱን ስንሰማ፤ ማለትም በሁነቶች፣ በልምዶች እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ልጆቹ በስደት እና በስቃይ ውስጥ እንዲያልፉ ሲፈቅድም፣ በዚያ ውስጥ እርሱን ስንሰማም፣ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከእግዚአብሔር የሰማነውን ወደ ተግባር ስንለውጥም መተንፈሳችን ነው፤ ስንታዘዝም እንዲሁ ወደ ውጪ መተንፈሳችን ነው፡፡ ወደ ውጪ መተንፈስ መታዘዝ፣ ለመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ - መታዘዝ፡፡ ለመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ ማለት አስተሳሰባችንን፣ የአፋችንን ቃል እና ተግባራችንን በመለወጥ ከኢየሱስ እና ከፈቃዱ ጋር እንዲጣመር ማድረግ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ ማለት ኢየሱስ ለእኛ ያካፈለውን፣ የሰጠንን በመስጠት እግዚአብሔር እኛን እንደባረከን ሌሎችም እንዲባረኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ለአንድ የኢየሱስ ተከታይ ይህ ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ እና ወደ ውጪ መተንፈስ አንገብጋቢ ጉደይ ነው፡፡ የሕይወቱም መሠረት ነው፡፡ "ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።" "እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።" ኢየሱስ እንዳለው የተናገረውን እና ያደረገውን እያንዳንዱን ነገር ለማከናወን መሠረት ያደረገው ከእግዚአብሔር በመስማት እና ያዳመጠውን ለመተግበር በመታዘዝ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ፡- እግዚአብሔርን ማዳመጥ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውጪ መተንፈስ፡- አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ለሰማው ነገር መታዘዝ እና የሰማውንም ለሌሎች ማካፈል ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው ተከታዮቹ በመንፈስ ቅዱስ - በእያንዳንዳችን እርሱን በምንከተው ሁሉ ላይ እፍ ባለው - በእስትንፋሱ ምክንያት ከእግዚአብሔርን እንሰማለን፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል::" ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ፡- እግዚአብሔርን ማዳመጥ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውጪ መተንፈስ፡- አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ለሰማው ነገር መታዘዝ እና የሰማውንም ለሌሎች ማካፈል ነው፡፡ ይህንን ሲል ኢየሱስ እንዴት መኖር እንዳለብን እያመላከተን ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምጽ የምንሰማው እንዴት ነው? የምንታዘዘውንስ ነገር የምናውቀው እንዴት ነው? ኢየሱስ "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" ብሏል፡፡ ተከታዮቹን ደግሞ "በጎቼ" ብሏቸዋል፡፡ ኢየሱስ እንዲህም ብሏል፡- በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፡፡ ኢየሱስ እንዳለውም የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ እግዚአብሔር የሚለውን ይሰማል፡፡ እናንተ የማትሰሙበት ምክንያት የእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታይ፣ ድምጹን ለመስማት ራሳችንን መስጠት - መቁረጥ አለብን፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው በጥሞና - ባለመናወጥ - በእርጋታ ሆነን ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው ኢየሱስ ላይ በማተኮር ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው በሃሳባችን፣ በራዕያችን፣ በስሜታችን እና በምናባችን ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ በትክክል የምንሰማው ስንጽፈው እና የሰማነውንም ስንመረምረው ነው፡፡ የሰማነው ሁሉ፣ ያሰብነው ሁሉ፣ በራዕያችን የታየን ሁሉ፣ የተሰማንም ሁሉ ወይ በምናባችን የተከሰተልን ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምጽ መሳይ የጠላት ድምጽም ይመጣል፡፡ ኢየሱስ እንዳለው ጠላታችን ውሸታም ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለውም ጠላታችን የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ከእርሱ እንደምንሰማ እና ሲናገርም እርሱ እንደሆነ እናውቃለን። በልምምድ እና በጸሎት የእርሱን ድምጽ እንደሚገባው ማወቅ እንችላለን፡፡ የምንሰማው ድምጽ ከእግዚአብሔር ይሁን ወይም ከሌላ መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት የምንሰማውን ድምጽ ለመመርመር የሚረዱ የተወሰኑ መንገዶች ናቸው፡- ኢየሱስ ሲናገር፣ ድምጹ ሁልጊዜም ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጣጣም መንገድ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ቀድሞ በነገረን መንገድ ነው፡፡ በድምጽ የምንሰማው ቃሉ ከተጻፈው ቃል ጋር በፍጹም አይጣረስም፤ አይምታታምም፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፣ ድምጹ ልባችንን በተስፋ እና በሰላም ይሞላዋል፡፡ ድምጹ በኩነኔ እና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ አይተወንም፡፡ ኢየሱስ ማንንም አይኮንንም፡፡ ከዚያ ይልቅ በፍቅር ያቀናናል፡፡ የኢየሱስ ድምጽ የሥጋን ሥራዎች፣ ወሲባዊ ኢ-ሥነምግባርን፣ የምንዝርናን፣ ቅድስና የለሽ ሃሳብን፣ ጣዖትን ማምለክን፣ ጥንቆላን፣ ጥላቻን እና ጸብን፣ ቅናት እና መራር ቁጣን፣ ራስ ወዳድነትን፣ አመጸኛ ተቃዋሚነትን፣ ክፍፍልን፣ ምቀኝነትን፣ ሥካርን እና ዘፋኝነትን በሰው ልብ ውስጥ አያነሳሳም፡፡ የእነዚህ ነገሮች ነገሮች መነሳሻ የእግዚአብሔር ድምጽ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፣ የኢየሱስ ድምጽ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬዎች ያፈራል፡፡ ፍቅርና ሃሴትን፣ ሰላምና ትዕግስትን፣ ርህራሄና ደግነትን፣ ታማኝነትን፣ ጨዋነትን እና ራስን መግዛትን ይሰጠናል፡፡ ኢየሱስ ሲናገር ድምጹ በጥርጥር ፋንታ መተማመንን ይሞላናል፡፡ በመጨረሻም፣ በውስጣችንም ከእግዚአብሔር የመስማትን ልምድ እና የድምጹን ሰላም እናውቃለን፡፡ ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ላንሰማ እንችላለን፡፡ ከድምጹ በመጨረሻ ማወቅ የሚገባንን የሚያሳውቀንን ያክል ብቻ ልንሰማ እንችላለን፡፡ የምንሰማው ግን ነገር ግን የጸና እና የማይቀለበስ ወይም የማይለወጥ ነው፡፡ ለኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ የምሥራቹ ይህ ነው፡- ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ውስጥ ዓየር ስንስብ፣ ዓየርን ወደ ውጪ ስንተነፍስ እና ለእግዚአብሔር በመታዘዝ የሰማነውን ለሌሎች ስናካፍል፣ እግዚአብሔር ከቀደመውም የበለጠ በግልጽ ይናገረናል፡፡ የእስትንፋሱን እፍታ ከቀደመውም በበለጠ በእኛ በኩል እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡ ድምጹንም የበለጠ ግልጽ በሆነ መንገድ እንሰማዋለን፡፡ የእርሱንም ድምጹ በሚገባ እናውቀዋለን፤ የሌላውን ድምጽ ግን አይደለም፡፡ ሥራውንም በዓለም ላይ እናየዋለን፤ ራሳችንንም በሥራው ተሳታፊ እናደርጋለን፡፡ ዓየር ወደ ውስጥ እንስባለን፡፡ ወደ ውጪም እንተነፍሳለን፡፡ ይህም ሕይወት ነው፡፡
ተወያዩ
(10 min)
- የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማትና ማወቅ መማሩ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
- ከጌታን መስማት እና ምላሽ መስጠት በእርግጥ ልክ እንደመተንፈስ ነውን? ለምን ወይም ለምንስ አይሆንም?
READ
(5 min)
S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
Zume ግብዓት ቅ.ም.ተ.ጸ.ማ.የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ኢየሱስ እንዲህ አለ -- ‹‹ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ 20ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤›› የኢየሱስ ተከታይ የሆነ እያንዳንዱ ሰው ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ የሚታዘዝ ከሆነ፣ ኢየሱስ ምን አንደሚያዝ ማወቅ ያስፈልገዋል። ታላቁ ትዕዛዝና ታላቁ ተልእኮ እግዚአብሔር የሚናገረን ነገር ታላቅ ማጠቃለያ ነው፣ ይሁንና የኢየሱስ ተከታይ እግዚአብሔር ወደፈጠረው ወደ ሙሉ መለኪያ የሚያድግ ከሆነ፣ የበለጠ ማወቅና መታዘዝ ያስፈልገዋል። ቅ.ም.ተ.ጸ.ማ የሚወክለው፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ምልከታ ትግበራ ጸሎት እና ማካፈል ነው ማንኛውም የጌታ ኢየሱስ ተከታይ ሊጠቀምበት የሚችለውን ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ ለመማርና ለማስታወስ ቀላል መንገድ ነው። እስቲ እያንዳንዱን ክፍል ትንሽ ተጨማሪ እንመልከት። መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ ወይም ስትሰሙ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት፦ ዛሬ ላይ በተለይም ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቅሶችን ፃፉ። ምልከታ፦ ትርጉሙን በተሻለ ለመገንዘብ እንዲረዳችሁ እነዚያን ጥቅሶች ወይም ቁልፍ ሀሳቦች በራሳችሁ ቃላት ጻፉ። ትግበራ፦ እነዚህን ትዕዛዛት ወይም ጽንሰ ሀሳቦች በራሳችሁ ህይወት ውስጥ መታዘዝ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ። የተለየ ምን ማድረግ ይኖርባችኃል? እነዚህን ፃፏቸው። ጸሎት፦ በቃሉ ውስጥ እያነበባችሁት ያለውን እና ትዕዛዙን ስለማክበርና የተማራችሁት በስራ ላይ ስለማስገባት የተረዳችሁን ነገር ለእግዚአብሔር የሚናገር ጸሎትን ጻፉ። ማካፈል፦ ስለተማራችሁት ነገር እና እንዴት እየተጠቀማችሁበት እንዳለ ለማን እንድትካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት። ስለዚህ እስቲ ቅ.ም.ተ.ጸ.ማየሚለውን ወደተግባር እናምጣው፦ ቅዱሳት መጻሕፍት፦ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‹‹ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና›› ይላል እግዚአብሔር። ‹‹ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።›› ኢሳ 55÷8-9 ምልከታ - ሰው ስለሆንኩ፣ የማውቀው ነገር እና የማደርገውን የማውቀው ላይ ውስን ነኝ። እግዚአብሔር ግን በምንም መንገድ አይገደብም። ሁሉንም ነገር ያያል እንዲሁም ያውቃል። ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል። ትግበራ - እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅና መንገዶቹ መልካም ስለሆኑ፣ በነገሮች መንገድ ከመታመን ይልቅ እሱን ከተከተልኩኝ በህይወቴ ውስጥ የበለጠ ስኬት አገኛለሁ። ጸሎት - ጌታ ሆይ፣ አንተን የሚያስደስትህን እና ሌሎችን የሚረዳ መልካም ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አላውቅም። መንገዶቼ ወደ ስህተቶች ያመራሉ። ሀሳቦቼ ወደ ጉዳት ይመራሉ። ይልቁኑም እባክህ መንገዶችህን እና ሃሳቦችህን አስተምረኝ። አንተን ስከተልህ መንፈስ ቅዱስህ እንዲመራኝ ፍቀድ። ማካፈል - እነዚህን ጥቅሶች እና ይህንን ትግበራ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እያለፈ እና ለሚገጥሙት አስፈላጊ ውሳኔዎች አቅጣጫ ለሚያስፈልገው ጓደኛዬ ስቲቭ አካፍላለሁ። S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት። በZume ግብዓት ውስጥ ካሉ ቀላል መሳሪያዎች አንዱ።
ልምምድ
(30 min)
SOAPS የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ቅዱሳት መጻሕፍት
ለእናንተ ልዩ ትርጉም ያላቸውን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቅሶችን ዛሬ ፃፉ።
ምልከታ
እነዚያን ጥቅሶች ወይም ቁልፍ ነጥቦች በተሻለ ለመረዳት በራሳችሁ አገላለፅ እንደገና ጻፏቸው።
ትግበራ
እነዚህን ትእዛዛት በህይወታችሁ መታዘዝ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ።
ጸሎት
ስለምን እንደተማራችሁ እና ለመታዘዝ ያቀዳችሁትን ለእግዚአብሔር የሚናገር ጸሎት ጻፉ።
ማካፈል
ስለተማራችሁት/ ስለተገበራችሁት ነገር ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት።
በትግበራ ያለ የ SOAPS ምሳሌ እነሆ፦
S - ‹‹ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና" ይላል እግዚአብሔር። ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።›› ኢሳ 55፥8-9
O - ሰው ስለሆንኩኝ፣ የማውቀው እና የማደርገውን የማውቀው ነገር ላይ ውስን ነኝ። እግዚአብሔር ግን ምንም ገደብ የለውም። ሁሉንም ነገር ያያል እና ያውቃል። ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል።
A - እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅ እና መንገዶቹ ምርጥ ስለሆኑ፣ በራሴ ነገሮች ከመታመን ይልቅ እሱን ብከተል ህይወቴ በበለጠ ስኬት ይሞላል።
P - ጌታ ሆይ፣ አንተን የሚያስደስትህን እና ሌሎችን የሚያግዝ ጥሩ ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አላውቅም። መንገዶቼ ወደ ስህተቶች ያመራሉ። ሀሳቦቼ ወደ ጉዳት ይመራሉ። ይልቁኑም እባክህ መንገዶችህን እና ሃሳቦችህን አስተምረኝ። አንተን እየተከተልኩህ እያለቅዱስ መንፈስህ ይምራኝ።
S - እነዚህን ጥቅሶች እና መተግበሪያውን ስቲቭ ከተባለ ጓደኛዬ ጋር እጋራለሁ፣ ጓደኛዬ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እያለፈ ስለሆነ ለሚወስናቸው አስፈላጊ ውሳኔዎች አቅጣጫ ያስፈልገዋል።
READ
(5 min)
የተጠያቂነት ቡድኖች
በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የተጠያቂነት ቡድኖች ኢየሱስም እንዲህ ብሏል፡- "…ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።" ኢየሱስ ተጠያቂነትን በተመለከተ ብዙ ታሪኮችን አካፍሏል በዚህም ስለምናደርገው እና ስለምንናገረው ነገር ተጠያቂ የመሆናችንንም እውነት በብዙ መንገድ አስታውቆናል። ኢየሱስ አሁንም እነዚህን ነገሮች ይነግረናል፤ ይኽም ለኋለኛው ጊዜ ዝግጁ እንድንሆን ነው። አንድ ቀን እኛ በእርሱ እንጠየቃለን፤ ስለዚህም አንዳችን በአንዳችን የመጠየቅን ልምምድ ከአሁኑ መለማመዳችን መልካም ነው። የተጠያቂነት ቡድኖች የሚመሠረቱት ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ነው፤ ይኸውም የሚቧደኑት ወንዶች ከወንዶች ጋር፣ ሴቶችም ከሴቶች ጋር ነው ማለት ነው። ቡድኖቹ በሳምንት አንድ ጊዜ እየተገናኙ ነገሮች በትክክል እየተከወኑ መሆናቸውን ለመረዳት፣ እንዲሁም ማስተካከያ ስለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንዲረዱ በተዘጋጁ ጥያቄዎች ላይ ውይይት እና ምክክር ያደርጋሉ። የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ተጠያቂ ነው፤ ስለዚህም ተጠያቂነትን ከሌሎች ተከታዮች ጋር መለማመድ ይገባዋል። የተጠያቂነት ቡድኖች፣ ሌላው በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት ውስጥ የሚገኝ ቀለል ያለ መሣሪያ ነው።
ልምምድ
(20 min)
የተጠያቂነት ቡድኖች
- እግዚአብሔርን እንዴት ሲሰራ አያችሁት?
- በዚህ ሳምንት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅነት በቃላቶቻችሁ እና በድርጅታችሁ ምስክር ሆናችኋልን?
- ለፆታዊ ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች ተጋልጣችኋል ወይንስ አእምሮአችሁ ባልተቀደሱ የጾታዊ አስተሳሰቦችን እንዲያዝናና ፈቅዳችኋል?
- በገንዘብ አጠቃቀማችሁ የእግዚአብሔርን ባለቤትነት እውቅና ሰጥታችኋል?
- የሆነ ነገር ከልብ ተመኝታችኋል?
- በቃላቶቻችሁ የአንድን ሰው ዝና ወይም ስሜት ጎድታችኋል?
- በቃልም ሆነ በተግባር ሐቀኝነት የጎደላችሁ ናችሁ ወይም ግብዝ ናችሁ?
- ሱስ የሚያስይዝ (ወይም ስንፍና ወይም ስነስርዓት የሌለው) ባህሪ ውስጥ ገብታችኋል?
- ለአልባስ፣ ለጓደኞች፣ ለስራ ወይም ለይዞታዎች ባሪያ ሆናችኋል?
- አንድን ሰው ይቅር ማለት ተስኗችኋል?
- እያጋጠሟችሁ ያሉ ስጋቶች ወይም ጭንቀቶች ምንድናቸው?
- አማራችኋል ወይም አጉረምርማችኃል?
- አመስጋኝ ልብን ይዛችሁ ቆይታችኋል?
- በወሳኝ ግንኙነቶቻችሁ ውስጥ አክባሪ፣ አስተዋይ እና ለጋስ ነበራችሁ?
- በሐሳባችሁ፣ በቃላችሁ ወይም በድርጊታችሁ ላይ ምን መሰናክሎች አጋጠማችሁ እና ምን ምላሽስ ሰጣችሁ?
- ሌሎችን፣ በተለይም አማኞችን ለማገልገል ወይም ለመባረክ የነበሯችሁን እድሎችን እንዴት ተጠቀማችሁ?
- ለጸሎት ልዩ መልስ አይታችኋል?
ይከልሱ
(1 min)
በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-
በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ መሳሪያዎች፡-
- እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
- የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
- መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
- የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
- S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
- የተጠያቂነት ቡድኖች
- እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል
- ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር
Take a Break
ማጠቃለያ
(1 min)
በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-
እና እነዚህን መሳሪያዎች ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን፡-
- እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
- የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
- መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
- የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
- S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
- የተጠያቂነት ቡድኖች
- እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል
- ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር
READ
(5 min)
ተጠቃሚ ሳይሆን አምራች
እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የኢየሱስ ተከታይ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከተራ ተጠቃሚነት ወጥቶ ወደ አምራችነት ሊለወጥ ወደሚችልበት መንገድ እንዲገባ እንዴት እንደምንረዳው እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነውን እቅዱን ሲያወጣ፣ አምራችነትን እና ተጠቃሚነትን አመጣጥነን፣ ለመፍጠር እና ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ባዶ ሆኖ መሞላት እና እንደገና የተሞላነውን ፈሰስ የማድረግን ሕይወት እንድንኖር አድርጎ ነው የሠራን፡፡ ነገር ግን በዚህ በወደቀችው ዓለማችን፣ ሰዎች የእግዚአብሔርን እቅድ በአመጽ ገፍተው ጥለዋል፤ ብዙዎቹም የእግዚአብሔርን ፍጹም እቅድ ሳይሆን ቁንጽል ሕይወት ለመኖር ኃይላቸውን ያጠፋሉ፡፡ ይማራሉ፤ ግን የተማሩትን ለሌሎች አያካፍሉም፡፡ ይሞላሉ፤ ነገር ግን ለሌሎች ፈሰስ አያደርጉም፡፡ ተጠቃሚ ናቸው፤ ነገር ግን አያመርቱም፡፡ የሚባዙ ደቀ መዛሙርትን ማድረግ የምንፈልግ ከሆነ፣ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን እንዴት አምራች እንደሚሆኑም ከእነርሱ ጋር መከፋፈል አለብን፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? ለሚለው፣ እግዚአብሔር እኛን በመንፈሳዊነት ለማሳደግ የተጻፈ ቃሉን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቀማል፡፡ እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ለመታጠቅ መማር፣ ቃሉን በአግባቡ መተርጎም እና በተግባር ማዋል አለበት፡፡ በሺህ በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ፣ በብዙ ጸሐፊዎች አማካኝነት እግዚአብሔር ቃሉን ለታመኑቱ፣ ሰምተው ለሚቀበሉት እና የሰሙትንም ለሌሎች ለሚያስተላልፉ ሰዎች ተናግሯል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔርን ታሪክ፣ እቅዱን፣ የልቡን ሃሳብና መንገዱን ይነግሩናል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍለ-ጊዜ ስለሁለት ቀላል መሣሪያዎች ተምረናል፤ እነዚህም መ.መ.ማ.ጸ.ማ. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የተጠያቂነት ቡድኖች ናቸው፡፡ በቀጣዩ ክፍለ-ጊዜም ስለአንድ ተጨማሪ ቀላል መሣሪያ ትማራላችሁ፤ ይህም የ3 - 3 ቡድኖች ነው፡፡ እነዚህ ሦስት መሣሪዎች በጋራ አዳዲስ ተከታዮች የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማሩ፣ እንዲተረጉሙ እና በተግባር ላይ እንዲያውሉ ለመርዳት በቅንጅት የሚሠሩ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሚዎች ብቻ ሳይሆኑ አድራጊዎች፣ እንዲሁም አካፋዮች እንዲሆኑም ጭምር ይማራሉ፡፡ እግዚአብሔርም የተጻፈውን ቃል ለመንፈሳዊ እድገታችን እንዲሆን ይጠቀምበታል፡፡ ይህም እኛ በጸሎት የምንለየው ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን መስማት እና ለእግዚአብሔር መናገር ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን በቅርበት እንድናውቀው፣ የልቡን ሃሳብ፣ ፈቃድ እና መንገዶቹን እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ ጸሎት ሌሎችን ለማገልገል እና ለመርዳት ያግዘናል፤ ግለሰቦችን በግል እንዲሁም ሰዎች እንደ ቡድን በተወሰኑ መንገዶች እንድንረዳቸው እና እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ እንዲያውቁ እንድናስተምራቸውም ይደግፈናል፡፡ ሁለት ቀላል መሣሪያዎች፤ የጉዞ ጸሎት እና የጸሎት ዑደት፡- ሰዎች በግላቸው የግል ጸሎትን ሕይወት እንዲያሳድጉ እና ሌሎችን በሚያገለግሉበት መንገድ መጸለይን እንዲማሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች ያለማቋረጥ የመጸለይን ልማድ እንዲያዳብሩ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ዓለምንም በዓይን በሚታየው እና በጆሮ በሚሰማው ብቻ ከመመዘን ይልቅ ከመንፈሳዊው ዓለም አንጻር መመልከትን እንዲማሩ ያደርጋሉ፡፡ በዘላቂነት ጥቅም ላይ ሲውሉም የኢየሱስን ተከታዮች የመጸለይን ብቃት እንዲጨምሩ ያደርጋሉ፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር የመስማትን ችሎታ እንዲጨምሩና የሰሙትንም ለሌሎች እንዲያካፍሉ ያደርጋሉ፡፡ እግዚአብሔር የክርስቶስን አካል፤ አማኞችን - "ቤተ ክርስቲያን" ብለን የምንጠራትን፣ እኛን በመንፈሳዊነት ለማሳደግ ይጠቀምበታል፡፡ እንደ አማኞች ስብስብ፣ አንዳችን ከአንዳችን ጋር የታሳሰርን ነን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው በኢየሱስ የሆንን እኛ ብዙ የአካል ክፍሎች ብንሆንም አንድ አካል ነን፤ አንዳችን የአንዳችን ነን፡፡ በሌላ አባባል፣ ትሥሥራችን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ አይደለም አንዳችን ከአንዳችን ጋርም የተሣሠርን ነን፡፡ እግዚአብሔር የሚነግረን አንዳችን ለአንዳችን ራሳችንን እንድንሰጥ እና አንዳችን አንዳችንን እንድናገለግል ነው፡፡ እያንዳንዳችን የተለያየ ዓይነት ጥንካሬ እና ደካማ ጎን አለን፡፡ እግዚአብሔርም በጠንካራ ጎናችን ድካም ያለባቸውን ሰዎች እንድንደግፍ ከእኛ ይጠብቀዋል፡፡ በደካማ ጎናችንም ደግሞ እርሱ የሰጣቸውን ብርታት ተጠቅመው ለሚደግፉን ለሌሎች ሰዎች ፈቃደኛ መሆናችንንም ከእኛ ይጠብቃል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ሰጥቷል፤ ስጦታዎቻችን አንዳችን አንዳችንን ለመደገፍ ማዋላቸውን ማረጋገጥ ይገባናል፤ የእያንዳንዳችን ስጦታዎች ወደ ሌላችን በመተላለፋቸው ውስጥ ዘርፈ-ብዙ የእግዚአብሔር በረከቶች መተላለፋቸውን ተረዱ፡፡ እንደ 3 - 3ኛዎቹ እና እንደተጠያቂነት ቡድኖች ያሉ ቀላል መሣሪያዎች፣ እንዲሁም አቻ አሳዳጊ የአማካሪ ቡድኖች አንዳችን ለአንዳችን እንድንረዳዳ፣ ሌሎችን እንድንወድድ እና በጎ ሥራዎችን እንድንሠራ የሚያበረታቱን እግዚአብሔር እንድናደርግ ያዘዘንን እንድንታዘዝ በማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ የተማርነውን ለሌሎች የምናካፍልበትን መንገድ እንድናገኝም ድጋፍ ያደርጉልናል፡፡ ስለኢየሱስ የሚደርስብንን ስደትና ስቃያችንን - መስዋዕትነት እና መጥፋታችንንም እግዚአብሔር እኛን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማሳደግ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ኢየሱስን በመውደዳችን እና በመታዘዛችን ምክንያት ሰዎች ጫና ሲያደርጉብን እና ጉዳት ሲያደርሱብን፣ ወይም ኢየሱስን እየወደድን እና እየታዘዝንም እንኳን ስደትና መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን ሲከሰቱ፣ እግዚአብሔር ስቃዮቻችንን ባሕርያችንን ለማጥራት እና የበለጠ የክርስቶስን መልክ እንድንይዝ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል፡፡ እርሱ ባሕርያችንን ያበለጽጋል፡፡ ያበረታናል፡፡ እንዲሁም እምነታችንን ያጠራል፡፡ አገልግሎታችንም ብቁ ያደርገዋል፡፡ ከዚያም በተለየ መንገድ በሕይወት ስቃይ እያዩ ያሉትንም እንድናገለግል ያደርገናል፡፡ ሁሉንም ሲያደርግ በሚያውቁን እና ሕመማችንን በሚረዱ ሰዎች ሁሉ ፊት ራሱን የበለጠ በመግለጥ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታዮች መሰደድ ሊያጋጥመን እንደሚችል እግዚአብሔር ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።" እንደ 3 - 3ኛ ቡድኖች እና እንደተጠሪነት ቡድኖች ያሉት ቀላል መሣሪያዎች የእግዚአብሔር ተከታዮች ስለገጠማቸው ስደትና ስቃይ ለሌሎች የሚያካፍሉበትን እድል ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህ ቡድኖች የኢየሱስን ተከታዮች የእግዚአብሔር ቃል ከባድ ጊዜዎች እንደሚያጋጥሟቸው እና እንዲህም ባሉ ሁኔታዎች ምንም እንኳን ነገሮች በተበላሸ ገጽታ ቢከሰቱም፣ ቃሉ ላይ ተደግፈው እንዴት ማለፍ እንደሚገባቸው ለማስተማር እድል ይሰጧችኋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ጸሎት፤ የአካል ሕይወት፤ ስደት እና ስቃይ፡፡ እነዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ፍጹም ወደ ሆነው ወደ ልጁ፣ ወደ ኢየሱስ መልክ እኛን የሚያሳድግባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቀላል መንገዶች እግዚአብሔር ከሚሰጠን መልካም ነገሮች ተጠቃሚዎች ብቻ እንዳንሆን፣ ነገር ግን አዘጋጆች እና አካፋዮች እንድንሆንም ይረዱናል፡፡
ተወያዩ
(10 min)
- ከላይ ከተዘረዘሩት አራት ዘርፎች (ጸሎት፣ የእግዚአብሔር ቃል፣ ወዘተ.) ውስጥ የትኞቹን አስቀድማችሁ እየተለማመዳችሁ?
- ስለ የትኞቹ ነው እርግጠኛ የማይሰማችሁ?
- ሌሎችን በማሰልጠን ረገድ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል?
READ
(5 min)
የጸሎት ዑደት
በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የጸሎት ዑደት ኢየሱስ ለተከታዮቹ ስለጸሎት ዓላማ፣ ትግበራ እና ስለተስፋ ቃሎቹ አስተምሯቸዋል። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።" ኢየሱስ ያስተማረው፣ ጸሎት ለሰዎች ለአደባባይ ታይታ-ክብር ማግኛ፣ ራስ-ተኮር የምኞት ዝርዝር ወይም ረብ-አልባ ንግግርን መደጋገም አለመሆኑን ነው። ኢየሱስ ያስተማረን ጸሎት ከሚወደን የሰማዩ አባታችን ጋር ቀጣይነት እና ቀጥተኛ ንግግር ማድረግ በመሆኑ በውስጡ ኃይል ያለው ነገር ነው። ልክ እንደማንኛውም መልካም ንግግር፣ መልካም ጸሎት ማለት በተናጋሪዎቹ መካከል መደማመጥ እና ንግግር ያለበት ነው። ዓለማትን ከፈጠረው ሕያው እግዚአብሔር ጋር መነጋገር ግን አስፈሪ ሊመስል ይችላል። ከመንፈሳዊው ዓለም በትክክል መስማት በእርግጥም ለብዙ ሰዎች ፍጹም አስፈሪ ክስተት ነው። መልካሙ ዜና ግን ይህ ነው፡- በጸሎት በርትተን ከወዳጃችን ከእግዚአብሔር ጋር በተሻለ ሁኔታ ጥልቅ ንግግር ማድረግ የሚቻል ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርም በትክክል የሚፈልገው ይህንን መሆኑ ነው። ነገር ግን ጸሎት ልክ አዲስ ቋንቋን እንደመልመድ ሲሆን፣ ጸሎታችሁን የምታሻሽሉት እንዴት ነው? መልሱ ቀላል ነው፤ ትለማመዳላችሁ። የጸሎት ዑደት ጸሎትን መለማመጃ እና እናንተ በራሳችሁ መጠቀም የምትችሉት እና ለማንኛውም የኢየሱስ ተከታይ ልታስተላልፉት የምትችሉት ቀላል መሣሪያ ነው። እያንዳንዱ 5 ደቂቃዎችን በሚወስዱ በ12 ቀላል ደረጃዎች፣ የጸሎት ዑደት አሥራ ሁለት ወደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ወደሚያስተምራቸው መንገዶች ይመራችኋል በመጨረሻም፣ አንድ ሰዓት የምትጸልዩበት መንገድ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል፡- "ሳታቋርጡ ጸልዩ።" ይህንን ማድረግ መቻላችንን ሁላችንም መናገር አንችልም። በዚህ መልኩ አንድ ሰዓት ከጸለይን በኋላ፣ አንድ ደረጃ ትቀርባላችሁ። የጸሎት ዑደት በዙሜ ቋት ከሚገኙት መካከል አንዱ ተጨማሪ መሣሪያ ነው።
ልምምድ
(60 min)
የጸሎት ዑደት
እያንዳንዳቸው 5 ደቂቃ በሚፈጁ በ12 ቀላል እርምጃዎች - መጽሐፍ ቅዱስ እንድንጸልይ በሚያስተምረን 12 መንገዶች ይህ የጸሎት ዑደት ይመራችኋል። በመጨረሻም፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ትጸልያላችሁ።

አመስግኑ የጸሎት ጊዜያችሁን ጌታን በማመስገን ጀምሩ። በሃሳባችሁ ለሚመጡት ነገሮች አመስግኑት። ባለፈው ሳምንት በህይወታችሁ ስላደረገው አንድ ልዩ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑት። ለቤተሰባችሁ ስላደረገው በጎነት አመስግኑት።
ጠብቁ ጌታን በመጠባበቅ ጊዜያችሁን አሳልፉ። በዝምታ ላይ ሃሳቡን እንዲነግራችሁ ፍቀዱለት።
ተናዘዙ እርስን የማያስደስት በህይወታችሁ ያለ ማንኛውንም ነገር እንዲያሳያችሁ መንፈስ ቅዱስን ለምኑት። የተሳሳቱ ዘንባሌዎቻችሁን እንዲጠቁማችሁ ጠይቁት፣ ከዚያም የንስሃ ጸሎት ያላደረጋችሁባቸው የተወሰኑ ድርጊቶችን እንዲገልጽላችሁ ጠይቁት። ከሃጢያታችሁ አሁን ለጌታ ተናዘዙ።
ቃሉን አንብቡ በመዝሙር፣ በነቢያት ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ባሉት ስለ ጸሎት የሚናገሩ ምንባቦችን የምታነቡበትን ጊዜ አሳልፉ።
ጠይቁ። እራሳችሁን ወክላችሁ
ምልጃ ሌሎችን ወክላችሁ ጠይቁ።
ቃሉን ጸልዩ ልዩ ምንባቦችን ጸልዩ። ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት ያደረጉ ጸሎቶችም ሆኑ ብዙ መዝሙሮች ለዚህ አላማ የሚጠቅሙ ናቸው።
አክብሩት በህይወታችሁ ውስጥ ስላሉት ነገሮች፣ በቤተሰባችሁ እና ቤተክርስቲያናችሁ ስም ጌታን አክብሩት።
ዘምሩ የምስጋና ወይም የአምልኮ ወይም ሌላ ዜማ ወይም መንፈሳዊ መዝሙር ዘምሩ።
አሰላስሉ ጌታ እንዲያናግራችሁ ለምኑት። የሚሰጣችሁን ስሜት ለመጻፍ እስክሪብቶ እና ወረቀት አዘጋጁ።
አዳምጡ ያነበባችሁትን፣ የጸለያችኋቸውን እና የዘመራችኋቸውን ነገሮች በማቀናጀት ጊዜ አሳልፉ፤ ጌታ እናንተን ለማናገር እንዴት ሁሉንም እንዳጣመራቸው ተመልከቱ።
አመስግኑት ከእርሱ ጋር ስላሳለፋችሁት ጊዜ እና እሱ ለሰጣችሁ ግንዛቤዎች ጌታን አመስግኑት ። ስለ ክቡር ባህሪያቱ አመስግኑት።
የDick Eastman መፅሃፍ The Hour that Changes the World (C) 2002 በ Dick Eastman ፣ Chosen Books፣ Grand Rapids፣ MI፣ በፍቃድ ጥቅም ላይ የዋለ።
ተወያዩ
(10 min)
- በጸሎት አንድ ሰአት ስለ ማሳለፍ ምን ምላሽ አላችሁ?
- ምን ተሰማችሁ?
- የተማራችሁት ወይም የሰማችሁት ነገር አለ?
- እንዲህ መሰሉን ጸሎት የዘወትር ልማድ ብታደርጉት ኖሮ ሕይወት ምን ትመስል ነበር?
READ
(5 min)
የ100 ዝርዝር
በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የ100 ሰዎች ስም ዝርዝር ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "እንግዲህ ሂዱና … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" ተከታዮቹም ያደረጉት ያላቸውን ነው። ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል። ወደ ጓደኞቻቸው ሄደዋል። በከተማቸው ወደሚያውቋቸውም ሰዎች ሄደዋል። አብረዋቸው ወደሚሰሩም ሰዎች ሄደዋል። ኢየሱስ "ሂዱ…" ነበር ያለው፤ እነርሱም እንዳላቸው በመሄድ ታዘዙ። የእግዚአብሔርም ቤተሰብ አደገ። እግዚአብሔር "እንድንሄድ እና ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ" የሚያስፈልገንን የግንኙነት መስመር ዘርግቶልናል። እነዚህም ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ጎረቤቶቻችን፣ አብረናቸው የምንሠራ እና የክፍል ጓደኞቻችን - በአጠቃላይ በሕይወታችን የምናውቃቸው እና ያገኘናቸው ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር በሕይወታችን ላስቀመጣቸው ለእነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ታማኝ በመሆን ደቀ መዛሙርትን በማፍራት ረገድ የመጀመሪያው ትልቅ ርምጃ ነው። ይህም ስም ዝርዝራቸውን ከመያዝ ቀላል ደረጃ ሊጀመር የሚችል ነው። የመቶ ሰዎች ስም ዝርዝር በዙሜ የመረጃ ቋት ውስጥ ካሉ ደቀ መዛሙርትን የማፍሪያ ቀላል መሣሪያዎች አንዱ ነው።
ልምምድ
(30 min)
የራስዎን የ100 ዝርዝር ይፍጠሩ
የዝምድናዎቻችሁን ዝርዝር ይሥሩ፤ በተጽዕኖ ክበባችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጻፉ። እያንዳንዱ ሰው ደቀ መዝሙር እንደሆነ፣ የማያምን እንደሆነ፣ ወይም የማይታወቅ እንደሆነ ምልክት ያድርጉ።
በቡድን ሆናችሁ እያንዳንዳችሁ የራሳችሁን ዝርዝር ለመሥራት ጊዜ ውሰዱ። ወረቀት ወይም በስልጠና ቁሳቁሶቻችሁ ውስጥ ያሉትን ዲጂታል መገልገያዎች መጠቀም ትችላላችሁ።
ይከልሱ
(1 min)
በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-
በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ መሳሪያዎች፡-
- እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
- የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
- መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
- የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
- S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
- የተጠያቂነት ቡድኖች
- እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል
- ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር