የZúme የግላዊነት ፖሊሲ

ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የተዘጋጀው ‹‹ማንነት የሚለይ መረጃ›› (PII) በመስመር ላይ ላይ ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ አስመልክቶ ስጋት ውስጥ የሚገቡ ሰዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ነው። በዩናይትድ ስቴትስ የግላዊነት ህግ እና የመረጃ ደህንነት ላይ እንደተገለጸው፣ PII ማለት አንድን ሰው ለመለየት፣ ለማነጋገር ወይም ለማግኘት ወይም አንድን ግለሰብ በአውድ ውስጥ ለመለየት በራሱ ወይም ከሌላ መረጃ ጋር ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መረጃ ማለት ነው። ማንነትን የሚለይ መረጃዎን ከድረ-ገጻችን ጋር በመሄደው መሰረት እንዴት እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀምበት፣ እንደምንጠብቀው ወይም በሌላ መንገድ እንዴት እንደምንይዝ ግልጽ መረዳት አንዲኖርዎት፣ እባክዎ የግላዊነት ፖሊሲያችንን ያንብቡ።

የማህበራዊ መለያ መግቢያዎች ምን አይነት ፈቃዶችን ይጠይቃሉ?

ከዚህ በታች ያሉት የግለ ማህደር ክፍሎች Facebook ወይም Google መግቢያ ጥቅም ላይ ከዋሉ ይለወጣሉ።

  • ይፋ ግለ ማህደር። ይህ እንደ መታወቂያ፣ ስም፣ ምስል፣ ጾታ እና አካባቢያቸው ያሉ የተወሰኑ የተጠቃሚ ውሂብን ያካትታል።
  • የኢሜይል አድራሻ።

ድረ-ገፃችን ተጠቅመን ከህዝቡ የምንሰበስበው ምን አይነት ግላዊ መረጃ ነው?

አንዳንድ ግላዊ መረጃ ለድረ-ገጹ ትክክለኛ አሰራር ክትትል የሚደረግበት ሲሆን ሌላ መረጃ ተጠይቆ ለተጨማሪ ስልጠና እና ድጋፍ ተቀምጧል።

  • የጣቢያውን እና የተግባቦት ግላዊ ጥራትን ለማሻሻል እንዲሁም ለደንበኞች አገልግሎት ጥያቄዎችና ስልጠናዎች የተጠቃሚው ትክክለኛ ስም ወይም ቅጽል ስም ይጠየቃል።
  • ትክክለኛውን የጣቢያ እና የተግባቦት ተግባር ለመደገፍ እና ተጠቃሚውን በተገቢው ስልጠና እና ግብዓቶች ለማገናኘት እንዲያግዘን የተጠቃሚ ቋንቋ ምርጫ ይከማቻል።
  • መለያ ለመፍጠር የተጠቃሚው ኢሜይል አድራሻ የሚያስፈልግ ሲሆን ለልውውጥ ግንኙነት እንደ የጣቢያ አሠራር አካል ሆኖ ያገለግላል።
  • ነፃ የማሰልጠን አገልግሎትን ለመደገፍ አላማ ሲባል የተጠቃሚው ስልክ ቁጥር ተሰብስቦ ይከማቻል።
  • የተጠቃሚ ከተማ የጣቢያ ግብዓቶችን እና ተግባቦቶችን ለግል የተበጀ ለማድረግ እና ተጠቃሚዎችን ከተገቢው የስልጠና እና የደንበኞች አገልግሎት ግብዓቶች ጋር ለማገናኘት ይጠየቃል።

መረጃ የምንሰበስበው መቼ ነው?

  • በመለያ በሚገባበት ወቅት የእርስዎን መረጃ እንሰበስባለን።
  • እንዲሁም በስልጠና ኮርስ እና በጣቢያ አጠቃቀም በኩል አፈፃፀምዎን እንከታተላለን።
  • በተለያዩ የምዝገባና የጥያቄ ቅጾች በኩል አስፈላጊ መረጃን ሁሉ እንጠይቃለን።

መረጃዎን እንዴት የምንጠቀመው እንዴት ነው?

  • በኢሜይል አድራሻዎ መሰረት በzume ስርዓት ውስጥ የተጠቃሚ መለያ ለመፍጠር መረጃዎን እንጠቀማለን።
  • እንደ የይለፍ ቃል ዳግም ማስጀመሪያ ጥያቄዎችና ሌሎች የስርዓት ማሳወቂያዎች ባሉ መሰረታዊ የልውውጥ ኢሜይሎች ኢሜይል እንልክልዎታለን።
  • በስልጠናው ሂደትዎ መሰረት አልፎ አልፎ ማሳሰቢያዎችን እና ማበረታቻዎችን በኢሜይል እንልክልዎታለን።

መረጃዎን የምንጠብቀው እንዴት ነው?

ምንም እንኳ በመስመር ላይ የሚተላለፉ ሚስጥራዊነት ያላቸውን መረጃዎች ለመጠበቅ ምስጠራን የምንጠቀም ቢሆንም መረጃዎን ከመስመር ላይ ውጪ እንጠብቀዋለን። በግል የሚለይ መረጃን የማግኘት መብት የተሰጣቸው አንድ የተወሰነ ስራ ለመስራት መረጃ የሚያስፈልጋቸው የቡድን አባላት ብቻ (ለምሳሌ፣ የድር አስተዳዳሪ ወይም የደንበኛ አገልግሎት) ብቻ ናቸው።

ግላዊ መረጃዎ ደህንነቱ ከተጠበቁ አውታረ መረቦች ጀርባ የተቀመጠ ነው፤ ለእንደዚህ አይነት ስርዓቶች ልዩ የመዳረሻ መብት ባላቸው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተደራሽ ሲሆን መረጃውን በሚስጥር እንዲይዙ ይገደዳሉ። በተጨማሪም፣ እርስዎ የሚያቀርቡት ሁሉም ሚስጥራዊነት ያለው/የክሬዲት መረጃ በSecure Socket Layer (SSL) ቴክኖሎጂ የተመሰጠረ ነው።

የግላዊ መረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ ስንል አንድ ተጠቃሚ ሲያስረክብ ወይም መረጃውን ሲደርስ የተለያዩ የደህንነት እርምጃዎችን እንተገብራለን።

‹‹ኩኪዎችን›› እንጠቀማለን?

ማናቸውም የኩኪዎች ወይም ሌሎች የመከታተያ መገልገያዎች - በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር፣ ተጠቃሚዎችን ለመለየትና ምርጫዎቻቸውን በማስታወስ በተጠቃሚው የሚፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት አላማ ብቻ ያገለግላሉ።

የእርስዎ የመረጃ ተደራሽነትና ቁጥጥር።

በ«አግኙን» ገጻችን በኩል እኛን በማነጋገር በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ።

  • ከእኛ ጋር ባደረጉት እንቅስቃሴ ምን ውሂብ እንዳሰባሰብን መመልከት።
  • ስለእርስዎ ያለንን ማንኛውንም ውሂብ መቀየር/ማስተካከል።
  • መለያዎን ወይም ስለእርስዎ ያለንን ማንኛውንም ውሂብ እንድንሰርዝ ማድረግ።
  • በእኛ የውሂብ አጠቃቀም ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ስጋት መግለፅ።
  • ከእኛ ሊኖርዎት ከሚችል ማንኛውም የወደፊት ግንኙነት መርጠው መውጣት።

አግኙን

ዝማኔዎች

የግላዊነት መመሪያችን በየጊዜው ሊለወጥ ይችላል፤ እንዲሁም ሁሉም ዝማኔዎች በዚህ ገጽ ላይ የሚለጠፉ ይሆናል።