Zúme Training Guidebook

20-Session Course

ክፍለ ጊዜ 1

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 3354

ፀልዩ

(5 min)

በጸሎት ጀምሩ። ያለ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ማስተዋል ማግኘትና መለወጥ አይቻልም። በዚህ ክፍለ ጊዜ ወቅት እንደ ቡድን መንፈስ ቅዱስን ለመጋበዝ ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

  • እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
  • የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
  • መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።

READ

(5 min)

እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል

ወደ ዙሜ ሥልጠና እንኳን በደህና መጣችሁ! ዙሜ(Zume) የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "እርሾ" ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው የእግዚአብሔር መንግሥት ጥቂት "እርሾ" ወስዳ ብዙ ሊጥ ውስጥ የከተተችን ሴት ትመስላለች፡፡ ሴት የዋ እርሾውን በሊጡ ውስጥ ስታኖረውም፣ እርሾው ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካው ድረስ ይስፋፋል፡፡ በዚህም ንግግሩ ኢየሱስ ያስረዳው አንድ ተራ ሰው በጣም ትንሽ ነገር ወስዶ ታላቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነን ነገር ለመፍጠር ሊጠቀምበት እንደሚችል ነው! ሕልማችን ኢየሱስ ያለውን ለማድረግ ነው… በዓለም ሁሉ ያሉ "ተራ" የሚባሉ ሰዎች ታናናሽ መሣሪያዎችን ወስደው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታላቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ መርዳት! ኢየሱስ ለተከታዮቹ በመጨረሻ ጊዜ የሰጣቸው ትዕዛዝ ለመረዳት ቀላል ነበሩ፡፡ እንዲህ ነው ያላቸው፡- "ሥልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" የኢየሱስ ትዕዛዝ ቀላል ነው፤ "ደቀ መዛሙርት አድርጉ" የሚል ነው፡፡ ትዕዛዙን እንዴት እንደሚፈጽሙም የነገራቸው ነገር ቀላል ነው፤ በምትሄዱበት ሁሉ ደቀ መዛሙርትን አድርጉ፡- በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዘውን ሁሉ እንዲያከብሩ እነርሱን በማስተማር ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤ ሆኖም አንድን ሰው ደቀ መዝሙር ማድረግ ምን ምን ደረጃዎች አሉት? 1 - ደቀ መዛሙርት ማድረግ ያለብን ሁልጊዜ ነው፤ የትም ብንሄድ፤ 2 - አንድ ሰው ኢየሱስን ለመከተል ሲወስን - መጠመቅ አለበት፡፡ 3 - አንድ ሰው ኢየሱስን በመከተል እያደገ ሲሄድ፣ ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ እንዴት መታዘዝ እንዳለበት ማስተማር ይገባል፡፡ ኢየሱስ ካዘዛቸው ነገሮች አንዱ ደቀ መዝሙር ማድረግ እንደመሆኑ፣ ኢየሱስን የሚከተል ሁሉ ሰዎችን እንዴት ደቀ መዝሙር ማድረግ እንዳለበት መማር አለበት፡፡ ደቀ መዛሙርት ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ እነዚያ ደቀ መዛሙርት የሆኑትም ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ ደቀ መዛሙርትን ማብዛት አለባቸው፡፡ ዙሜ የሚሠራውም እንደዚህ ነው፡፡ ልክ እንደ እርሾ ነው፤ ሊጡ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሊጡ ውስጥ ይሠራል፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ደቀ መዛሙርትን እንዲፈሩ ሲያዛቸው፣ አንድ የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል፤ "እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሏቸዋል፡፡ የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ እርሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር የመሆኑን ነገር ሊያስበው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ እንዳለው ከእኛ ጋር ስለሆነ! ይህም ማለት የእርሱ ተከታይ የሆንን እኛ እያንዳንዳችን ደቀ መዛሙርትን እንድናፈራ ለሚፈልገው ለኢየሱስ ራሳችንን ማስገዛት አለብን ማለት ነው፡፡ እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "… ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ... ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" እኛን የላከን ኢየሱስ የተደገፈበት ሥልጣን … የራሱ ሥልጣን ነው፡፡ እርሱ እንዳለውም ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን የለም፡፡ ከእርሱም የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ትውፊት የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ባህልም የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ሕግም በምድር ላይ አልታየም፡፡ ኢየሱስ ያለው ይህንን ነው፡- "ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡" ሥራው ሁሉ ተሠርቶ እስኪያልቅ ድረስ፣ ልክ እንደ ዙሜ - ልክ እንደ እርሾ - መሄዳችንን እና ማደጋችንን እንቀጥላለን፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ኢየሱስ ሁሉም ተከታዮቹ ለታላቁ ተልዕኮ እንዲታዘዙ ካሰበ፣ ለምንድነው ጥቂቶቹ ብቻ ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉት?

READ

(5 min)

ደቀ መዛሙርት እና ቤተ ክርስቲያን

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ - ጊዜ ስለደቀ መዛሙርት እና ስለቤተ ክርስቲያን እንነጋገራለን፡፡

ደቀ መዝሙር ምንድነው? ሰውን ደቀ መዝሙር የምታደርጉትስ እንዴት ነው?

አንድን የኢየሱስ ተከታይ የሆነን ሰው የእርሱን ትዕዛዛት ሁሉ እንዲታዘዝ የምታስተምሩት እንዴት ነው?

እንደ ዓለም እሥረኛ ይኖር የነበረን አንድን ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋ አድርጋችሁ የምታስታጥቁት እንዴት ነው?

ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል ትርጉሙ ተከታይ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ደቀ መዝሙር የእግዚአብሔር ተከታይ ነው፡፡

"ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።"

ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግሥት ኢየሱስ ንጉሣችን ነው፡፡ እኛም ዜጎቹ ነን፤ ፈቃዱን ለማገልገል የተሰጠን የእርሱ ዜጎች ነን፡፡ የእርሱ ፍላጎጎቶች፣ ዓላማዎች፣ የልብ ናፍቆቶች እርሱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እና እሴቶቹ በእኛ ዘንድ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውና የተመረጡ ናቸው፡፡

ቃሉ ሕጉ ነው፡፡ ስለዚህ የመንግሥቱ ሕግ ምንድነው? ዜጎቹ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የሚነግራቸው?

አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ፡፡" ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡"

ኢየሱስ እንዲህም ብሏል፡- "የእግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ትእዛዛት፣ ሕግ ሁሉ እና በነቢያት የተጻፉት በሁለት ነገሮች ተጠቃለዋል። እነርሱም፡- እግዚአብሔርን መውደድ እና ሰውን መውደድ ናቸው፡፡"

ኢየሱስ ያለው ይህን ነው፡- "ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡"

እርሱ አክሎ ያለውም ይህን ነው፡- "የነገርኳችሁን ሁሉ እንዲታዘዙ አስተምሯቸው፡፡"

ደቀ መዛሙርት ማድረግ የኢየሱስን ትዕዛዛት ማስተማርን የሚያጠቃልል በመሆኑ፣ አዲስ ኪዳን በአንድ ቃል ሲጠቃለል እንዲህ ሊባል ይችላል፡- "ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡"

ደቀ መዝሙር እግዚአብሔርን የሚወድ እና ሰዎችን የሚወድ፣ እንዲሁም ደቀ መዛሙርትን የሚያደርግ የኢየሱስ ተከታይ ነው፡፡

**ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነች? **

ምናልባትም ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንጻው ነው ብላችሁ ስታስቡ ኖራችኋል፤ አንድ የሆነ የምትሄዱበት ሥፍራ አድርጋችሁም ተረድታችሁታል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ግን ቤተ ክርስቲያን ማለት ስብስብ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ እናንተም እንደ ደቀ መዛሙርት አባል የሆናችሁበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡

"ቤተ ክርስቲያን" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሦስት የተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ውሏል፡-

  • ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ፣ የነበሩ እና ገናም የሚሆኑ ሰዎች ሁሉ አባል የሆኑበት ማለት ነው፡፡
  • የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ በዓለም ላይ በአንድ በተወሰነ ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ማለት ነው፡፡
  • የቤት ቤተ ክርስቲያን … የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ስብስብ ሲሆን፣ ከተሰብሳቢዎቹ በአንዳቸው ወይም ከአንድ በላይ በሆኑት መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚሰባሰቡ ናቸው፡፡

አንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ፡- በአካባቢያቸው የሚገናኙ፣ እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ሰዎችን የሚወዱ እና ደቀ መዛሙርትን የሚያደርጉ እና በመጨረሻውን ዘመን ቤተ ክርስቲያንን የሚያንጹ የኢየሱስ ተከታዮች ናቸው፤ እንዲህ ያለችው ተቋም የቤት ወይም ያልተወሳሰበች - ቀላል ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

እንዲህ ያሉት ያልተወሳሰቡ ወይም ቀላል ቤተ ክርስቲያኖች ታላቅ ነገር ለመሥራት ሲሰባሰቡ፣ የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያንን ይፈጥራሉ፡፡

እነዚህ ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት በክልል ሲተሳሰሩም የታሪክን እና የሥፍራን አድማስ ተሻግረው ዓለም አቀፍ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ያንጻሉ፡፡

ቀላል የቤት ቤተ ክርስቲያን ይህች ናት፡፡

**ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስ ኢየሱስን ማዕከል እና ንጉሣቸው ያደረጉ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ **

ቀላል - ያልተወሳሰቡ አብያተ ክርስቲያናት እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ሰዎችን የሚወዱ እና ደቀ መዛሙርትን የሚያፈሩ እና የሚባዙ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው፡፡አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ህንጻዎች፣ መርሃ - ግብሮች እና በጀቶች እንዲሁም ቅጥር ሠራተኞች አሏቸው፡፡ ነገር ግን፣ ቀለል ያሉ የቤት ቤተ ክርስቲያናት እግዚአብሔርን ለመውደድ፣ ሰዎችን ለመውደድ እና ራሳቸውን የሚያባዙ ደቀ መዛሙርትን ለማባዛት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውስጥ ምንም አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንኛውም ተጨማሪ ነገር ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ የሚያወሳስባት እና ለመባዛቷ እንቅፋት የሚሆን በመሆኑ፣ ሥልጠናችን ውስጥ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎች፣ እንደ ቤተ ክስቲያን መርሃ-ግብሮች እና እንደ በጀት እንዲሁም እንደ ቅጥር ሠራተኞች ያሉትን ጉዳዮች በመባዛት መርህ ለታነጹት ለከተማ እና ለክልል አብያተ ክርስቲያናት እንተዋቸዋለን፡፡

ልብ አድርጉ፣ "ዙሜ" ማለት "እርሾ" ማለት ነው፤ ይህም ቅንጣት የሆነ አንድ የሴል ሕዋስ ሲሆን፣ ራሱን ግን በፍጥነት የሚያባዛ ወይም የሚያራባ ነው፡፡

በዙሜ ሥልጠና እኛም ልክ እንደዚያ እርሾው ቀላል እና የምንባዛ እንሆናለን፡፡ ከመባዛታችን አስቀድመን ግን እግዚአብሔር እንዲባዛ የሚፈልግው ምን እንደሆነ ስለማወቃችን እርግጠኛ እንሁን፡፡ ምክንያቱም መባዛት መልካም ነገር ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ግን መልካም ላይሆን ይችላል፡፡የካንሠር ሕመም የብዜት ውጤት ነው፡፡ ሆኖም ግን ገዳይ ነው፡፡ስለዚህ ሞትን ሳይሆን ሕይወትን የምናባዛው እንዴት ነው? ደቀ መዛሙርትን ማባዛት የተገባን ወይም ለዚህ የበቃን ደቀ መዛሙርት መሆናችንንስ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ተወያዩ

(10 min)

  1. ስለ ቤተ ክርስቲያን ስታስቡ ወደ አእምሮአችሁ የሚመጣው ምንድን ነው?
  2. በዚያ ስዕል እና በቪዲዮው ላይ እንደ ‹‹ቀላል ቤተ ክርስቲያን›› በተገለጸው መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
  3. የትኛውን ማባዛት ቀላል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ እና ምክኒያታችሁስ?

READ

(5 min)

እግዚአብሔርን መስማትና መታዘዝ

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ከእግዚአብሔር ስለመስማት እና ለሰማነው ስለመታዘዝ እንማራለን፡፡ እስትንፋስ ሕይወት ነው፡፡ ዓየር ወደ ውስጥ እንስባለን፡፡ ወደ ውጪም እንተነፍሳለን፡፡ ሕይወት እንተነፍሳለን ማለት ነው፡ መተንፈስ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ያን ያክል በጣም አስፈላጊው ነገር ነው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን "እስትንፋስ" ብሎ ይጠራዋል፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከእግዚአብሔር ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በጸሎት ከእግዚአብሔር ስንሰማ እና ከእርሱ ጋር ስንነጋገርም እንዲሁ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በአካሉ፤ በቤተ ክርስቲያን ወይም በሌሎች የኢየሱስ ተከታዮች በኩልም የእግዚብሔርን ቃል ስንሰማ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በሥራዎቹ በኩል እርሱን ስንሰማ፤ ማለትም በሁነቶች፣ በልምዶች እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ልጆቹ በስደት እና በስቃይ ውስጥ እንዲያልፉ ሲፈቅድም፣ በዚያ ውስጥ እርሱን ስንሰማም፣ ዓየር ወደ ውስጥ ሳብን ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከእግዚአብሔር የሰማነውን ወደ ተግባር ስንለውጥም መተንፈሳችን ነው፤ ስንታዘዝም እንዲሁ ወደ ውጪ መተንፈሳችን ነው፡፡ ወደ ውጪ መተንፈስ መታዘዝ፣ ለመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ - መታዘዝ፡፡ ለመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ ማለት አስተሳሰባችንን፣ የአፋችንን ቃል እና ተግባራችንን በመለወጥ ከኢየሱስ እና ከፈቃዱ ጋር እንዲጣመር ማድረግ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በመታዘዝ ወደ ውጪ መተንፈስ ማለት ኢየሱስ ለእኛ ያካፈለውን፣ የሰጠንን በመስጠት እግዚአብሔር እኛን እንደባረከን ሌሎችም እንዲባረኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ለአንድ የኢየሱስ ተከታይ ይህ ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ እና ወደ ውጪ መተንፈስ አንገብጋቢ ጉደይ ነው፡፡ የሕይወቱም መሠረት ነው፡፡ "ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።" "እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።" ኢየሱስ እንዳለው የተናገረውን እና ያደረገውን እያንዳንዱን ነገር ለማከናወን መሠረት ያደረገው ከእግዚአብሔር በመስማት እና ያዳመጠውን ለመተግበር በመታዘዝ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ፡- እግዚአብሔርን ማዳመጥ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውጪ መተንፈስ፡- አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ለሰማው ነገር መታዘዝ እና የሰማውንም ለሌሎች ማካፈል ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው ተከታዮቹ በመንፈስ ቅዱስ - በእያንዳንዳችን እርሱን በምንከተው ሁሉ ላይ እፍ ባለው - በእስትንፋሱ ምክንያት ከእግዚአብሔርን እንሰማለን፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል::" ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ፡- እግዚአብሔርን ማዳመጥ ነው፡፡ ዓየርን ወደ ውጪ መተንፈስ፡- አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ለሰማው ነገር መታዘዝ እና የሰማውንም ለሌሎች ማካፈል ነው፡፡ ይህንን ሲል ኢየሱስ እንዴት መኖር እንዳለብን እያመላከተን ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምጽ የምንሰማው እንዴት ነው? የምንታዘዘውንስ ነገር የምናውቀው እንዴት ነው? ኢየሱስ "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" ብሏል፡፡ ተከታዮቹን ደግሞ "በጎቼ" ብሏቸዋል፡፡ ኢየሱስ እንዲህም ብሏል፡- በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፡፡ ኢየሱስ እንዳለውም የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ እግዚአብሔር የሚለውን ይሰማል፡፡ እናንተ የማትሰሙበት ምክንያት የእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታይ፣ ድምጹን ለመስማት ራሳችንን መስጠት - መቁረጥ አለብን፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው በጥሞና - ባለመናወጥ - በእርጋታ ሆነን ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው ኢየሱስ ላይ በማተኮር ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ የምንሰማው በሃሳባችን፣ በራዕያችን፣ በስሜታችን እና በምናባችን ነው፡፡ የእርሱን ድምጽ በትክክል የምንሰማው ስንጽፈው እና የሰማነውንም ስንመረምረው ነው፡፡ የሰማነው ሁሉ፣ ያሰብነው ሁሉ፣ በራዕያችን የታየን ሁሉ፣ የተሰማንም ሁሉ ወይ በምናባችን የተከሰተልን ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምጽ መሳይ የጠላት ድምጽም ይመጣል፡፡ ኢየሱስ እንዳለው ጠላታችን ውሸታም ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለውም ጠላታችን የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ከእርሱ እንደምንሰማ እና ሲናገርም እርሱ እንደሆነ እናውቃለን። በልምምድ እና በጸሎት የእርሱን ድምጽ እንደሚገባው ማወቅ እንችላለን፡፡ የምንሰማው ድምጽ ከእግዚአብሔር ይሁን ወይም ከሌላ መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት የምንሰማውን ድምጽ ለመመርመር የሚረዱ የተወሰኑ መንገዶች ናቸው፡- ኢየሱስ ሲናገር፣ ድምጹ ሁልጊዜም ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጣጣም መንገድ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ቀድሞ በነገረን መንገድ ነው፡፡ በድምጽ የምንሰማው ቃሉ ከተጻፈው ቃል ጋር በፍጹም አይጣረስም፤ አይምታታምም፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፣ ድምጹ ልባችንን በተስፋ እና በሰላም ይሞላዋል፡፡ ድምጹ በኩነኔ እና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ አይተወንም፡፡ ኢየሱስ ማንንም አይኮንንም፡፡ ከዚያ ይልቅ በፍቅር ያቀናናል፡፡ የኢየሱስ ድምጽ የሥጋን ሥራዎች፣ ወሲባዊ ኢ-ሥነምግባርን፣ የምንዝርናን፣ ቅድስና የለሽ ሃሳብን፣ ጣዖትን ማምለክን፣ ጥንቆላን፣ ጥላቻን እና ጸብን፣ ቅናት እና መራር ቁጣን፣ ራስ ወዳድነትን፣ አመጸኛ ተቃዋሚነትን፣ ክፍፍልን፣ ምቀኝነትን፣ ሥካርን እና ዘፋኝነትን በሰው ልብ ውስጥ አያነሳሳም፡፡ የእነዚህ ነገሮች ነገሮች መነሳሻ የእግዚአብሔር ድምጽ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፣ የኢየሱስ ድምጽ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬዎች ያፈራል፡፡ ፍቅርና ሃሴትን፣ ሰላምና ትዕግስትን፣ ርህራሄና ደግነትን፣ ታማኝነትን፣ ጨዋነትን እና ራስን መግዛትን ይሰጠናል፡፡ ኢየሱስ ሲናገር ድምጹ በጥርጥር ፋንታ መተማመንን ይሞላናል፡፡ በመጨረሻም፣ በውስጣችንም ከእግዚአብሔር የመስማትን ልምድ እና የድምጹን ሰላም እናውቃለን፡፡ ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ላንሰማ እንችላለን፡፡ ከድምጹ በመጨረሻ ማወቅ የሚገባንን የሚያሳውቀንን ያክል ብቻ ልንሰማ እንችላለን፡፡ የምንሰማው ግን ነገር ግን የጸና እና የማይቀለበስ ወይም የማይለወጥ ነው፡፡ ለኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ የምሥራቹ ይህ ነው፡- ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ውስጥ ዓየር ስንስብ፣ ዓየርን ወደ ውጪ ስንተነፍስ እና ለእግዚአብሔር በመታዘዝ የሰማነውን ለሌሎች ስናካፍል፣ እግዚአብሔር ከቀደመውም የበለጠ በግልጽ ይናገረናል፡፡ የእስትንፋሱን እፍታ ከቀደመውም በበለጠ በእኛ በኩል እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡ ድምጹንም የበለጠ ግልጽ በሆነ መንገድ እንሰማዋለን፡፡ የእርሱንም ድምጹ በሚገባ እናውቀዋለን፤ የሌላውን ድምጽ ግን አይደለም፡፡ ሥራውንም በዓለም ላይ እናየዋለን፤ ራሳችንንም በሥራው ተሳታፊ እናደርጋለን፡፡ ዓየር ወደ ውስጥ እንስባለን፡፡ ወደ ውጪም እንተነፍሳለን፡፡ ይህም ሕይወት ነው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማትና ማወቅ መማሩ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
  2. ከጌታን መስማት እና ምላሽ መስጠት በእርግጥ ልክ እንደመተንፈስ ነውን? ለምን ወይም ለምንስ አይሆንም?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

  • እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል
  • የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
  • መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።

NEXT STEP

ታዘዙ

እነዚህን ትርጓሜዎች ከጓደኛቻችሁ ጋር መጋራት ተለማመዱ እና ጌታ በልባችሁ እና በነፍሳችሁ ውስጥ እንዲሰርጽባችሁ ጸልዩ። ከማን ጋር እንድትካፈሉ እንደሚፈልግ ጌታን ጠይቁ።

አካፍሉ

ፍቺዎቹን እንድታደርጉ ጌታ ለሚያሳስባችሁ ማንኛውም ሰው አካፍሉ። ከዚያ ለሌላ ሰው ማካፈል እንዲችሉ አስታጥቁዋቸው።

ክፍለ ጊዜ 2

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 4568

ፀልዩ

(5 min)

በቡድኑ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ሰው በቡድኑ እንዲጸልይለት የሚፈልግበትን ልዩ ፍላጎቶች ያሉት እንደሆነ ጠይቁ።

የእግዚአብሔር ህዝቦች ሲጸልይ እንደሚሰማቸው እና እንደሚሰራ በቃሉ ተስፋን ስለሰጠን እግዚአብሔርን አመስግኑ።

ቆይታችሁን እንዲመራላችሁ የእግዚአብሔር ቅዱሱ መንፈስን ጠይቁ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

READ

(5 min)

S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

Zume ግብዓት ቅ.ም.ተ.ጸ.ማ.የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ኢየሱስ እንዲህ አለ -- ‹‹ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ 20ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤›› የኢየሱስ ተከታይ የሆነ እያንዳንዱ ሰው ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ የሚታዘዝ ከሆነ፣ ኢየሱስ ምን አንደሚያዝ ማወቅ ያስፈልገዋል። ታላቁ ትዕዛዝና ታላቁ ተልእኮ እግዚአብሔር የሚናገረን ነገር ታላቅ ማጠቃለያ ነው፣ ይሁንና የኢየሱስ ተከታይ እግዚአብሔር ወደፈጠረው ወደ ሙሉ መለኪያ የሚያድግ ከሆነ፣ የበለጠ ማወቅና መታዘዝ ያስፈልገዋል። ቅ.ም.ተ.ጸ.ማ የሚወክለው፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ምልከታ ትግበራ ጸሎት እና ማካፈል ነው ማንኛውም የጌታ ኢየሱስ ተከታይ ሊጠቀምበት የሚችለውን ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ ለመማርና ለማስታወስ ቀላል መንገድ ነው። እስቲ እያንዳንዱን ክፍል ትንሽ ተጨማሪ እንመልከት። መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ ወይም ስትሰሙ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት፦ ዛሬ ላይ በተለይም ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቅሶችን ፃፉ። ምልከታ፦ ትርጉሙን በተሻለ ለመገንዘብ እንዲረዳችሁ እነዚያን ጥቅሶች ወይም ቁልፍ ሀሳቦች በራሳችሁ ቃላት ጻፉ። ትግበራ፦ እነዚህን ትዕዛዛት ወይም ጽንሰ ሀሳቦች በራሳችሁ ህይወት ውስጥ መታዘዝ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ። የተለየ ምን ማድረግ ይኖርባችኃል? እነዚህን ፃፏቸው። ጸሎት፦ በቃሉ ውስጥ እያነበባችሁት ያለውን እና ትዕዛዙን ስለማክበርና የተማራችሁት በስራ ላይ ስለማስገባት የተረዳችሁን ነገር ለእግዚአብሔር የሚናገር ጸሎትን ጻፉ። ማካፈል፦ ስለተማራችሁት ነገር እና እንዴት እየተጠቀማችሁበት እንዳለ ለማን እንድትካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት። ስለዚህ እስቲ ቅ.ም.ተ.ጸ.ማየሚለውን ወደተግባር እናምጣው፦ ቅዱሳት መጻሕፍት፦ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‹‹ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና›› ይላል እግዚአብሔር። ‹‹ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።›› ኢሳ 55÷8-9 ምልከታ - ሰው ስለሆንኩ፣ የማውቀው ነገር እና የማደርገውን የማውቀው ላይ ውስን ነኝ። እግዚአብሔር ግን በምንም መንገድ አይገደብም። ሁሉንም ነገር ያያል እንዲሁም ያውቃል። ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል። ትግበራ - እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅና መንገዶቹ መልካም ስለሆኑ፣ በነገሮች መንገድ ከመታመን ይልቅ እሱን ከተከተልኩኝ በህይወቴ ውስጥ የበለጠ ስኬት አገኛለሁ። ጸሎት - ጌታ ሆይ፣ አንተን የሚያስደስትህን እና ሌሎችን የሚረዳ መልካም ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አላውቅም። መንገዶቼ ወደ ስህተቶች ያመራሉ። ሀሳቦቼ ወደ ጉዳት ይመራሉ። ይልቁኑም እባክህ መንገዶችህን እና ሃሳቦችህን አስተምረኝ። አንተን ስከተልህ መንፈስ ቅዱስህ እንዲመራኝ ፍቀድ። ማካፈል - እነዚህን ጥቅሶች እና ይህንን ትግበራ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እያለፈ እና ለሚገጥሙት አስፈላጊ ውሳኔዎች አቅጣጫ ለሚያስፈልገው ጓደኛዬ ስቲቭ አካፍላለሁ። S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት። በZume ግብዓት ውስጥ ካሉ ቀላል መሳሪያዎች አንዱ።

ልምምድ

(30 min)

SOAPS የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የQR ኮድን ቃኙ።

ማቴዎስ 6፥9-13 ላይ ያለውን ክፍል ተጠቅማችሁ በSOAPS የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ በግል ስሩ። (20 ደቂቃ)

ሁላችም ተመለሱና የየራሳችሁን S.O.A.P.S. በሁለት ወይም በሦስት ቡድን አካፍሉ። (10 ደቂቃ)

ቅዱሳት መጻሕፍት

ለእናንተ ልዩ ትርጉም ያላቸውን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቅሶችን ዛሬ ፃፉ።

ምልከታ

እነዚያን ጥቅሶች ወይም ቁልፍ ነጥቦች በተሻለ ለመረዳት በራሳችሁ አገላለፅ እንደገና ጻፏቸው።

ትግበራ

እነዚህን ትእዛዛት በህይወታችሁ መታዘዝ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ።

ጸሎት

ስለምን እንደተማራችሁ እና ለመታዘዝ ያቀዳችሁትን ለእግዚአብሔር የሚናገር ጸሎት ጻፉ።

ማካፈል

ስለተማራችሁት/ ስለተገበራችሁት ነገር ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት።

በትግበራ ያለ የ SOAPS ምሳሌ እነሆ፦

S - ‹‹ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና" ይላል እግዚአብሔር። ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።›› ኢሳ 55፥8-9

O - ሰው ስለሆንኩኝ፣ የማውቀው እና የማደርገውን የማውቀው ነገር ላይ ውስን ነኝ። እግዚአብሔር ግን ምንም ገደብ የለውም። ሁሉንም ነገር ያያል እና ያውቃል። ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል።

A - እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅ እና መንገዶቹ ምርጥ ስለሆኑ፣ በራሴ ነገሮች ከመታመን ይልቅ እሱን ብከተል ህይወቴ በበለጠ ስኬት ይሞላል።

P - ጌታ ሆይ፣ አንተን የሚያስደስትህን እና ሌሎችን የሚያግዝ ጥሩ ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አላውቅም። መንገዶቼ ወደ ስህተቶች ያመራሉ። ሀሳቦቼ ወደ ጉዳት ይመራሉ። ይልቁኑም እባክህ መንገዶችህን እና ሃሳቦችህን አስተምረኝ። አንተን እየተከተልኩህ እያለቅዱስ መንፈስህ ይምራኝ።

S - እነዚህን ጥቅሶች እና መተግበሪያውን ስቲቭ ከተባለ ጓደኛዬ ጋር እጋራለሁ፣ ጓደኛዬ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እያለፈ ስለሆነ ለሚወስናቸው አስፈላጊ ውሳኔዎች አቅጣጫ ያስፈልገዋል።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

NEXT STEP

ታዘዙ

SOAPSን መለማመድ ጀምሩ። አሁን እና በሚቀጥለው ስብሰባችሁ መካከል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጊዜ ይኑራችሁ። በማቴዎስ 5-7 ላይ አተኩሩ፣ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ አንብቡት። የSOAPS ቅርጸት በመጠቀም ዕለታዊ ማስታወሻ ይኑራችሁ።

አካፍሉ

ቢያንስ አምስት የምታውቋቸውን አማኞች የራሳቸውን S.O.A.P.S. መጀመር እንዲችሉ ጌታ እንዲመራችሁ ጠይቁ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በየቀኑ ይለማመዱ እና ከዚያ ያድርጉት።

ክፍለ ጊዜ 3

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 8767

ፀልዩ

(5 min)

በሕይወታችን ስላለው ነገር ጸልዩ እና እግዚአብሔር አመስግኑት። በቡድኑ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚሰማበት ጆሮ እንዲኖረው እና የሚናገረውን እንዲታዘዝ ፀልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የተጠያቂነት ቡድኖች

READ

(5 min)

የተጠያቂነት ቡድኖች

በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የተጠያቂነት ቡድኖች ኢየሱስም እንዲህ ብሏል፡- "…ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።" ኢየሱስ ተጠያቂነትን በተመለከተ ብዙ ታሪኮችን አካፍሏል በዚህም ስለምናደርገው እና ስለምንናገረው ነገር ተጠያቂ የመሆናችንንም እውነት በብዙ መንገድ አስታውቆናል። ኢየሱስ አሁንም እነዚህን ነገሮች ይነግረናል፤ ይኽም ለኋለኛው ጊዜ ዝግጁ እንድንሆን ነው። አንድ ቀን እኛ በእርሱ እንጠየቃለን፤ ስለዚህም አንዳችን በአንዳችን የመጠየቅን ልምምድ ከአሁኑ መለማመዳችን መልካም ነው። የተጠያቂነት ቡድኖች የሚመሠረቱት ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ነው፤ ይኸውም የሚቧደኑት ወንዶች ከወንዶች ጋር፣ ሴቶችም ከሴቶች ጋር ነው ማለት ነው። ቡድኖቹ በሳምንት አንድ ጊዜ እየተገናኙ ነገሮች በትክክል እየተከወኑ መሆናቸውን ለመረዳት፣ እንዲሁም ማስተካከያ ስለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንዲረዱ በተዘጋጁ ጥያቄዎች ላይ ውይይት እና ምክክር ያደርጋሉ። የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ተጠያቂ ነው፤ ስለዚህም ተጠያቂነትን ከሌሎች ተከታዮች ጋር መለማመድ ይገባዋል። የተጠያቂነት ቡድኖች፣ ሌላው በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት ውስጥ የሚገኝ ቀለል ያለ መሣሪያ ነው።

ልምምድ

(20 min)

የተጠያቂነት ቡድኖች

የQR ኮድን ቃኙ።

ተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በቡድን መድቡ።

ቀጣዮቹን 20 ደቂቃዎች በተጠያቂነት ጥያቄዎች በኩል አብራችሁ በመስራት አሳልፉ።

  1. እግዚአብሔርን እንዴት ሲሰራ አያችሁት?
  2. በዚህ ሳምንት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅነት በቃላቶቻችሁ እና በድርጅታችሁ ምስክር ሆናችኋልን?
  3. ለፆታዊ ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች ተጋልጣችኋል ወይንስ አእምሮአችሁ ባልተቀደሱ የጾታዊ አስተሳሰቦችን እንዲያዝናና ፈቅዳችኋል?
  4. በገንዘብ አጠቃቀማችሁ የእግዚአብሔርን ባለቤትነት እውቅና ሰጥታችኋል?
  5. የሆነ ነገር ከልብ ተመኝታችኋል?
  6. በቃላቶቻችሁ የአንድን ሰው ዝና ወይም ስሜት ጎድታችኋል?
  7. በቃልም ሆነ በተግባር ሐቀኝነት የጎደላችሁ ናችሁ ወይም ግብዝ ናችሁ?
  8. ሱስ የሚያስይዝ (ወይም ስንፍና ወይም ስነስርዓት የሌለው) ባህሪ ውስጥ ገብታችኋል?
  9. ለአልባስ፣ ለጓደኞች፣ ለስራ ወይም ለይዞታዎች ባሪያ ሆናችኋል?
  10. አንድን ሰው ይቅር ማለት ተስኗችኋል?
  11. እያጋጠሟችሁ ያሉ ስጋቶች ወይም ጭንቀቶች ምንድናቸው?
  12. አማራችኋል ወይም አጉረምርማችኃል?
  13. አመስጋኝ ልብን ይዛችሁ ቆይታችኋል?
  14. በወሳኝ ግንኙነቶቻችሁ ውስጥ አክባሪ፣ አስተዋይ እና ለጋስ ነበራችሁ?
  15. በሐሳባችሁ፣ በቃላችሁ ወይም በድርጊታችሁ ላይ ምን መሰናክሎች አጋጠማችሁ እና ምን ምላሽስ ሰጣችሁ?
  16. ሌሎችን፣ በተለይም አማኞችን ለማገልገል ወይም ለመባረክ የነበሯችሁን እድሎችን እንዴት ተጠቀማችሁ?
  17. ለጸሎት ልዩ መልስ አይታችኋል?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • የተጠያቂነት ቡድኖች

NEXT STEP

ታዘዙ

የተጠያቂነት አጋር (ተመሳሳይ ጾታ) አግኙ እና በየሳምንቱ ከእነሱ ጋር መገናኘት ጀምሩ።

አካፍሉ

ቢያንስ አምስት የምታውቋቸውን አማኞች የየራሳቸውን የተጠያቂነት ቡድን ስብሰባ እንዲጀምሩና ከዚያ እንዲያደርጉ እንድታበረታቱ ጌታ እንዲመራችሁ ጠይቁ።

ክፍለ ጊዜ 4

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 6787

ፀልዩ

(5 min)

እንደ ኢየሱስ ስላደረገን ነገር ጸልዩ እና አመስግኑት። የጋራ ቆይታችሁን እንዲመራላችሁ መንፈስ ቅዱስን ጋብዙ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ, ይህንን ጽንሰ-ሐሳብ እንሰማለን እና እንነጋገራለን-

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
  • ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር

READ

(5 min)

ተጠቃሚ ሳይሆን አምራች

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የኢየሱስ ተከታይ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከተራ ተጠቃሚነት ወጥቶ ወደ አምራችነት ሊለወጥ ወደሚችልበት መንገድ እንዲገባ እንዴት እንደምንረዳው እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነውን እቅዱን ሲያወጣ፣ አምራችነትን እና ተጠቃሚነትን አመጣጥነን፣ ለመፍጠር እና ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ባዶ ሆኖ መሞላት እና እንደገና የተሞላነውን ፈሰስ የማድረግን ሕይወት እንድንኖር አድርጎ ነው የሠራን፡፡ ነገር ግን በዚህ በወደቀችው ዓለማችን፣ ሰዎች የእግዚአብሔርን እቅድ በአመጽ ገፍተው ጥለዋል፤ ብዙዎቹም የእግዚአብሔርን ፍጹም እቅድ ሳይሆን ቁንጽል ሕይወት ለመኖር ኃይላቸውን ያጠፋሉ፡፡ ይማራሉ፤ ግን የተማሩትን ለሌሎች አያካፍሉም፡፡ ይሞላሉ፤ ነገር ግን ለሌሎች ፈሰስ አያደርጉም፡፡ ተጠቃሚ ናቸው፤ ነገር ግን አያመርቱም፡፡ የሚባዙ ደቀ መዛሙርትን ማድረግ የምንፈልግ ከሆነ፣ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን እንዴት አምራች እንደሚሆኑም ከእነርሱ ጋር መከፋፈል አለብን፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? ለሚለው፣ እግዚአብሔር እኛን በመንፈሳዊነት ለማሳደግ የተጻፈ ቃሉን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቀማል፡፡ እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ለመታጠቅ መማር፣ ቃሉን በአግባቡ መተርጎም እና በተግባር ማዋል አለበት፡፡ በሺህ በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ፣ በብዙ ጸሐፊዎች አማካኝነት እግዚአብሔር ቃሉን ለታመኑቱ፣ ሰምተው ለሚቀበሉት እና የሰሙትንም ለሌሎች ለሚያስተላልፉ ሰዎች ተናግሯል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔርን ታሪክ፣ እቅዱን፣ የልቡን ሃሳብና መንገዱን ይነግሩናል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍለ-ጊዜ ስለሁለት ቀላል መሣሪያዎች ተምረናል፤ እነዚህም መ.መ.ማ.ጸ.ማ. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የተጠያቂነት ቡድኖች ናቸው፡፡ በቀጣዩ ክፍለ-ጊዜም ስለአንድ ተጨማሪ ቀላል መሣሪያ ትማራላችሁ፤ ይህም የ3 - 3 ቡድኖች ነው፡፡ እነዚህ ሦስት መሣሪዎች በጋራ አዳዲስ ተከታዮች የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማሩ፣ እንዲተረጉሙ እና በተግባር ላይ እንዲያውሉ ለመርዳት በቅንጅት የሚሠሩ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሚዎች ብቻ ሳይሆኑ አድራጊዎች፣ እንዲሁም አካፋዮች እንዲሆኑም ጭምር ይማራሉ፡፡ እግዚአብሔርም የተጻፈውን ቃል ለመንፈሳዊ እድገታችን እንዲሆን ይጠቀምበታል፡፡ ይህም እኛ በጸሎት የምንለየው ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን መስማት እና ለእግዚአብሔር መናገር ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን በቅርበት እንድናውቀው፣ የልቡን ሃሳብ፣ ፈቃድ እና መንገዶቹን እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ ጸሎት ሌሎችን ለማገልገል እና ለመርዳት ያግዘናል፤ ግለሰቦችን በግል እንዲሁም ሰዎች እንደ ቡድን በተወሰኑ መንገዶች እንድንረዳቸው እና እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ እንዲያውቁ እንድናስተምራቸውም ይደግፈናል፡፡ ሁለት ቀላል መሣሪያዎች፤ የጉዞ ጸሎት እና የጸሎት ዑደት፡- ሰዎች በግላቸው የግል ጸሎትን ሕይወት እንዲያሳድጉ እና ሌሎችን በሚያገለግሉበት መንገድ መጸለይን እንዲማሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች ያለማቋረጥ የመጸለይን ልማድ እንዲያዳብሩ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ዓለምንም በዓይን በሚታየው እና በጆሮ በሚሰማው ብቻ ከመመዘን ይልቅ ከመንፈሳዊው ዓለም አንጻር መመልከትን እንዲማሩ ያደርጋሉ፡፡ በዘላቂነት ጥቅም ላይ ሲውሉም የኢየሱስን ተከታዮች የመጸለይን ብቃት እንዲጨምሩ ያደርጋሉ፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር የመስማትን ችሎታ እንዲጨምሩና የሰሙትንም ለሌሎች እንዲያካፍሉ ያደርጋሉ፡፡ እግዚአብሔር የክርስቶስን አካል፤ አማኞችን - "ቤተ ክርስቲያን" ብለን የምንጠራትን፣ እኛን በመንፈሳዊነት ለማሳደግ ይጠቀምበታል፡፡ እንደ አማኞች ስብስብ፣ አንዳችን ከአንዳችን ጋር የታሳሰርን ነን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው በኢየሱስ የሆንን እኛ ብዙ የአካል ክፍሎች ብንሆንም አንድ አካል ነን፤ አንዳችን የአንዳችን ነን፡፡ በሌላ አባባል፣ ትሥሥራችን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ አይደለም አንዳችን ከአንዳችን ጋርም የተሣሠርን ነን፡፡ እግዚአብሔር የሚነግረን አንዳችን ለአንዳችን ራሳችንን እንድንሰጥ እና አንዳችን አንዳችንን እንድናገለግል ነው፡፡ እያንዳንዳችን የተለያየ ዓይነት ጥንካሬ እና ደካማ ጎን አለን፡፡ እግዚአብሔርም በጠንካራ ጎናችን ድካም ያለባቸውን ሰዎች እንድንደግፍ ከእኛ ይጠብቀዋል፡፡ በደካማ ጎናችንም ደግሞ እርሱ የሰጣቸውን ብርታት ተጠቅመው ለሚደግፉን ለሌሎች ሰዎች ፈቃደኛ መሆናችንንም ከእኛ ይጠብቃል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ሰጥቷል፤ ስጦታዎቻችን አንዳችን አንዳችንን ለመደገፍ ማዋላቸውን ማረጋገጥ ይገባናል፤ የእያንዳንዳችን ስጦታዎች ወደ ሌላችን በመተላለፋቸው ውስጥ ዘርፈ-ብዙ የእግዚአብሔር በረከቶች መተላለፋቸውን ተረዱ፡፡ እንደ 3 - 3ኛዎቹ እና እንደተጠያቂነት ቡድኖች ያሉ ቀላል መሣሪያዎች፣ እንዲሁም አቻ አሳዳጊ የአማካሪ ቡድኖች አንዳችን ለአንዳችን እንድንረዳዳ፣ ሌሎችን እንድንወድድ እና በጎ ሥራዎችን እንድንሠራ የሚያበረታቱን እግዚአብሔር እንድናደርግ ያዘዘንን እንድንታዘዝ በማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ የተማርነውን ለሌሎች የምናካፍልበትን መንገድ እንድናገኝም ድጋፍ ያደርጉልናል፡፡ ስለኢየሱስ የሚደርስብንን ስደትና ስቃያችንን - መስዋዕትነት እና መጥፋታችንንም እግዚአብሔር እኛን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማሳደግ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ኢየሱስን በመውደዳችን እና በመታዘዛችን ምክንያት ሰዎች ጫና ሲያደርጉብን እና ጉዳት ሲያደርሱብን፣ ወይም ኢየሱስን እየወደድን እና እየታዘዝንም እንኳን ስደትና መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን ሲከሰቱ፣ እግዚአብሔር ስቃዮቻችንን ባሕርያችንን ለማጥራት እና የበለጠ የክርስቶስን መልክ እንድንይዝ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል፡፡ እርሱ ባሕርያችንን ያበለጽጋል፡፡ ያበረታናል፡፡ እንዲሁም እምነታችንን ያጠራል፡፡ አገልግሎታችንም ብቁ ያደርገዋል፡፡ ከዚያም በተለየ መንገድ በሕይወት ስቃይ እያዩ ያሉትንም እንድናገለግል ያደርገናል፡፡ ሁሉንም ሲያደርግ በሚያውቁን እና ሕመማችንን በሚረዱ ሰዎች ሁሉ ፊት ራሱን የበለጠ በመግለጥ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታዮች መሰደድ ሊያጋጥመን እንደሚችል እግዚአብሔር ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።" እንደ 3 - 3ኛ ቡድኖች እና እንደተጠሪነት ቡድኖች ያሉት ቀላል መሣሪያዎች የእግዚአብሔር ተከታዮች ስለገጠማቸው ስደትና ስቃይ ለሌሎች የሚያካፍሉበትን እድል ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህ ቡድኖች የኢየሱስን ተከታዮች የእግዚአብሔር ቃል ከባድ ጊዜዎች እንደሚያጋጥሟቸው እና እንዲህም ባሉ ሁኔታዎች ምንም እንኳን ነገሮች በተበላሸ ገጽታ ቢከሰቱም፣ ቃሉ ላይ ተደግፈው እንዴት ማለፍ እንደሚገባቸው ለማስተማር እድል ይሰጧችኋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ጸሎት፤ የአካል ሕይወት፤ ስደት እና ስቃይ፡፡ እነዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ፍጹም ወደ ሆነው ወደ ልጁ፣ ወደ ኢየሱስ መልክ እኛን የሚያሳድግባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቀላል መንገዶች እግዚአብሔር ከሚሰጠን መልካም ነገሮች ተጠቃሚዎች ብቻ እንዳንሆን፣ ነገር ግን አዘጋጆች እና አካፋዮች እንድንሆንም ይረዱናል፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ከላይ ከተዘረዘሩት አራት ዘርፎች (ጸሎት፣ የእግዚአብሔር ቃል፣ ወዘተ.) ውስጥ የትኞቹን አስቀድማችሁ እየተለማመዳችሁ?
  2. ስለ የትኞቹ ነው እርግጠኛ የማይሰማችሁ?
  3. ሌሎችን በማሰልጠን ረገድ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል?

READ

(5 min)

የ100 ዝርዝር

በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የ100 ሰዎች ስም ዝርዝር ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "እንግዲህ ሂዱና … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" ተከታዮቹም ያደረጉት ያላቸውን ነው። ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል። ወደ ጓደኞቻቸው ሄደዋል። በከተማቸው ወደሚያውቋቸውም ሰዎች ሄደዋል። አብረዋቸው ወደሚሰሩም ሰዎች ሄደዋል። ኢየሱስ "ሂዱ…" ነበር ያለው፤ እነርሱም እንዳላቸው በመሄድ ታዘዙ። የእግዚአብሔርም ቤተሰብ አደገ። እግዚአብሔር "እንድንሄድ እና ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ" የሚያስፈልገንን የግንኙነት መስመር ዘርግቶልናል። እነዚህም ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ጎረቤቶቻችን፣ አብረናቸው የምንሠራ እና የክፍል ጓደኞቻችን - በአጠቃላይ በሕይወታችን የምናውቃቸው እና ያገኘናቸው ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር በሕይወታችን ላስቀመጣቸው ለእነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ታማኝ በመሆን ደቀ መዛሙርትን በማፍራት ረገድ የመጀመሪያው ትልቅ ርምጃ ነው። ይህም ስም ዝርዝራቸውን ከመያዝ ቀላል ደረጃ ሊጀመር የሚችል ነው። የመቶ ሰዎች ስም ዝርዝር በዙሜ የመረጃ ቋት ውስጥ ካሉ ደቀ መዛሙርትን የማፍሪያ ቀላል መሣሪያዎች አንዱ ነው።

ልምምድ

(30 min)

የራስዎን የ100 ዝርዝር ይፍጠሩ

የQR ኮድ ይቃኙ ወይም አንድ ወረቀት ይጠቀሙ።

በቡድናችሁ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሰዎች የራሳቸውን የዝምድናዎች ዝርዝር ሞልተው ለማጠናቀቅ እንዲችሉ ቀጣዮቹን 30 ደቂቃዎች እንዲኖራቸው አድርጉ። የምትችሉትን ያህል ዘርዝሩ።

በመቀጠልም ከእግዚአብሔር ጋር ስላላቸው ዝምድና ያላችሁን የተሻለ ግንዛቤ እንደሚከተሉት ምልክት ያድርጉ፦ ደቀ መዝሙር፣ የማያምን ወይም የማይታወቅ።

የዝምድናዎቻችሁን ዝርዝር ይሥሩ፤ በተጽዕኖ ክበባችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጻፉ። እያንዳንዱ ሰው ደቀ መዝሙር እንደሆነ፣ የማያምን እንደሆነ፣ ወይም የማይታወቅ እንደሆነ ምልክት ያድርጉ።

በቡድን ሆናችሁ እያንዳንዳችሁ የራሳችሁን ዝርዝር ለመሥራት ጊዜ ውሰዱ። ወረቀት ወይም በስልጠና ቁሳቁሶቻችሁ ውስጥ ያሉትን ዲጂታል መገልገያዎች መጠቀም ትችላላችሁ።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው ሀሳብ፡-

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • የሸማች የአኗኗር ዘይቤ ከአምራች የአኗኗር ዘይቤ የንፅፅር አቀማመጥ
  • ተዛማጅ ባለአደራነት - የ100 ዝርዝር

NEXT STEP

ታዘዙ

በዚህ ሳምንት “የማያምን” ወይም “የማይታወቅ” ተብሎ ምልክት ካደረጋችሁባቸው 100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ለአምስት ሰዎች በመጸለይ ጊዜ አሳልፉ። ለታሪኩ ፍላጎት ያላቸው ዝግጁ እንዲሆኑ ልባቸውን እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔርን ለምኑት።

አካፍሉ

የ100 መገልገያዎችን ዝርዝር ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ እና ከቀጣዩ ክፍለ ጊዜ በፊት አግኙት።

ክፍለ ጊዜ 5

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 3450

ፀልዩ

(5 min)

በሕይወታችን ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ስላው ፍቅሩ ጸልዩ እና እግዚአብሔርን አመስግኑት። በቡድኑ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች እግዚአብሔር በሚያያቸው መንገድ እንዲያይ ጸልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል

READ

(5 min)

የጸሎት ዑደት

በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የጸሎት ዑደት ኢየሱስ ለተከታዮቹ ስለጸሎት ዓላማ፣ ትግበራ እና ስለተስፋ ቃሎቹ አስተምሯቸዋል። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።" ኢየሱስ ያስተማረው፣ ጸሎት ለሰዎች ለአደባባይ ታይታ-ክብር ማግኛ፣ ራስ-ተኮር የምኞት ዝርዝር ወይም ረብ-አልባ ንግግርን መደጋገም አለመሆኑን ነው። ኢየሱስ ያስተማረን ጸሎት ከሚወደን የሰማዩ አባታችን ጋር ቀጣይነት እና ቀጥተኛ ንግግር ማድረግ በመሆኑ በውስጡ ኃይል ያለው ነገር ነው። ልክ እንደማንኛውም መልካም ንግግር፣ መልካም ጸሎት ማለት በተናጋሪዎቹ መካከል መደማመጥ እና ንግግር ያለበት ነው። ዓለማትን ከፈጠረው ሕያው እግዚአብሔር ጋር መነጋገር ግን አስፈሪ ሊመስል ይችላል። ከመንፈሳዊው ዓለም በትክክል መስማት በእርግጥም ለብዙ ሰዎች ፍጹም አስፈሪ ክስተት ነው። መልካሙ ዜና ግን ይህ ነው፡- በጸሎት በርትተን ከወዳጃችን ከእግዚአብሔር ጋር በተሻለ ሁኔታ ጥልቅ ንግግር ማድረግ የሚቻል ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርም በትክክል የሚፈልገው ይህንን መሆኑ ነው። ነገር ግን ጸሎት ልክ አዲስ ቋንቋን እንደመልመድ ሲሆን፣ ጸሎታችሁን የምታሻሽሉት እንዴት ነው? መልሱ ቀላል ነው፤ ትለማመዳላችሁ። የጸሎት ዑደት ጸሎትን መለማመጃ እና እናንተ በራሳችሁ መጠቀም የምትችሉት እና ለማንኛውም የኢየሱስ ተከታይ ልታስተላልፉት የምትችሉት ቀላል መሣሪያ ነው። እያንዳንዱ 5 ደቂቃዎችን በሚወስዱ በ12 ቀላል ደረጃዎች፣ የጸሎት ዑደት አሥራ ሁለት ወደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ወደሚያስተምራቸው መንገዶች ይመራችኋል በመጨረሻም፣ አንድ ሰዓት የምትጸልዩበት መንገድ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል፡- "ሳታቋርጡ ጸልዩ።" ይህንን ማድረግ መቻላችንን ሁላችንም መናገር አንችልም። በዚህ መልኩ አንድ ሰዓት ከጸለይን በኋላ፣ አንድ ደረጃ ትቀርባላችሁ። የጸሎት ዑደት በዙሜ ቋት ከሚገኙት መካከል አንዱ ተጨማሪ መሣሪያ ነው።

ልምምድ

(60 min)

የጸሎት ዑደት

ቡድኑ የሚመለስበትና እንደገና የሚገናኝበት ጊዜ አመቻቹ። ሁሉም ሰው ለመጸለይ ጸጥ ያለ ቦታ እንዲያገኝና ወደ ቡድኑ እንዲመለስ ጥቂት ተጨማሪ ደቂቃዎችን ማካተታችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

ጊዜያችሁ ነፃ ከሆነ፣ ሙሉውን ሰዓት ውሰዱ። እያንዳንዱን ክፍል ለ5 ሙሉ ደቂቃዎች ይጸልዩ። ይህም ይህን ክፍለ ጊዜ ከአንድ ሰአት በላይ ስልጠና ያደርገዋል።

ረዘም ያለ ክፍለ ጊዜ መውሰድ ካልቻላችሁ፣ እያንዳንዳቸው የጸሎት ክፍሎችን ከ5 ደቂቃዎች ወደ 3 ደቂቃዎች ቀንሱ።

እያንዳንዳቸው 5 ደቂቃ በሚፈጁ በ12 ቀላል እርምጃዎች - መጽሐፍ ቅዱስ እንድንጸልይ በሚያስተምረን 12 መንገዶች ይህ የጸሎት ዑደት ይመራችኋል። በመጨረሻም፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ትጸልያላችሁ።

prayer cycle

አመስግኑ የጸሎት ጊዜያችሁን ጌታን በማመስገን ጀምሩ። በሃሳባችሁ ለሚመጡት ነገሮች አመስግኑት። ባለፈው ሳምንት በህይወታችሁ ስላደረገው አንድ ልዩ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑት። ለቤተሰባችሁ ስላደረገው በጎነት አመስግኑት።

ጠብቁ ጌታን በመጠባበቅ ጊዜያችሁን አሳልፉ። በዝምታ ላይ ሃሳቡን እንዲነግራችሁ ፍቀዱለት።

ተናዘዙ እርስን የማያስደስት በህይወታችሁ ያለ ማንኛውንም ነገር እንዲያሳያችሁ መንፈስ ቅዱስን ለምኑት። የተሳሳቱ ዘንባሌዎቻችሁን እንዲጠቁማችሁ ጠይቁት፣ ከዚያም የንስሃ ጸሎት ያላደረጋችሁባቸው የተወሰኑ ድርጊቶችን እንዲገልጽላችሁ ጠይቁት። ከሃጢያታችሁ አሁን ለጌታ ተናዘዙ።

ቃሉን አንብቡ በመዝሙር፣ በነቢያት ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ባሉት ስለ ጸሎት የሚናገሩ ምንባቦችን የምታነቡበትን ጊዜ አሳልፉ።

ጠይቁ። እራሳችሁን ወክላችሁ

ምልጃ ሌሎችን ወክላችሁ ጠይቁ።

ቃሉን ጸልዩ ልዩ ምንባቦችን ጸልዩ። ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት ያደረጉ ጸሎቶችም ሆኑ ብዙ መዝሙሮች ለዚህ አላማ የሚጠቅሙ ናቸው።

አክብሩት በህይወታችሁ ውስጥ ስላሉት ነገሮች፣ በቤተሰባችሁ እና ቤተክርስቲያናችሁ ስም ጌታን አክብሩት።

ዘምሩ የምስጋና ወይም የአምልኮ ወይም ሌላ ዜማ ወይም መንፈሳዊ መዝሙር ዘምሩ።

አሰላስሉ ጌታ እንዲያናግራችሁ ለምኑት። የሚሰጣችሁን ስሜት ለመጻፍ እስክሪብቶ እና ወረቀት አዘጋጁ።

አዳምጡ ያነበባችሁትን፣ የጸለያችኋቸውን እና የዘመራችኋቸውን ነገሮች በማቀናጀት ጊዜ አሳልፉ፤ ጌታ እናንተን ለማናገር እንዴት ሁሉንም እንዳጣመራቸው ተመልከቱ።

አመስግኑት ከእርሱ ጋር ስላሳለፋችሁት ጊዜ እና እሱ ለሰጣችሁ ግንዛቤዎች ጌታን አመስግኑት ። ስለ ክቡር ባህሪያቱ አመስግኑት።

የDick Eastman መፅሃፍ The Hour that Changes the World (C) 2002 በ Dick Eastman ፣ Chosen Books፣ Grand Rapids፣ MI፣ በፍቃድ ጥቅም ላይ የዋለ።

ተወያዩ

(10 min)

  1. በጸሎት አንድ ሰአት ስለ ማሳለፍ ምን ምላሽ አላችሁ?
  2. ምን ተሰማችሁ?
  3. የተማራችሁት ወይም የሰማችሁት ነገር አለ?
  4. እንዲህ መሰሉን ጸሎት የዘወትር ልማድ ብታደርጉት ኖሮ ሕይወት ምን ትመስል ነበር?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • እንዴት አንድ ሰዓት በጸሎት ውስጥ ማሳለፍ እንደሚቻል

NEXT STEP

ታዘዙ

በዚህ ሳምንት ውስጥ ለአንድ ሰዓት ያህል ስትጸልዩ እንዲመራችሁ የጸሎት ዑደቱን ተጠቀሙ።

አካፍሉ

የጸሎት ዑደቱን ጌታ ለሚመራችሁ ማንኛውም ሰው አካፍሉ። ለሌሎችም እንዲያካፍል አነሳሱት።

ክፍለ ጊዜ 6

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 2344

ፀልዩ

(5 min)

ጸልዩ እና በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ህልውናውን ስለተለማመዳችሁባቸው መንገዶች እግዚአብሔርን አመስግኑ እና የአብሮ ጊዜያችሁን እንዲመራ መንፈስ ቅዱስን ጋብዙት።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

  • መንፈሳዊ ኢኮኖሚ
  • ታላቁን በረከት መልቀቅ
  • ወንጌል እና ወንጌልን እንዴት ማካፈል እንደሚቻል

READ

(5 min)

መንፈሳዊ ኢኮኖሚ

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ስለ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ምጣኔ ሐብት እንነጋገራለን፡፡ በዚህች የወደቀ ሥርዓት ባለባት ዓለም ውስጥ ሰዎች ሲወስዱ፣ ሲቀበሉ እና በዙሪያቸው ካሉት ይልቅ የበለጠ ሲያገኙ እንደተሸለሙ ይቆጥሩታል፡፡ እግዚአብሔር በቅዱሱ መጽሐፉ ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፡- "አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ …" እግዚአብሔር ግን በመንግሥቱ ምጣኔ ሃብታዊ አሳቡ ሽልማታችን የሆነውን የሚያመላክተን እኛ በምናገኘው ነገር ሳይሆን፣ በልግስና በምንሰጠው መሆኑን ነው፡፡ ይህንንም እንዲህ በማለት ገልጧል፡- እኔ አድናችኋለሁ፤ እናንተም ለሌሎች በረከት ትሆናላችሁ፡፡ ኢየሱስም ያለው እንዲሁ ነው፡- "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነው፡፡" እግዚአብሔር የሚሰጠንን በልግስና መስጠት እና እግዚአብሔር ሲባርከንም ሌሎችን መባረክ የመንፈሳዊ አተነፋፈሳችን የመሠረት ድንጋይ መሆኑን ከዚህ ቀደም በተማርነው ትምህርት ተገንዝበናል፡፡ ከእግዚአብሔር መስማታችን መንፈሳዊውን ንጹህ ዓየርን ወደ ውስጥ መሳብ ነው፡፡ ወደ ውጪ ማስወጣት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሰማነውን መታዘዝ እና ለሌሎች ማካፈልነው፡፡ ለመታዘዝ እና ጌታችን ለእኛ ያካፈለውን ለማካፈል ታማኞች ስንሆን፣ እርሱ ለእኛ ካካፈለውም በላይ የማካፈል ቃል ኪዳን አለው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው "ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥" ይህ ወደ ጠለቀው መገለጣዊ ዕይታ የሚወስድ መንገድ ነው፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሆነ ታላቅ ቅርርብ እና እግዚአብሔር እንድንኖር የፈጠረንልንን የተትረፈረፈ ሕይወት መኖርም ነው፡፡ ይህም በመልካሙ ሥራ ውስጥ እግዚአብሔር እንድንሄድበት የተለመው መንገድም ነው፡፡ ታላቁን ሽልማት ከእግዚአብሔር መሸለም ከፈለግን፣ እግዚአብሔር እንደሚባርክ ቃል የገባውን ሁለቱን ነገሮች ማድረግን መለማመድ አለብን፡፡ ማድረግ ያለብንም መታዘዝ እና ማካፈል ማድረግ እና ማስተማር መለማመድ እና ለሌሎች ማስተላለፍ - እግዚአብሔር እንድናደርግ የነገረንን ሁሉ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሌሎችም የእግዚአብሔርን ታላቅ ሽልማት እንዲቀበሉ የምንፈልግ ከሆነም፣ እኛ ያደረግነውን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ማሳየት ይገባናል፡፡ ይህም በከፊል ደቀ መዝሙር የመሆን አንድ ክፍል ሲሆን፣ ደቀ መዝሙር የማድረግም ዋናው አካል ነው፡፡ እኛ ተከታዮች እና መሪዎች ነን፡፡ እኛ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ነን፡፡ እኛ የተባረክን እና ደግሞም የምንባረክ ነን፡፡ መታዘዝን እና የተማርነውን ለሌሎች ማካፈልን ለመጀመር ሁሉን እስክናውቅ ድረስ እንድንጠብቅ እግዚአብሔር አይፈልግም፡፡ ምክንያቱም እኛ ሁሉን የምናውቅበት ቀን በፍጹም አይመጣም፡፡ ደቀ መዛሙርትን ከማብዛታችን በፊት በሕይወት የመብሰላችንን ነገር እግዚአብሔር አይጠብቀውም፡፡ በሕይወት የመብሰላችንን ነገር እግዚአብሔር አይጠብቀውም፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ያወቅነውን እንድንታዘዝ፣ እንዲሁም የሰማነውን እንድናካፍል ነው፡፡ ለሌሎችም ይህንኑ እንዲያደርጉ እንድናስተምርም ይፈልጋል፡፡ ይህም ሌላ ሳይሆን - እንድናደርግ የነገረንን መታዘዝ እና ማካፈል ነው፡፡ የብስለት እና የእድገት መንገድም ይኸው ነው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. በእግዚአብሔር መንፈሳዊ ኢኮኖሚ እና በእኛ ምድራዊ ነገሮች መካከል የምናስተውላቸው አንዳንድ ልዩነቶች ምንድን ናቸው?

READ

(5 min)

ትልቅ፣ ታላቅ እና ከሁሉ የላቀ በረከት

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ፣ እጅግ ታላቅ እና ከሁሉ የላቀ በረከቶች እነዚህንም ከሌሎች ጋር እንደምትከፋፈሉ እንነጋገራለን፡፡ አንድ ሰው ኢየሱስን ለመከተል ሲመርጥ፣ ይህን ጠብቆ በትክክል እንዲሄድ የምትረዱት እንዴት ነው? በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን አምራች እንዲሆን የምትደግፉትስ እንዴት ነው? እግዚአብሔር ሊሰጠው የወደደውን የእግዚአብሔርን በረከቶች ሁሉ እንዲቀበል የምትረዱትስ እንዴት ነው? ይህንን በመንገር መጀመር ይቻላል፡- • ኢየሱስን መከተል በረከት ነው፡፡ • ሌሎች ኢየሱስን እንዲከተሉ መምራት ታላቅ በረከት ነው፡፡ • በአዲስ መንፈሳዊ ቤተሰብ ውስጥ መቀላቀል ታላቅ በረከት ነው፡፡ • ሌሎች የኢየሱስ ተከታዮች አዳዲስ መንፈሳዊ ቤተሰቦችን እንዲመሠርቱ ማስታጠቅ ከበረከቶች ሁሉ የላቀው ነው፡፡ "ኢየሱስን ለመከተል በመወሰናችሁ እግዚአብሔር ባርኳችኋል፡፡ በእግዚአብሔር ታላቅ በረከት ብቻ ሳይሆን በጣም በላቀው በረከቱ፤ ከዚህም በላይ እጅግ በጣም በላቀው በረከት እንድትባረኩ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ እንዴት እንደሚቻል ማየት ትፈልጋላችሁ?" ብላችሁ ትጠይቋቸዋላችሁ፡፡ ስለዚህ የበለጠ ለማወቅ የፈለጉ እንደሆነም፣ የሚያውቋቸውን የ100 ሰዎች ሥም ዝርዝር እንዲጽፉ ጠይቋቸው፡፡ ከዘረዘሯቸው 100 ሰዎችም 5ቱን እንዲመርጡ ጠይቋቸው፡፡ 5ቱ ሰዎች ግን ኢየሱስን የማያውቁ እና የማይከተሉ፣ እንዲሁም ትክክለኛውን የሕይወት መንገድ ኢየሱስን ሊተዋወቁ ይገባል ብለው የሚያስቧቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ኢየሱስን መከተል መባረክ ነው፡፡ ይህንን በረከት ከሌላ ከማን ጋር መካፈል ትፈልጋላችሁ? ምስክርነታቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ አስተምራቸዋለሁ፤ ያም እግዚአብሔር በሕይወታቸው እየሠራ ያለውን ታሪክ ነው፡፡ ወንጌልን ማለትም እግዚአብሔር በዓለም ላይ ምን እየሠራ እንዳለ ታሪክ ለሌሎች እንዴት እንደሚያካፍሉም አስረዳቸዋለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ታላቅ፣ አዎ በጣም ታላቅ የሆነውን እና እጅግ ታላቅ የሆነው በረከቱን እንዴት ለሌሎች እንደሚያካፍሉም አስገነዘባቸዋለሁ፡፡ የተመረጡትን 5 ሰዎችም እያንዳንዳቸው እነዚህን ነገሮች እንዲለማመዱ አደርጋቸዋለሁ፡- በመጀመሪያ ታሪካቸውን፣ ከዚያም የእግዚአብሔርን ታሪክ፣ እና የእግዚአብሔርን በረከቶች እንዲያካፍሉ አስተምራቸዋለሁ፡፡ በእያንዳንዱ ልምምዳቸውም ከሚመርጧቸው ሰዎች የአንዱን ገጸ-ባሕርይ በመወከል እኔም እተውናለሁ፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜም ታሪካቸውን ይናገራሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ታሪክ ይናገራሉ፡፡ እኔንም የኢየሱስ ተከታይ እንድሆን ግብዣ ያቀርቡልኛል፡፡ በዚህ ጊዜም የእግዚአብሔርን ታላቅ፣ በጣም ታላቅ እና አዎ እጅግ በጣም ታላቅ የሆነውን በረከት ምንነት ያስተምራሉ፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜም እኔ ጥያቄ እጠይቃለሁ፤ ወይም የወከልኩት ገጸ-ባሕርይ ሊሰጠው የሚችለውን ሃሳብ እሰጣለሁ፡ ከልምምዳችን ፍጻሜ በኋላም በሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀጠሮ እንይዛለን፡፡ ከተቻለም ከሁለት ቀን በኋላ እንገናኛለን፡፡ የተከፋፈልነውም ነገር ውጤት አስገኝቶ እንደሆነ እንገመግማለን፡፡ የመረጧቸውን 5 ሰዎች እንደሚገባው ለማግኘት እንዲችሉ በቂ ጊዜ እሰጣቸዋለሁ፡፡ ሆኖም የምሰጣቸው ጊዜ ግን ነገሩን ችላ እስኪሉት ወይም እስኪዘነጉት የሚያደርስ አይደለም፡፡ ሁልጊዜም ለክትትል እንዲያመቸኝ የስልክ ቁጥራቸውን ወይም የኢ-ሜይል አድራሻቸውን እይዛለሁ፡፡ ሃሳባቸውን በሚያካፍሉበትም ወቅት እግዚአብሔር ትክክለኛውን ቃል እንዲሰጣቸውም እጸልይላቸዋለሁ፡፡ ከሁለት ቀን በኋላም፣ የሚያካፍሉት ነገር በምን ሁኔታ እንዳለ እንደገና ተገናኝተን እናወራለን፡፡ ከማንም ጋር ካልተከፋፈሉም፣ ታሪካቸውን የማካፈያውን ልምምድ እንደገና እንድናደርግ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ከመረጧቸው ሰዎች አንዱን በሚያገኙበት ወቅት አብሬኣቸው እንድሆንም እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ታሪካቸውን ማካፈል ለመጀመር የሚረዳቸውን ማንኛውን ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ጥረት አድርጋለሁ፡፡ ይሁን እንጂ አዳዲስ ነገሮችን አልናገርም፡፡ ለተማሩት ነገር ታማኝነታቸውን የሚያሳዩበትን ምርጥ እድል እንዲጠቀሙ ሁኔታዎችን አመቻችላቸዋለሁ፡፡ እምቢ ካሉ እና ምክንያት የሚደረድሩ ከሆነ ግን፣ እግዚአብሔርን "ዘርህ የተዘራው እውን በምርጥ መሬት ላይ ይሆን? በዚህስ መንገድ ለመንግሥትህ ፍሬ ይገኝ ይሆን? ወይስ የመንግሥትህን ሃብት ፈሰስ የማደርግበት ሌላ ሥፍራ ይኖር ይሆን?" ስል እጠይቃለሁ፡፡ ታሪካቸውን የሚያካፍሉ ከሆነ፣ የደስታችንን ጊዜ እናከብራለን! ምንም እንኳን 100 ሰዎች ዝርዝራቸው ውስጥ አንዳቸውም ጌታን ለመከተል እሺታቸውን ባያሳዩም፣ እነዚህ ሰዎች ግን ለሰሙት ታዘው የተማሩትን ለሌሎች ማካፈል በመቻላቸው ብቻ ደስታዬ ወደር አይኖረውም፡፡ ታማኝ መሆን ይህ ነው፡፡ በጥቂቱ ታማኝ ሆነዋልና፣ የበለጠውን ላካፍላቸው ደስታዬ ብዙ ነው፡፡ ስለጥምቀት ደግሞ ከእነርሱ ጋር እከፋፈላለሁ፤ በዚህም እንዲቀጥሉ ወይም የሚጠቀሙበትን ሌላ መሣሪያ እሰጣቸዋለሁ፡፡ በዝርዝር ከያዟቸው 100 ሰዎች ሌሎችን እንዲመርጡ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ እነዚህም ኢየሱስን የማያውቁ ወይም የማይከተሉ መሆናቸውንም አሳስባቸዋለሁ፡፡ ከዚያም እንደ ቀድሞው ልምምዳችንን እናደርጋለን፤ ይህም ታሪካቸውን፣ የእግዚአብሔርን ታሪክ እና የእግዚአብሔርን በረከቶች አያይዞ የሚቀርብ ነው፡፡ ከዚያም የጋራ ጸሎት እናደርጋለን፡፡ የተማሩትን ለእነዚህ ሊያካፍሏቸው እንደሚገባ ላመኑባቸው ሰዎች ካካፈሉ፣ በእርግጥ አሁንም ማካፈላቸውን በደስታ እናከብረዋለን! የእግዚአብሔር ቤተሰብ እየሰፋ ነው! እኔ ሁልጊዜም ታላቅ የሆነውን፣ በጣም ታላቅ የሆነውን፣ አዎ እጅግ በጣም ታላቅ የሆነውን በረከት ለሌሎች ማካፈላቸውን እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተሰብ እድገት የሚወስነው ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በረከት ለሌሎች ማካፈል ተስኗቸው እንደሆነም፣ አሁንም ቀድሞ ያደረግነውን እንተሳሰባለን - በረከቶቹን እናስባለን፡፡ አዲስ እንዴት አማኝ የሚያውቃቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሊይዝ እንደሚችል፣ እንዴት ታሪኩን ማካፈል እንደሚችል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ታሪክ በመንገር እንዴት የእግዚአብሔርን በረከት እንደሚሰጥ፤ በአጠቃላይ አዲስ አማኝ እንዴት የተማረውን ለሌሎች እንደሚያካፍልም የሚማርበትን መለማመዳችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህን ከተለማመድን በኋላ፣ ወደሌላ አዲስ አማኝ እልካቸዋለሁ፤ በዚህም የተማሩትን ማካፈልን እንዲቀጥሉ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን፣ እነዚያ የተማሩትን ከስም ዝርዝር ውስጥ ለመረጡት ተወዳጅ ሰው ቢያካፈሉ እና የእግዚአብሔርን በረከቶች እንዲካፈል ቢያደረጉስ? እንደዚህ ሲሆን ደግሞ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡ እንዲህ ያለውን ሰው ነው የእግዚአብሔር ቃል "መልካም መሬት" ብሎ የሚጠራው፡፡ መልካም የእግዚአብሔር ቤተሰብ ቀድሞ ካየኋቸው ሰዎች በላይ በተለየ የሚያሳድግ ሰው መሆን ነው! እንደዚህ ያሉ ሰዎች ሳገኝ በተለየ መንገድ በተደጋጋሚ የማገኝበትን ሁኔታ አመቻቻለሁ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያድጉም በጣም እተጋለሁ፡፡ እንደ ጥምቀት ያለውን አዲስ ትምህርና 3 - 3ኛን ቡድንም እንዴት እንደሚመሠርቱ አስተምራቸዋለሁ ፡፡ በዚህ ጊዜም እንደ መንፈሳዊ ቤተሰብ ሆነው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ እንደ እነርሱ አዳዲስ ከሆኑት ደቀ መዛሙርት ጋር ይህኑ አደርጋለሁ፡፡ ታማኝ እስከሆኑ ድረስ፣ በጣም ደስተኛ በመሆን የምችለውንና ያለኝን ሁሉ በማካፈል ከዚያ ቀጥሎም እግዚአብሔር የሚያደርገውን እጠብቃለሁ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን በአንድ ጊዜ እንድ እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ ሁልጊዜም ለመማር፣ ለመታዘዝ እና ያወቁትን ለማካፈል እንዲችሉ እድል መስጠት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔርን ያለኝን ከእነርሱ ጋር እንድከፋፈል እንዲሁም እንድንማማር ስለፈቀደልኝ እና ስለሰጠኝ ሰዎች እያመሰገንኩ ስጸልይ ታላላቅ በረከቶቹን እንዲያፈስስባቸውም እለምነዋለሁ፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ኢየሱስን ለመከተል ስትጀምሩ የተማራችሁት ምሳሌ ይህ ነበረ? ካልሆነስ፣ ምን የተለየ ነበር?
  2. ወደ እምነት ከመጣችሁ በኋላ፣ ሌሎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ከመጀመራችሁ በፊት ምን ያህል ጊዜ ወስዶባችሁ ነበር?
  3. አዳዲስ የኢየሱስ ተከታዮች ማካፈል እና ሌሎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ቢጀምሩ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።››

ተወያዩ

(10 min)

  1. "ምሥክሩ" እንድትሆኑ እና ታሪኩን እንድትናገሩ የሚለውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስትሰሙ ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው ምንድነው?
  2. ኢየሱስ ምሥራቹን ለማካፈል ሌላ መንገድ ሳይሆን ተራ ሰዎችን የመረጠው ለምን ይመስላችኋል?
  3. የእግዚአብሔርን ታሪክ ለማካፈል የበለጠ ምቾት እንዲሰማችሁ ለማድረግ ምን ያስፈልጋችኋል?

ወንጌሉ

የእግዚአብሔርን ታሪክ (ወንጌልም ተብሎም ይጠራል) ለመንገር ምንም “ሌላ የተሻለ ምርጥ መንገድ” የለም ምክንያቱም የተሻለ ምርጡ መንገድ በምታካፍሉት ሰው መሠረት ይወሰናልና። እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር የእግዚአብሔርን ታሪክ በቅዱሳት መጻህፍት እውነት በሆነ እና ከሚያካፍለው አድማጭ ጋር በተገናኘ መንገድ መንገርን መማር አለበት።

የሚከተሉትን ሁለት አቀራረቦች ይገምግሙ እና አንዱን ለመለማመድ ይምረጡ።

READ

(5 min)

የዝግጅት አቀራረብ 1

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍል፣ የእግዚአብሔርን ታሪክ፣ ወንጌልን - ከፍጥረት እስከ ፍርድ - የሰውን ልጅ ታሪክ፣ ከአፈጣጠሩ እስከ ዘመን ፍጻሜው እንዴት እንደምናካፍል እንማራለን፡፡ የእግዚአብሔርን ታሪክ የምናካፍልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ታሪክ ለመንገር ምርጡ መንገድ እንደምታካፍሉት ሰዎች ሁኔታ እንደ ንጽረተ-ዓለማቸው ወይም ዓለምን እንደሚያዩበት እና እንደ ሕይወት ልምዳቸው የሚወሰን ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ለመስማት ቀና በሆኑ ልቦችና ለመሥራት በሚፈቅድ ልብ ይጠቀማል፡፡ ሥራው የእግዚአብሔር ነው፡፡ በዚህ ሥራም ተሳታፊ እንድንሆን የሚጋብዘንም እርሱ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ታሪክ ማስተዋወቂያው አንደኛው መንገድ እግዚአብሔር ፍጥረቱን ከፈጠረበት በዘመን ፍጻሜ እስካለው እስከ ፍርዱ ድረስ ያለውን ታሪክ በመተረክ ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔርን ታሪክ በዚህ መንገድ ስንናገረም እንደሁኔታው ልናሳጥረውም ልናስረዝመውም እንችላለን፤ በዝርዝር ልንገልጸውም ወይም ዋና ሁነቶችን አተኩረን ልንገልጸውም እንችላለን፡፡ አንድ መሳት የሌለብን ነገር ግን ፡ ሁልጊዜም ስንናገር የሰሚዎቹን ሰዎች ባሕል አቆራኝተን መሆን ይኖርበታል፡ በተለያዩ ባሕሎች እና ንጽረተ-ዓለም ወይም ምልከታ - ዓለም ባላቸው ሕዝቦች መካከል የእግዚአብሔርን ታሪክ ስንተርክም የማስተማሩን እና የመማሩን ሂደት እንዲያቀልልን የእጃችንን እንቅስቃሴ መጠቀምም እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር መልካም ዜና ታሪክም ይህንን ይመስላል፡- በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን እና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ፈጠረ፡፡ መጀመሪያዎቹን ሰዎች ወንድ እና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው፡፡ ውብ በሆነችው ኤደን ገነት ውስጥም አኖራቸው፡፡ የቤተሰቡ አካልም አደረጋቸው፤ ከእነርሱም ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት እንዲኖረውም አደረገ፡፡ የፈጠራቸውም ለዘላለም እንዲኖሩ አድርጎ ነው፡፡ ሲፈጥራቸው ሞት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ በዚያ ፍጹም ሰላማዊ በሆነውም ሥፍራ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ላይ አመጸ፡፡ ከዚያም ኃጢአት እና ስቃይ ወደ ዓለም እንዲገቡ አደረገ፡፡ ከዚህ የተነሳም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከኤድን ገነት አስወጣው፡፡ በእግዚአብሔር እና በሰውም ልጅ መካከል የነበረው ግንኙነት ተበላሸ፡፡ በዚህ የተነሳም ሰው ከሞት ጋር መጋፈጥ ግድ ሆነበት፡፡ ለብዙ መቶ ዓመታትም እግዚአብሔር መልዕክተኞቹን ወደ ዓለም ሲልክ ቆየ፡፡ በመልዕክተኞቹም በኩል እግዚአብሔር የሰው ልጅ ስለሠራው ኃጢአት በማስሳሰብ እርሱ ግን በታማኝነቱ እና በቃል-ኪዳን አክባሪነቱ የሰው ልጅን አዳኝ ወደ ዓለም እንደሚልክ ሲናገሩ ቆዩ፡፡ አዳኙም በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል የነበረውን የቀረበ ግንኙነት ያድሳል፡፡ አዳኙ የሰውንም ልጅ ከሞት ያድነዋል፡ አዳኙ ለሰው ልጅ የዘላለምንም ሕይወት ይሰጠዋል፤ ከሰውም ጋር ለዘላለም ይኖራል፡ እግዚአብሔር በብዙ ስለወደደን የዘመኑ ፍጸሜ በደረሰ ጊዜ ለዓለም አዳኝ እንዲሆን ልጁን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ በዓለም የተወለደውም ከድንግል ማርያም ነው፡፡ የኖረውም ፍጹም ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት ነው፡፡ ኃጢአትን በፍጹም አላደረገም፡፡ ኢየሱስ ሰዎችን ስለ እግዚአብሔር አስተምሯል፡፡ ታላቅ ኃይሉን ተጠቅሞም ብዙ ተዓምራትንም አድርጓል፡፡ አጋንንትን አስወጥቷል፡፡ ብዙ ሰዎችን ከበሽታቸው ፈውሷል፡፡ ዓይነ-ሥውራንን አብርቷል፡፡ መስማት የተሳናቸውን ፈውሷል፡፡ መሄድ የተሳናቸውንም ቆመው እንዲሄዱ አድርጓል፡፡ ኢየሱስ የሞተውንም ከሞት አስነስቷል፡ ብዙ የሃይማኖት ሰዎች በኢየሱስ ድርጊት ሰግተው ነበር፤ በቅንዓት ይቃጠሉም ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳም፣ ሊገድሉት ያሴሩ ነበር፡፡ እርሱ ኃጢአትን በፍጹም ባለማድረጉ ምክንያት፣ ሞት የሚገባው አልነበረም፡፡ እርሱ ግን ለሁላችን ሲል በመስዋዕትነት መሞትን መረጠ - ራሱንም እንደመስዋዕት በግ አቀረበ፡፡ በስቃይ የተሞላው ሞቱም የሰው ልጆችን ሁሉ ኃጢአት መደምሰስ የሚችል ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላም ኢየሱስ በመቃብር ተቀበረ፡፡ ኢየሱስ ያቀረበውንም መስዋዕት እግዚአብሔር ተመለከተ፡፡ ተቀበለውም፡፡ መቀበሉንም ማረጋገጡን ለማሳየት በሦስተኛው ቀን ከሞት አስነሳው፡፡ ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን መስዋዕት ራሱን እንደሰጠ ብናምን እና ብንቀበል ከኃጢአታችንም ተመልሰን ኢየሱስን የምንከተል ከሆነ፣ እግዚአብሔር ከኃጢአታችን ሁሉ ያነጻናል፡፡ እንደ ቤተሰብም እጁን ዘርግቶ እንደገና ይቀበለናል፡፡ በውስጣችን እንዲኖር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ይልክልናል፤ እርሱም ኢየሱስን መከተል እንድንችል ያደርገናል፡፡ ይህን የታደሰ ግንኙነታችንን እንደ መግለጫ እና መረጋገጫም የውሃ ጥምቀት እናደርጋለን፡፡ ለኃጢአት መሞታችንን ለማመላከት በውሃ ውስጥ ሰጥመን እናሳየለን፡፡ ከሰጠምንበት ውሃው ውስጥ በመውጣትም ኢየሱስን በመከተል አዲስ ሕይወት መጀመራችንን እናመላክታለን፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በምድር ላይ 40 ቀናትን ቆይቷል፡፡ ተከታዮቹንም ወደ ዓለም ሁሉ እንዲሄዱ እና የእግዚአብሔርን የማዳን መንገድ - የምሥራቹን ወንጌል እንዲናገሩ ኢየሱስ አዟቸዋል፡፡ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ያለውም ይህን ነው፡- "እንግዲህ ሂዱና አ ሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" ኢየሱስም በዓይናቸው ፊት ከፍ ከፍ ብሎ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ይኸው ኢየሱስ እንደዚያው በሄደበት መንገድ ከሰማይ ዳግመኛ ይመጣል፡፡ እርሱን ያልወደዱትን እና ያልታዘዙትንም ሁሉ የዘላለም ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ የወደዱትን እና የተቀበሉትንም ይቀበላቸዋል የዘላለምም ሽልማት ይሸልማቸዋል፡፡ እኛ እርሱን አምነን የተቀበልነውም እርሱ ባዘጋጃት አዲስ ሰማይ እና ምድር ለዘላለም እንኖራለን፡፡ ምክንያቱም እኛ ኢየሱስ ለኃጢአታችን የከፈለውን መስዋዕት አምነን ተቀብለናል፡፡ ከዚህ የተነሳም ከኃጢአታችን ሁሉ አንጽቶ ቀድሶናል፤ አድሶናልም፤ ከእግዚአብሔር ቤተሰብም ጋር ቀላቅሎናል፡፡ እርሱ ወዶናል እና እኛም እንወደዋለን፤ በመንግሥቱም ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንኖራለን፡፡ እግዚአብሔር ይወዳችኋል፤ ይህንን ስጦታ እንድትቀበሉም ይፈልጋል፡፡ ይህንን ስጦታ አሁን መቀበል ትወዳላችሁ?

READ

(5 min)

3-ክቦች

ወደ Zume ስልጠና እንኳን በደህና ተመለሳችሁ። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ ሶስት ክቦች የተባለውን መገልገያ በመጠቀም የእግዚአብሔር ታሪክ የሆነውን ወንጌል እንዴት እንደምናካፍል እንማራለን። የእግዚአብሔርን ታሪክ የምናካፍልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። የተሻለው መንገድ ልታካፍሉት ባሰባችሁት ሰውና ያ ሰው ለዓለም ባለው አመለካከት እና የህይወት ልምዶቹ መሠረት ይወሰናል። እግዚአብሔር ለመስማት፣ ለማካፈል፣ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑ ልቦችን ይጠቀማል። ይህ የእግዚአብሔር ስራው ነው። እኛን እንድንቀላቀል ብቻ ይጋብዘናል። የምናካፍልበት አንዱ መንገድ ሦስት ክቦች የምንለውን ቀላል ሥዕል ተጠቅመን የእግዚአብሔርን ታሪክ በማካፈል ነው። ሁላችንም የምንኖረው በጣም ጎዶሎ በሆነ ዓለም ነው። የመከራ፣ ሞት፣ ጦርነት፣ በሽታ፣ የሱሶች ታሪኮችን እናያለን እንዲሁም እንሰማለን። ይህ በሁሉም ቦታ ያለ ነው። ይሄ ሁሉ ግን የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ንድፍ አይደለም። የእግዚአብሔር ፍጹም ንድፉ በፍቅር፣ በደስታ፣ በአንድነትና በሠላም የተሞላ ዓለም ነው። ራሳችንን ከእግዚአብሔር ፍጹም ንድፍ አፈንግጠን ወደ ስብራት የመጣንበት መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳችን ኃጢአት ብሎ በሚጠራው ነገር ነው። ኃጢአት ከእግዚአብሔር መንገድ ርቀን የራሳችንን መንገድ መከተል ማለት ነው። ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል። ኃጢአት ስብራት ውስጥ ይጥለናል። ኃጢአት ወደ መንፈሳዊ ሞት ያመራናል። ሰዎች ከስብራት መውጣት ይፈልጋሉ። ከስብራት ለመውጣት ሁሉንም አይነት የተለያዩ ነገሮችን ሞከርን። አንዳንዶቻችንም አደንዛዥ ዕጾችና አልኮል ሞክረን ነበር። አንዳንዶቻችን በጥሩ ሥራ ወይም ብዙ ገንዘብ በማግኘት ከስብራት ለመውጣት ሞክረናል። አንዳንዶቻችን ከሰዎች ጋር ቅርበት መፍጠር ከስብራት እንደሚያወጣን እናስባለን። አንዳንዶች ደግሞ ሐይማኖትን ይሞክራሉ። ጥሩ ባህሪ ወይም ሌሎችን መርዳት ነፃ የሚያወጣን ይመስለናል። ከእነዚህ የተዘረዘሩት ነገሮች ውስጥ አንዳቸውም የስብራትን ችግር በትክክል አይፈቱም። ከችግሩ ለአፍታ ያህል የራቅን መስሎ በሚሰማን ጊዜ እንኳን፣ ወደ ነበርንበት ቦታ እንመለሳለን። እዚህ ጋር የሚከብድ እውነታ የሚሆነው አሁንም እዚያው ከሆንን፣ አሁንም በስብራት ውስጥ ከሆንን፣ ህይወት ሲያበቃ፣ ቀጥሎ ከእግዚአብሔር በቋሚነት ለዘለዓለም እንደተለየን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ ያንን ከእግዚአብሔር ተለይተን የምንቆይበትን ስፍራ ሲኦል ይለዋል፤ እግዚአብሔር ግን በስብራት ውስጥ እንድንቆይ አይፈልግም። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እኛን በጣም ከመውደዱ የተነሳ የራሱን ልጅ ልኮልናል ይላል። ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ኃጢአታችንን ሊሽርልን እና ከስብራት ነፃ ሊያወጣን ነው። ግን እንዴት? ኢየሱስ ይህን ሁሉ ሊያደርግ የቻለው እንዴት ነው? ኢየሱስ ፍጹም ሕይወትን ኖሯል። በጭራሽ ኃጢአት ያልሰራ ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው። በእግዚአብሔር ፍጹም ንድፍ ውስጥ የቆየው ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው። ከዚያም ኢየሱስ ፍጹም ህይወቱን አሳልፎ ሰጥቶ የእኛን ቦታ ወሰደ። ለኃጢአታችን ዋጋ ለመክፈል በመስቀል ላይ ሞተ። ስለዚህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ኃጢአታችንን በሞቱ ሽሯል። ኢየሱስ ከሞተና ከተቀበረ ከሶስት ቀናት በኋላ፣ በታላቅ መስዋዕትነቱ ምክንያት ከሙታን ተነሳ። እግዚአብሔር ኢየሱስን በሰማይ እና በምድር ላለው ነገር ሁሉ ንጉስ አደረገው። ንጉሡ ኢየሱስ ከስብራት የምንወጣበትን መንገድ አዘጋጅቶልናል። ከኃጢአታችን ተመልሰን ኢየሱስ ስለ እኛ እንደሞተ ካመንን እና በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ከተጠመቅን እግዚአብሔር ልክ እንደ ኢየሱስ በአዲስ ዓይነት ሕይወት መመላለስ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል ሆነን ለዘላለም እንድንመላለስ እንደሚያስነሳን ተናግሯል። ከዚያ እኛም በተሰበረው ዓለም ውስጥ ብንሆን እንኳ ይህንን አዲስ ሕይወት በመምሰል የኢየሱስን መምጣት፣ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚሰራበትን ጊዜ፣ ፍጹም በሆነ ሙሉነት ከእርሱ ጋር ለዘላለም የምንሆንበትን ጊዜ እንጠባበቃለን። ከእሱ ጋር ባለን ግንኙነት እንድናድግ እግዚአብሔር ይፈልጋል። እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ አካል ወደ መጀመሪያው እንከን የለሽ ንድፍ እንድንመለስ እግዚአብሔር ይፈልጋል። ኢየሱስ ተልዕኮን፣ የመኖርን ምክንያት እና ምርጡን ህይወት የምንመራበትን መንገድ ይሰጠናል። ኢየሱስ ለእኛ የሰጠን ተልዕኮ መሄድ ነው። ልክ እንደ አባቱ ኢየሱስም ይልከናል። ሌሎች ነፃ እንዲወጡና የዘላለም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል እንዲሆኑም ለማድረግ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ስብራት መለሰው። በዚህ ሶስት ክቦች ዓለም ውስጥ፣ ሁለት አይነት ሰዎች ብቻ ናቸው ያሉት። የእግዚአብሔር ፍጹም ንድፍ አካል የሆኑ። የእግዚአብሔርን የማዳን ተልዕኮ የሚኖሩ። እግዚአብሔርን ከዘላለማዊ ቤተሰቡ የሚያገናኙ ሰዎች ወይም ነፃ ለመውጣት ማንኛውንም ነገር እየሞከሩ ያሉ፣ አሁንም በስብራት ውስጥ ያሉ አንድ ሰው እንደሚያድናቸው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች። አሁን የቱ ጋር እንዳላችሁ ታውቃላችሁ? የት መሆንስ እንደምትፈልጉ ታውቃላችሁ? የእግዚአብሔርን ታሪክ የምናካፍልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ዋናው ነገር ማካፈል ነው። እግዚአብሔር ለመስማት፣ ለማካፈል፣ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑ ልቦችን ይጠቀማል። ይህ የእግዚአብሔር ስራው ነው። እኛን እንድንቀላቀል ብቻ ይጋብዘናል።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

  • መንፈሳዊ ኢኮኖሚ
  • ታላቁን በረከት መልቀቅ
  • ወንጌል እና ወንጌልን እንዴት ማካፈል እንደሚቻል

NEXT STEP

ታዘዙ

የመንፈሳዊ ኢኮኖሚ ፅንሰ-ሀሳብን ከጓደኞቻችሁ ጋር መካፈል ተለማመዱ እና ጌታ በልባችሁ እና በነፍሳችሁ ውስጥ እንዲያሰርጸው ጸልዩ። ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ ለማወቅ ጌታን ጠይቁት።

አካፍሉ

ስለ ታላቁ በረከት ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት። እንዲሁም እንዲለማመዱትም አድርጉ። ወደዚያ ሄዳችሁ ከማግኘታችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ ያካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 7

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 1116

ፀልዩ

(5 min)

ኢየሱስን በመከተል ሌሎች ኢየሱስን እንዲከተሉና ሌሎችን አዲስ መንፈሳዊ ቤተሰቦችን እንዲፈጥሩ በማብቃት እያንዳንዱ የቡድናችሁ አባል በረከቶችን እንዲለማመድ ጸልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

ልምምድ

(50 min)

ወንጌልን አካፍሉ

የQR ኮድን ቃኙ።

ለሁለት ወይም ለሦስት ሰዎች ተከፋፈሉ እና የእግዚአብሔርን ታሪክ እርስ በርሳችሁ መነጋገርን ተለማመዱ።

ከተለማመዳችሁ በኋላ ተቀያይሩ። መደጋገም በራስ መተማመንን ያመጣል። ይህን ስትጨርሱም፣ የእግዚአብሔርን ታሪክ ለማካፈል ዝግጁ ትሆናላችሁ።

የእግዚአብሔር ታሪክ፦ ከፍጥረት እስከ ፍርድ አይነት

በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔር ምድርንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ፈጠረ።

የቀደመውን ወንድ እና የቀደመችውን ሴት ፈጠረ። በውብ የአትክልት ስፍራ አስቀመጣቸው። የቤተሰቦቹ አካል አደረጋቸው እና ከእነሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው።

ለዘላለም እንዲኖሩ ፈጠራቸው። ከውድቀት በፊት ሞት አልነበረም። ይሁንና በዚህ ፍጹም ቦታ እንኳን ሆኖ ሰው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ ኃጢአት እና መከራን ወደ ዓለም አመጣ። እግዚአብሔርም ሰውን ከገነት አባረረው። አዳም እና ሄዋን ባለመታዘዛቸው በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ግንኙነት ፈርሷል። በውጤቱም የሰው ልጅ ሞትን መጋፈጥ ነበረበት። እግዚአብሔር ግን በብዙ መቶ ዓመታት ውስጥ መልእክተኞችን ወደ ዓለም መላኩን ቀጥሎ ነበር። ለሰው ልጅ ኃጢአቱን ማስታወስ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ታማኝነት እና አዳኝ (ኢየሱስን) ወደ ዓለም ለመላክ የገባውን ቃል ነግሯል።

የሚላክላቸው አዳኝ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ይመልሳል።ሰውን ከሞት ይታደጋል። የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል እናም ለዘላለም ከሰው ጋር ይኖራል። እግዚአብሔር ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ጊዜው ሲደርስ አዳኝ እንዲሆንልን ልጁን ኢየሱስን ወደ ዓለም ላከው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። በድንግል ማሪያም ተወለደ። ፍጹም የሆነ ሕይወት ኖሯል። ኃጢአትን አልሰራም። ኢየሱስ ሰዎችን ስለ እግዚአብሔር አስተምሯል። ታላቅ ኃይሉን ያሳዩ በርካታ ተአምራትን አድርጓል። ብዙ አጋንንትን አስወጥቷል። ብዙ ሰዎችን ፈውሷል። ዕውሮችን አብርቷል። ደንቆሮዎችን እንዲሰሙ አደርጓል። አንካሶች እንዲራመዱ አድርጓል። ሙታንን አስነስቷል። ይህም ሆኖ ግን በርካታ የሐይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ስጋትና ቅናት ነበራቸው።

እንዲገደል ፈልገው ነበር። ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአት ስላልሠራ መሞት አላስፈለገውም ነበር።

ቢሆንም ኢየሱስ ለሁላችንም መሥዋዕት ሆኖ መሞትን መረጠ። አሳዛኝ ሞቱ የሰው ልጆችን ኃጢአት ሻረ። ከዚህም በመቃብር ተቀበረ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ያቀረበውን መስዋዕት አይቶ ተቀበለ። እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ኢየሱስን ከሙታን በማስነሳቱ መስዕዋትን መቀበሉን አሳይቷል።

የኢየሱስን መስዋዕት አምነን ከተቀበልን እና ኢየሱስን ከተከተልን ከኃጢያት ሁሉ እንደሚያነፃን እናም ወደ ቤተሰቡ እንደሚቀበለን እግዚአብሔር ተናግሯል።

እግዚአብሔር በውስጣችን እንዲኖር እና ኢየሱስን እንድንከተል መንፈስ ቅዱስን ይልክልናል። ይህንን የታደሰ ግንኙነት ለማሳየትና ለማፅናት በውሃ ጥቀምቀት ተጠምቀናል።

እንደ ሞት ምልክት እንዲሆን ከውኃው በታች ጠልቀናል። አዲስ ሕይወት ተቀብለን ኢየሱስን እንደተከተልን ምልክት እንዲሆን ከውኃው ወጥተናል።

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ በምድር ላይ ለ40 ቀናት ቆይቷል።

ኢየሱስ ተከታዮቹ በሁሉም ቦታ ሄደው የወንጌሉን ምሥራች በመላው ዓለም ላሉ ሰዎች እንዲናገሩ አስተምሯቸዋል። ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።

ከዚያም ኢየሱስ በዓይናቸው እያዩት ወደ ሰማይ አረገ። አንድ ቀን፣ ኢየሱስ በሄደበት መንገድ ዳግም ይመጣል። እርሱን የማይወዱትንና የማይታዘዙትን ሰዎች ለዘላለም ይቀጣቸዋል። የሚወዱት እና የሚታዘዙትን ግን ለዘላለም ይቀበላል እናም ይሸልማል። በአዲሱ ሰማይ እና በአዲሱ ምድር ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም እንኖራለን።

ኢየሱስ ለኃጢአቴ የከፈለውን መስዋዕት አምናለሁ እናም ተቀብያለሁ። ኃጢያቴን አጥቦ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል አድርጎኛል። ይወደኛል፣ እኔም እወደዋለሁ፤ በመንግስቱም ለዘላለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ። እግዚአብሔር ይወዳችኋል እናም ይህን ስጦታ እንድትቀበሉ ይፈልጋል። አሁን ጌታን መቀበል ትፈልጋላችሁ?

ታሪኩን ለመናገር ምቾት እስኪሰማችሁ ድረስ ይህን የወንጌል አቀራረብ ተለማመዱ።

ይከልሱ

(1 min)

NEXT STEP

ታዘዙ

ምንን ከፍጥረትን እስከ ፍርድ ታሪክ (ወይም የእግዚአብሔርን ታሪክ ለማካፈል በሌላ መንገድ) እንድታሰለጥኑለት እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ።

አካፍሉ

በዚህ ሳምንት የእግዚአብሔርን ታሪክ የምትለማመዱበትን ጊዜ በማሳለፍ ከ100 ዝርዝራችሁ ውስጥ ቢያንስ "የማያምን" ወይም "የማይታወቅ" ባላችሁ ምልክት ካደረጋችሁበት የሆነ ሰው ጋር ተካፈሉ።

ክፍለ ጊዜ 8

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 5431

ፀልዩ

(5 min)

ምሥራቹን ለሌሎች እንድናካፍል ወደጠራን እግዚአብሔር ጸልዩ እናም አመስግኑት። ለእያንዳንዱ የቡድናችሁ አባል የክርስቶስን አእምሮ እንዲሰጠው እና እንያንዳንዱንም በመንፈሱ እንዲሞላቸው እግዚአብሔርን ለምኑት።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና እነዚህን መሳሪያዎች ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን፡-

  • ጥምቀት እና እንዴት ማጥመቅ እንደሚቻል
  • የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

READ

(5 min)

ጥምቀት

በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት ጥምቀት ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …" ጥምቀት፡- ጥምቀት ወይም በመነሻ ቃሉ "ባፕቲዞ" ማለት ማጥለቅ ወይም ማስጠም ማለት ሲሆን፣ ይህም ልክ ልብስ በቀለም ሲነከር ተለውጦ እንደሚወጣው ያለ ትርጓሜ ያለው ነው። ጥምቀት የአዲስ ሕይወትን ምስል የያዘ ነው፤ በኢየሱስ መልክ እንጠመቃለን፤ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር እንደታዘዘው የመታዘዝን መልክ ይዘን ከውሃው እንወጣለን። ይህም መልክ ለኃጢአት የመሞት መልክ ነው፤ ልክ ኢየሱስ ስለኃጢአታችን እንደሞተው ማለት ነው፤ የአሮጌው ሕይወታችን ገጽታ የመቀበርም መልክ ነው፤ ልክ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳው እና ዛሬም እንደ ሕያው ጥምቀት በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ሕይወት ዳግመኛ የመወለድ ገጽታንም የያዘ ነው። ከዚህ በፊት ማንንም አጥምቃችሁ የማታውቁ ከሆነ፣ ማጥመቅ አስፈሪ ነገር ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም እንደእርሱ መሆን የለበትም። ከዚህ ቀጥሎ የማጥመቅ ጥቂት መመሪያዎች ቀርበዋል፡- የረጋ ውሃ አግኙ፤ ውሃውም ተጠማቂውን አዲስ ደቀ መዝሙር ለማጥለቅ በቂ ጥልቀት ያለው ይሁን። ይህም የመዋኛ ገንዳ፣ ወንዝ፣ ሃይቅ፣ ውቅያኖስ ወይም ሌላ ውሃ ማከማቻ ሊሆን ይችላል። በጥምቀትም ወቅት ደቀ መዝሙሩ የአጥማቂውን አንድ እጅ በሚገባ ይያዝ ፤ አጥማቂው በሌላኛው እጁም የተጠማቂውን ጀርባ ይደግፍ። ከዚያም አጥማቂው የተጠማቂውን ውሳኔ ለማረጋገጥ ሁለት ጥያቄዎችን ይጠይቅ፡- "ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታህ/ሽ እና አዳኝህ/ሽ አድርገህ/ሽ ተቀብለሃል/ሻልን?" "ኢየሱስን እንደ ንጉሥህ በቀሪው ዘመንህ ለመታዘዝ እና ለማገልገል ትፈቅዳለህ/ትፈቅጃለሽን?" ለሁለቱም ጥያቄዎች የተጠማቂው/ዋ ምላሽ "አዎ" ከሆነ፣ ከዚያም አጥማቂው እንዲህ ይበል፡- "በኢየሱስ ማመንህን/ሽን ስለመሰከርህ/ሽ፣ አሁን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሃለሁ/ሻለሁ። ተጠማቂው/ዋ በውሃው ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንዲጠልቅ/እንድትጠልቅ እና ከውሃውም እንዲወጣ/እንድትወጣ አጥማቂው ይርዳቸው። አጥማቂው፣ የኢየሱስ ተከታይ የሆነን/ችን አንድ ሰው አጠመቀ ማለት ነው፤ ይህም/ችም ሰው የሰማይ አዲስ ዜጋ እና አዲስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው/ች ማለት ነው። ስለዚህ ይህ የደስታ ጊዜ ነው!ለእግዚብሔርም ክብር የመስጫ ጊዜ ነው! ጥምቀት ኢየሱስ ለተከታዮቹ የሰጠው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ነው፤ የዙሜ የመሣሪያዎች ቋትም መሠረት ነው።

ተወያዩ

(10 min)

  1. አንድ ሰው አጥምቃችሁ ታውቃላችሁ?
  2. ለማጥመቅስ አስባችሁ ታውቃላችሁ?
  3. ታላቁ ተልዕኮ ለእያንዳንዱ የኢየሱስ ተከታይ ከሆነ፣ ሁሉም የኢየሱስ ተከታይ ሌሎችን እንዲያጠምቅ ተፈቅዶለታል ማለት ነውን? ለምን ወይም ለምንስ አይሆንም?

ጠቃሚ ማሳሰቢያ - ተጠምቀሃል?

ካልተጠመቃችሁ፣ ከዚህ ስልጠና ማብቂያ አንድ ተጨማሪ ክፍለ ጊዜ በፊት ይህን እንድታቅዱ እናበረታታችኋለን። ለኢየሱስ "አዎ" እያላችሁ እያከበራችሁ እያለ የዚህ አስፈላጊ ቀን አካል እንዲሆን ቡድናችሁን ጋብዙ።

READ

(5 min)

የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

በዙሜ የሥልጠና መሣሪያዎች ቋት የሦስት ደቂቃ ምስክርነት ኢየሱስ ለተከታዮቹ እንዲህ ነው ያለው፡- "እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ።" እንደ ኢየሱስ ተከታዮች፣ እኛ "ምስክሮች"ም ነን፤ ኢየሱስ በሕይወታችን ያደረገውን ለውጥ "የምንመሰክር" ነን ማለት ነው። የእኛ ምስክርነት የሚባለውም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የቅርብ ግንኙነት ታሪክ ነው። ሁሉም ሰው ታሪክ አለው። ይህም ታሪካችሁን መናገርን የምትለማመዱበት አጋጣሚ ነው። ይህንን ነገር አብሮ/ራ የሚለማመድ/የምትለማመድ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ምረጡ። ከዚያም ከ100ዎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር 5ቱን ለዩ። የምትመርጧቸውንም ሰዎች "ክርስቲያን ያልሆኑ" ወይም "መንፈሳዊ አቋማቸው የማይታወቅ" መሆናቸውን አረጋግጡ። ታሪካችሁን እና ከኢየሱስ ጋር ያላችሁን ታሪክ መናገርን ለልምምድ ከመረጣችኋቸው ሰዎች ጋር ተለማመዱ። በዚህ ጊዜም ምስክርነታችሁን ልትነግሯቸው ካሉት 5 ሰዎች የአንዱን ገጸ-ባሕርይ በመሆን ተውኑ። በዚህም ለ5ቱ ሰዎች እንደሚስማማ አድርጋችሁ ታሪካችሁን መቅረጽንም ተለማመዱ። ይህም ታሪካችሁን አሳጥራችሁ በ3 ደቂቃ ውስጥ ማቅረብ ያስችላችኋል። ታሪካችሁን የምታቀርቡባቸው ሥፍር ቁጥር የሌላቸው- በጣም ብዙ መንገዶች አሉ፤ ታሪክን ለሌሎች ከመንገር አንጻር ግን ውጤታማ የሆኑት ጥቂት ናቸው፡- ኢየሱስን ለመከተል ለምን እንደመረጣችሁ በጥቂት ቃላት መግለጽ ትችላላችሁ። ይህም ገና አዲስ ለሆነ አማኝ በጣም ጠቃሚ አቀራረብ ነው። ኢየሱስን ከመቀበላችሁ "በፊት" እና "በኋላ" ሕይወታችሁን መንገር ትችላላችሁ። ይህም ሕይወታችሁ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ከመቀበላችሁ በፊት ምን ይመስል እንደነበር እና ኢየሱስን ከተቀበላችሁም "በኋላ" ምን እንደሚመስል መንገር ነው። ይህም ቀላል እና ኃይለኛ አቀራረብ ነው። "ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ" እና "ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ውጪ" በሚልም የኑሮውን ገጽታ ማቅረብ ትችላላችሁ። በተለይ ኢየሱስን መከተል የጀመራችሁት በለጋ እድሜያችሁ ከሆነ፣ እንዲህ ያለው አቀራረብ ውጤታማ ይሆናል። ታሪካችሁን ማካፈል እንደጨረሳችሁም፣ ይህን ልምምድ የሚያደርጉ ጓደኞቻችሁ ሚናችሁን ይውሰዱ እና እነርሱ እንደ ምስክርነቱ አድማጭ ይሁኑ። እርስ በእርሳችሁም አንዴ ምስክርነቱን ተናጋሪ፣ አንዴ ደግሞ አድማጭ ሁለታችሁም አምስቱን ምርጫችሁን እስክታጠናቅቁ ተለማመዱ። ከዚህም በላይ ተጽዕኖ እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ? ታሪካችሁን ስትናገሩ፣ የምትናገሩት ባለሦስት ዘርፍ ታሪክ እየተናገራችሁ እንደሆነ ማሰባችሁ መልካም ውጤት ያስገኛል። ይኸውም፣ የሰሚዎቹ ታሪክ፡- የግል መንፈሳዊ ጉዞውን እንዲነግራችሁ የምታናግሩትን/የምታናግሯትን ሰው ጠይቁ። ታሪካችሁ፡- ከሰሚው/ዋ ሕይወት እና ልምድ አንጻር የተቀረጸውን ታሪካችሁን ተርኩለት/ላት። የእግዚአብሔር ታሪክ፡- በመጨረሻም ከሰሚው/ዋ የዓለም ምልከታ - ንጽረተ-ዓለም፣ እሴት እና የሕይወት ዋና ነገር ጋር በተቆራኘ መልኩ የእግዚአብሔርን ታሪክ ንገሩ። ነገሩን እንዴት እንደምትጀምሩ ጭንቀት ከገባችሁ፣ ቀለል አድርጋችሁ እዩት። ኢየሱስን ለምን መከተል እንደወሰናችሁ የሆነ ነገር በሉ። የእናንተን ታሪክ የሌላውን ሰው ሕይወት ለመለወጫ እግዚአብሔር ሊጠቀምበት ይችላል። ነገር ግን አስታውሱ፣ ታሪካችሁን መናገር ያለባችሁ ግን እናንተ ናችሁ። በሦስት ደቂቃ የምትናገሩት ታሪካችሁ በዙሜ የመሣሪያዎች ቋት ውስጥ ያለ ሌላው ቀላል መሣሪያ ነው።

ልምምድ

(30 min)

የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

የQR ኮድን ቃኙ።

ታሪካችሁን በመፃፍና ለሶስት ደቂቃዎች ብቻ በማቆየት ስሩ። (10 ደቂቃ)

ከሁለት እስከ ሶስት በቡድኖች ተከፋፍላችሁ ማካፈልን ተለማመዱ። (20 ደቂቃ)

ሦስት መሰረታዊ የምሥክርነት አይነቶች

ታሪካችሁን ለማቅረብ የምታዘጋጁባቸው በርካታ መንገዶች ቢኖሩም በጥሩ ሁኔታ ይረዳሉ ብለን የምናስባቸው አንዳንድ መንገዶች እነሆ፦

  • ቀላል መግለጫ - ኢየሱስን ለመከተል ለምን እንደመረጣችሁ ለመግለፅ ቀላል መግለጫ ማካፈል ትችላላችሁ። ይህ ለአዲስ አማኝ በሚገባ ይሰራል።
  • በፊት እና በኋላ - "በፊት" እና "በኋላ" የነበራችሁን ታሪክ - ኢየሱስን ከማወቃችሁ በፊት ህይወታችሁ ምን ይመስል እንደነበረ እና አሁን ምን እንደሚመስል ማካፈል ትችላላችሁ። ቀላል እና ብርቱ ነው።
  • ከ…ጋር እና ያለ - "ከ…ጋር" እና "ያለ" ታሪክ - ህይወታችሁ "ከኢየሱስ ጋር" ምን እንደሚመስል እና "ያለ ኢየሱስ" ምን እንደሚመስል ማካፈል ትችላለችሁ። በወጣትነታችሁ ኢየሱስን ወደማመን ከመጣችሁ ይህ የታሪክህ እትም በሚገባ ይሰራል።

ምስክርነታችሁን የምታካፍሉባቸው ሶስት ክፍሎች

ታሪካችሁን በምታካፍሉበት ወቅት፣ እንደ የሶስት ክፍል ሂደት አድርጋችሁ ማሰቡ አስፈላጊ ነው ነው፦

  • ታሪካቸው - የምታወሩትን ሰው ስለ መንፈሳዊ ህይወቱ እንዲያካፍላችሁ ጠይቁ።
  • ታሪካችሁ - ከዚያም ለተሞክሯቸው ያዘጋጃችሁትን ምስክርነታችሁን አካፍሏቸው።
  • የእግዚአብሔር ታሪክ - በስተመጨረሻም የእግዚአብሔርን ታሪክ ከዓለም እይታ፣ እሴቶች አንፃር እና ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ነገሮች ጋር በሚያገናኝ መንገድ አካፍሉ።

ምስክርነታችሁ ተፅዕኖ ለመፍጠር የግድ ረጅም መሆን ወይም ብዙ ዝርዝሮችን ማጋራት የለበትም። ይልቁኑም፣ታሪካችሁን በ3-ደቂቃ ለማጠቃለል የጥያቄዎች እና የጥልቅ ውይይት ጊዜ ተዘጋጅቶላችኋል። እንዴት እንደሚጀመር ግራ ከተጋባችሁ - ቀለል አድርጉት። እግዚአብሔር የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ የእናንተን ታሪክ ሊጠቀምበት ይችላል፣ነገር ግን መናገር የምትችሉት ራሳችሁ መሆናችሁን አስታውሱ።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ መሳሪያዎች፡-

  • ጥምቀት እና እንዴት ማጥመቅ እንደሚቻል
  • የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

NEXT STEP

ታዘዙ

ኢየሱስን የሚከተል ነገር ግን ያልተጠመቀ ሰው የምታውቁ ከሆነ፣ እንዲጠመቅ አጥብቃችሁ ጠይቁት እና ለማጥመቅ ጥያቄን አቅርቡ። አለበለዚያ ክህሎቶቹን ከወዳጅ ጋር ተለማመዱ።

አካፍሉ

ጥምቀት ምን እንደሆነ እና እንዴት ማድረግ እንደሚገባ ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁ። እንዲሁም እንዲለማመዱትም አድርጉ። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ እና ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት አግኙዋቸው።

ክፍለ ጊዜ 9

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 8768

ፀልዩ

(5 min)

ጸልዩ እና ከክርስቶስ ሞት፣ መቃብርና ትንሳኤ ጋር አንድ የመሆን ስጦታ የሰጠንን እግዚአብሄርን አመስግኑት። ቆይታችሁን እንዲመራላችሁ የእግዚአብሔር ቅዱሱ መንፈስን ጠይቁ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

ምስክርነታችሁን አካፍሉ

መደጋገም በራስ መተማመንን ይፈጥራል።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • የሶስት ደቂቃ ምስክርነት

NEXT STEP

ታዘዙ

ምስክርነታችሁን በመለማመድ በዚህ ሳምንት ጊዜ አሳልፉ፣ ከዚያም ከ100 ዝርዝራችሁ ውስጥ "የማያምን" ወይም "ያልታወቀ" ብላችሁ ምልክት ካደረጋችሁበት ቢያንስ አንድ ሰው ጋር ተካፈሉ።

አካፍሉ

በሶስት ደቂቃ ምስክርነት መገልገያ እንድታሰለጥኑ የሚፈልገውን እግዚአብሔርን ጠይቁት። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ።

ጠቃሚ ማሳሰቢያ – ቡድናችሁ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ የጌታን እራት ያከብራል። አስፈላጊ አቅርቦቶቹን (ዳቦ እና ወይን / ጭማቂ) ማስታወሳችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

ክፍለ ጊዜ 10

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 2347

ፀልዩ

(5 min)

በምስክርነታችን በኩል ለሚሰራባቸው መንገዶች ጸልዩ እና እግዚአብሄርን አመስግኑት፤ የጋራ ቆይታችሁን እንዲመራላችሁ መንፈስ ቅዱስን ጋብዙ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • ጅምር (እንደ ትንሽ ዳክዬ ያለ) ደቀ መዝሙርነት – ወዲያውኑ መምራት
  • መንግሥቱ የሌለበትን የሚመለከቱ አይኖች
  • የጌታ እራት እና እንዴት አንዲከናወን ማድረግ እንደሚቻል

READ

(5 min)

ጅምር ደቀ መዝሙርነት

ወደ ዙሜ ሥልጠና በድጋሚ እንኳን በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ የዳክዬ ጫጩቶቸን አካሄድ እንማራለን፡፡ ይህም ሞዴል ደቀ መዛሙርትን በማፍራት ረገድ ሁለት ጠቃሚ መርሆዎችን ለመረዳት ያስችለናል፡፡ የዳክዬ ግልገሎችስ እናታቸውን ተከትለው ሲጓዙ አይታችኋል? በዓለም የትም ሥፍራ ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ ይህ የዳክዬ ጫጩቶች ባሕርያዊ መገለጫ ተመሳሳይ ነው፡፡ እናት ዳክዬ ስትመራ፣ ጫጩቶቹ ይከተላሉ፤ ሁሉም አንድ ረድፍ ይዘው አንድ በአንድ ይከተላሉ፡፡ ይህንን ትዕይንት ቀረብ ብላችሁ ብትመለከቱት ደግሞ ሌላ ዓይነት ክስተትም ታገኛላችሁ፡፡ ያውም ምንድነው፣ እያንዳንዷ ጫጩት ዳክዬ በአንድ ጊዜ ሁለት ሚናዎችን ትጫወታለች፡- እያንዳንዷ ጫጩት ዳክዬ እናቷን ወይም ከፊቷ በቅርበት የምትሄደውን ሌላዋን ጫጩት ትከተላለች፡፡ ስለዚህም ትንሽዋ ዳክዬ በአንድ ጊዜ ከፊት ያለችውን በመከተል ተመሪ ስትሆን፣ ከኋላ ያለችውን በመምራት ደግሞ መሪ ሆና ትታያለች፡፡ ስለዚህ ጫጩቷ ዳክዬ መሪ ነች ተመሪ? ብለን ብንጠየቅ፣ መልሱ ሁለቱንም የሚል ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው እናታቸውን የሚከተሉ ጫጩት ዳክዬዎች የደቀ መዛሙርነትን መርሆ ከማሳየት አንጻር ገላጭ ምሳሌነት አለው የተባለው፡፡ እግዚአብሔር ቤተሰዎቹ በሕይወት እንዲበዙ እና እንዲያድጉ ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ የኢየሱስ ተከታይ መሪ እንዲሆንም ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ አማኝ ሕይወቱን የሚያካፍል እንዲሆንም ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ደቀ መዝሙርም ደቀ መዝሙር የሚያፈራ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ተከታዮቹ ሁሉ በአንድ ጊዜ መሪም ተመሪም መሆናቸውንም ይጠብቃል፡፡ እንደ ደቀ መዝሙር እና ደቀ መዝሙር አድራጊ ይህንን እንዳናደርግ ወጥመድ የሚሆንብን አንድ ነገር ቢኖር ሕይወታችንን ከማካፈላችን አስቀድሞ ሁሉን - አወቅ ወይም እውቀት - ዘለቅ መሆን አለብን የሚለው የተሳሳተ እምነታችን ነው፡፡ የደቀ መዝሙርነት መርህ ግን ከዚህ በተቃራኒ የቆመ ነው፡፡ ደቀ መዛሙርት ልክ እንደ ጫጩቶቹ ዳክዬዎች ናቸው፡፡ መሪ ለመሆን፣ ሁሉን ማወቅ አይኖርባቸውም፡፡ ማድረግ የሚገባቸው አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በእምነት ማደጋቸውን እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ የሚመራ ሁሉ እንዲከተለው፣ ሕይወቱን የሚያካፍል ሁሉ ደግሞ የሚያምን፣ እንዲሁም ደቀ መዝሙር የሚያፈራ ሁሉ ደቀ መዝሙሩ እንዲሆን እግዚአብሔር ይጠብቃል፡፡ ሌላው እንደ ደቀ መዝሙር አድራጊዎች የተያዝንበት ወጥመድ፣ የሆነ ሥፍራ ያለ የሆነ ሰው ሁሉን ያውቃል፤ እርሱን ብንከተል እንደላደላለን የሚለው የስሕተት እምነት ነው፡፡ ይሁንና ይህም ደቀ መዝሙር የማፍራት መርህ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እናቲቱ ዳክዬ ሁላችን የምንከተለው መሪ አንድ ነው፤ እርሱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የትኛውም ሚሽነሪ ወይም መጋቢ ወይም የሴሚናሪ መምህር ሳይሆን የእምነታችን ሙሉ መለኪያ ሊሆን የተገባው ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሌሎቻችን ሁላችን ወደእርሱ በማደግ "ሂደት ላይ ያለን ነን"፡፡ ሁልጊዜም ለኢየሱስ ቅርብ የሆነና ልንከተለው የምንችለው ሰው ይኖራል፡፡ እኛ ልንመራው የምንችለው ሌላ ሰው ደግሞ ወዲያ ይኖራል፡፡ በየትም ሥፍራ እንሁን፣ ዓይንና ልባችን ሳይነቃነቁ ጸንተው መቆም ያለባቸው ጌታ ኢየሱስ ላይ ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ከተጻፉት መጽሐፍት አብዛኞቹን የጻፈው እና ብዙዎቹን የመጀመሪያው ክፍለ - ዘመን አብያተ ክርስቲያናትን የተከለው ጳውሎስ፣ "እኔን ተከተሉ - እኔን ምሰሉ" ብሎ አልጻፈም፤ ይልቁንም "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" ነው ያለው፡፡ ጳውሎስ እንደ ደቀ መዝሙር በየትኛውም ሥፍራ ያሉ የዳክዬ ጫጩቶችን መርህ አውቆ ተከትሏል፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሠራተኛ የሆነ ማንኛውም መሪ ኢየሱስን የሚከተል ሊሆን ይገባዋል፤ ማኞች ሁሉ እንዲሁ ኢየሱስን ልንከተል ይገባናል፡፡ "ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።" በማለትም ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ጨምሮ ጽፏል፡፡ ጳውሎስ እንደ ደቀ መዝሙር በየትኛውም ሥፍራ የዳክዬ ጫጩቶችን መርህ አውቆ ተከትሏል፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሠራተኛ ማንኛውም መሪ ኢየሱስን የሚከተል ሊሆን ይገባዋል፤ አማኞች ሁሉ እንዲሁ ሕይወታችንን ለሌሎች በመስጠት ኢየሱስን ልንከተል ይገባናል፡፡ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ልቆ እንዲያድግ እና በእምነትም እንዲጎለብት ከፈለጋችሁ፣ በአንድ ጊዜ መከተልም መምራትም የሚችሉትን የዳክዬ ጫጩቶችን ዓይነት ደቀ መዛሙርት ስለማፍራት አስቡ፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. የበለጠ መማር የምትፈልጉበት የደቀ መዝሙርነት አንዱ ዘርፍ (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ/መረዳት፣ መጸለይ፣ የእግዚአብሔርን ታሪክ ማካፈል፣ ወዘተ.) ምንድን ነው? ለመማርስ ሊረዳችሁ የሚችል ማን ነው?
  2. ከሌሎች ጋር ልታካፍሉት የምትችሉት አንዱ የደቀመዝሙርነት ዘርፍ የትኛው ነው? ለማንስ ማካፈል ትችላላችሁ?

READ

(5 min)

መንግሥቱ የሌለበትን የሚመለከቱ አይኖች

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህም ክፍል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት የሌለችበትን ሥፍራ ማየት ሲጀምሩ እንዴት በፍጥነት እና በስፋት ደቀ መዛሙርት እንደሚበዙ እንማራለን፡፡ የሰው ልጆች ስልሆንን እያሰብነው የምንቆየው፣ የምናተኮረውና የምንሠራው በዓይናችን ያየናቸውን ነገሮች ነው፡፡ ይህንም ገሃዳዊ እውነታ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህም ነገሮች ያሉበት ሁኔታ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን የበለጠ በፍጥነት የምታድገው ማየት በማንችላቸው ላይ ስናተኩር ነው፡፡ እነዚህም የማይታዩ - የሌሉ ወይም እስከዚህ ጊዜ ድረስ ያልተከሰቱ ነገሮች ናቸው፡፡ በምድራችን እና በዙሪያችን የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ እንደሆነች በምድር የማትገለጥባቸው ቦታ እና ሁኔታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳም ትልቅ ክፍተት አለ፤ ስብራት፣ ሕመም፣ ስደት፣ ስቃይ እና አልፎ ተርፎም ሞት የየእለቱ የሕይወት ክስተቶች ሆነው ይታያሉ፡፡ ደቀ መዝሙር የሆነ የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ የእግዚአብሔር መንግሥት የተንሰራፋችበትን ብቻ ሳይሆን፣ የሌለችበትንም መመልከት መቻል አለበት፡፡ ለዚህም የመንግሥቱ ሥራ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ወደ ጨለማው ሥፍራ ጣልቃ በመግባት፣ ሸለቆውን የመሙላት እና ብርሃንን የማብራትን ሥራ በዚህ የምድር ሕይወታችን ይከናውናል፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የሌለችበትን ሥፍራ ለሁለት መመልከት እንችላለን፤ ይኸውም በምናውቃቸው ሰዎች እና እስካሁንም ባላገኘናቸው ሰዎች አማካኝነት ነው፡፡ የመጀመሪያው መንገድ በምናውቃቸው ሰዎች ነው ብለናል፡፡ ይኸውም በተለያየ መንገድ ግንኙነት ባለን በጓደኞቻችን እና በቤተሰባችን፣ አብረናቸው በምንሠራው ሰዎች፣ በክፍል ጓደኞቻችን፣ በጎረቤቶቻችን እና በመሣሠሉት ውስጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ታሪክ በፍጥነት ሰፍቶ መታወቅ የሚችለው በዚህ መንገድ ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች እንወዳቸዋለን፡፡ ስለእነርሱም ያገባናል፡፡ ይህም በተፈጥሮኣችን ውስጥ ያለ ነው፡፡ ኢየሱስ በምሳሌ ስለአንድ ራስ ወደዳድ ባለጸጋ ሰው ተናግሯል፤ ይህ ሰው በሕይወቱ ኩሩ እና ከራሱ ሌላ ለማንም የማይጨነቅ ነበር፡፡ ይኸው ሰው በሲዖል በቅጣት ላይ የነበረ መሆኑንም ነግሮናል፡፡ በሲዖል ሆኖም እንዲህ ሲል ለምኗል፡- "አባት ሆይ፥ አላዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ 'እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው' አለ፡፡" ኢየሱስ በዚህ ምሳሌው ራስ ወዳዶቹ እና በስቃይ ላይ ያሉ ሰዎች እንኳን የቅርባቸው ለሆኑ ሰዎች ምን ያክል እንደሚያስቡ ያሳየናል፡፡ የምናውቃቸው ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ የተቀመጡት እግዚአብሔር እኛን እንደወደደን እንድንወዳቸው ነው፡፡ እነዚህን ግንኙነቶቻቸንንም በትዕግስት እና በጽናት በመልካም ሁኔታ፣ በባለአደራነት ልብ እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ደቀ መዛሙርት ሊባዙ የሚችሉት እግዚአብሔር በዙሪያቸው ስላስቀመጣቸው ሰዎች ማሰብ ሲጀምሩና አቅደው አንድ ነገር ለመሥራት ሲነሳሱ ነው፡፡ ለእነርሱ ያላቸውን ሃሳብ እና ጥንቃቄ እንዲጨምሩ በማድረግ ጥቂት አቅደው በጥቂት ደረጃዎች ብቻ በደቀ መዛሙርት ብዜት ሊባዙ መቻላቸውን እንዲያስቡ እርዷቸው፡፡ የምታቅዱትም እንዲህ ነው፡- የሚያውቋቸውን 100 ሰዎች ስም ዝርዝር እንዲጽፉ አድርጓቸው፡፡ እነዚህንም ቀጥሎ በተገለጸው መልኩ በሦስት እንዲከፍሏቸው አድርጉ፡፡ • ኢየሱስን የሚከተሉ፤ አማኞች፣ • ኢየሱስን የማይከተሉ፤ አማኝ ያልሆኑ፣ • ኢየሱስን ይከተሉ አይከተሉ እርግጠኛ መሆን የማይችሉባቸው፤ ለአማኞቹ፣ ደቀ መዛሙርቱ የበለጠ ታማኝ እና ፍሬኣማ እንዲሆኑ ማስታጠቅ እና ማበረታታት ይችላሉ፡፡ አማኝ ላልሆኑት ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ አፍቃሪውን አባት እንዴት እንደሚያስተዋውቋቸው እና እንደሚያካፍሏቸው መማር ይችላሉ፡፡ ኢየሱስን ስለመከተላቸው እና ስላለመከተላቸው እርግጠኛ ስላልሆኑትም፣ ደቀ መዛሙርት ጊዜያቸውን በመስጠት የበለጠ ስለ እነዚህ ሰዎች ለማወቅ መማር ይችላሉ፡ ገና ባላገኘናቸውም ሰዎች አሻግረን እግዚአብሔርን መንግሥት ያልደረሰችበትን አካባቢ መመልከት እንችላለን፡፡ እኛ ልናገኛቸው ከምንችላቸው ሰዎች ውጪ ያሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች አናውቃቸውም፡፡ ነገር ግን አዘውትረን "እንዴት አደራችሁ" ከማለት የዘለለ ቅርበት የሌለን በመንገድ የምናያቸው የንግድ ሰዎች እና ሴቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በየመንደሩ ያሉ እንግዶችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ገና ያላየናቸው ከተሞች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ኢየሱስ ያለው ይህንን ነው፡ "አሕዛብን ሁሉ … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፡፡" ኢየሱስ ያለው ይህ ነው፤ ስለ እኔ ለማንኛውም ሰው ንገሩ፡- "በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ… ።" ለምናውቃቸው ሰዎች የተማርነውን ማካፈል የእግዚአብሔር ታሪክ የሚጓዝበት ፈጣኑ መንገድ ነው፡፡ የተማርነውን ከማናውቃቸው ሰዎች ጋር መከፋፈልም የእግዚአብሔር ታሪክ ሩቅ መንገድ እንዲሄድ የምናደርግበት ነው፡፡ የማናውቃቸውን ሰዎች የምንወድድ እና ስለእነርሱም ግድ የሚለን ከሆነ ይህ ተፈጥሮአዊ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አናውቃቸውም፡፡ እንዲህ አይነቱ ልምምድ ሲገጥመን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነገር ነው፡፡ እርሱም መንፈስ ቅዱስ በህይወታችን በሥራ ላይ እንዳለ ማረጋገጫ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጽኑ ፍላጎት ለተጣሉት፣ በሕይወት ደረጃ የመጨረሻ ታችኛው ረድፍ ላይ ላሉት እና ለጠፉት ነው፡፡ ልቡ ያለማቋረጥ አሁንም አሁንም በፍቅር የሚንሰፈሰፈው ስለ እነዚህ ሰዎች ነው፡፡ የእግዚብሔር አይነት በፍቅር የሚቃጠል ልብ እንዲኖረን የምንፈልግ ከሆነ፣ ሕይወታችንን መስጠት እና ያለንን ሁሉ ማፍሰስ ያለብን በእነዚህ ሰዎች ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚያዘን እንድንሄድ ነው፡፡ የመሄዳችን ከፊል መልክም ወደምናውቃቸው ሰዎች ብቻ መሄድ አይደለም፤ ይልቁንም እኛ ወደማናውቃቸው እና በሌላ የዓለም ጥግ በጨለማ ውስጥ ወደሚኖሩ ሰዎች ነው፤ እነዚህም ምናልባት የኢየሱስን ስም ከናካቴውም - በፍጹም ሰምተው የማያውቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው፣ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታይ ታዲያ እኛም የሰጠንን ጸጋ በሰጠን ሁኔታ ለትሁታን፣ ተስፋ ለቆረጡት እና ለጠፉት መስጠት ይገባናል፡፡ ደቀ መዛሙርት እግዚአብሔር በሕይወታቸው ውስጥ ስላስቀመጠው ሰዎች ማሰብ ሲችሉ ይበዛሉ፡፡ ደቀ መዛሙርት እግዚአብሔር በእነርሱ ዙሪያ በቅርበት ስላላስቀመጣቸው ሰዎች ሲያስቡም ይበዛሉ፡፡ ምክንያቱም አስበው እና አቅደው ወደ እነዚህ ሰዎች እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ደቀ መዛሙርት ለሌሎች ያላቸውን የያገባኛል ስሜት እንዲጨምሩ እና እንዴት እንደሚባዙ የሚረዱበትን ሥልጠና ትንሽ እቅድ በማውጣት እግዚአብሔር አስቀድሞ ወንጌልን እንዲሰሙ ያዘጋጃቸውን ሰዎች እንዲፈልጉ ሊረዷቸው ይችላሉ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ወደ ቤትም ስትገቡ እግዚአብሔር ይህን ቤት በሰላም ይባርክ ብላችሁ ሰላምታ ስጡ፤ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ።" ሰዎቹ ሰላም ወዳድ ከሆኑ በሰላም ይባረካሉ ሰላም ወዳዶች ካልሆኑ ደግሞ ሰላማችሁ ይመለስላችኋል፡፡ አስቀድሞ እግዚአብሔር ለመስማት ያዘጋጀውን ሰው የሰላም ሰው እንለዋለን፤ እንዲህ ያለው ሰው ለእግዚአብሔር መልዕክት ምላሽ የሚሰጥ ነው፤ መልዕክቱንም ለሌሎች ለማካፈል ታማኝ እና ታዛዥ ነው፡፡ የአካባቢውን ሰው ብዙም በማናውቅበት ስፍራዎች ለጓደኞቻችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ አብረውን ለሚሠሩትና ለክፍል ጓደኞቻችን ወንጌልን ከማካፈል ይልቅ አካባቢውን ለመድረስ የሰላምን ሰው ማሰልጠን የተሻለ ነው፡፡ የበለጠ ፍሬኣማ የሚያደርገን ግን ታማኝ በሆኑ ሰዎች ላይ ስናተኩር ነው፡፡ አስታውሱ ታማኝነት እግዚአብሔር የሚለንን በመታዘዝ እንዲሁም ለሌሎች በማካፈል የሚገለጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ታዘው የተማሩትን የሚያካፍሉ ሰዎች ኢየሱስ በምሳሌው እንዳነሳው ያሉ መልካም መሬቶች ናቸው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ጥቂት ዘርን በመልካም መሬት የዘሩ፣ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ በተገቢው መንገድ እንደዘራነው መጠን አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።" • ታማኝ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የማይቀበል ጠንካራ ልብ የላቸውም፡፡ • ታማኝ ሰዎች በስደት ወይም ወቅቱ በከፋ ጊዜ ወደኋላ የሚንሸራተቱ አይደሉም፡፡ • ታማኝ ሰዎች በዚህ ዓለም ጭንቀት ወይም ታይቶ በሚጠፋው ሃብት አይረበሹም፡፡ • ታማኝ ሰዎች ኢየሱስ ባዘዘው መሠረት የእግዚአብሔርን ታሪክ ለሌሎች እንዳካፈለው በጌርጌሴኖን ከአጋንንት እስራት እንደፈታው ሰው ታዛዦች ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ አንድ ታማኝ ሰው ኢየሱስን የበለጠ ለማወቅ የሚጓጉ እና የሚናፍቁ ሌሎች ሰዎችን ያፈራል፡፡ ዓይናችንን ከፍተን የእግዚአብሔር መንግሥት የሌለችበትን ሥፍራ መመልከት እና የምናውቃቸውን ወይም የማናውቃቸውን ሰዎች መድረስ ደቀ መዛሙርት የተባዙበት መንገድ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም መንግሥት በስፋት እና በፍጥነት ያደገበትም ነው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ከማን ጋር መካፈል የበለጠ ምቾት ይሰማችኋል -- አስቀድማችሁ የምታውቋቸውን ሰዎች ወይም እስካሁን ያላገኛችኋቸውን ሰዎች?
  2. ለምን የሆነ ይመስላችኋል?
  3. ብዙም ምቾት የማይሰማችሁን ነገር ለሰዎች በመናገር መሻሻል የምትችሉት እንዴት ነው?

READ

(5 min)

የጌታ እራት እና እንዴት አንዲከናወን ማድረግ እንደሚቻል

Zume Toolkit የጌታ እራት ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው፡፡" ቅዱስ ቁርባን ወይም "የጌታ እራት" ከኢየሱስ ጋር ያለንን የቀረበ ግንኙነት እና ቀጣይነት ያለውን ኅብረት የምናከብርበት መንገድ ነው፡፡ ይህንን መታሰቢያ በቀጣዩ ሁኔታ ቀለል ባለ መልክ ልናከብረው እንችላለን፡- እንደ ኢየሱስ ተከታዮች ስንሰበሰብ፣ ለጸጥታ እና ለጥሞና ጊዜ እንውሰድ፤ በዚያ ጸጥታም ኃጢአታችንን እያሰብን እንናዘዝ፡፡ አንድ ሰው ደግሞ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያንብብ፡- "ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህም ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።" 1ኛ ቆሮንቶስ 11:23-24) በምትሰበሰቡ ጊዜ ለኅብረታችሁ የለያችሁትን ኅብስት አስተላልፉ እና ተመገቡ፡፡ ንባባችሁን በመቀጠልም፣ "እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።" (1ኛ ቆሮንቶስ 11:25) ለኅብረታችሁ የለያችሁትን ወይን ተከፋፈሉ እና ጠጡ፡፡ ንባባችሁን ለመፈጸምም ቀጥላችሁ ይህን ክፍል አንብቡ፡- "ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።" (1ኛ ቆሮንቶስ 11:26) በጌታ እራት ተካፍላችኋል፡፡ በጸሎት ወይም በዝማሬ አክብሩት፤ እናንተ የእርሱ እርሱም የእናንተ ሆኗል! የጌታ እራት የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሥርዓት ነው፤ እንዲሁም በZume የመሣሪያዎች ቋት ውስጥ አንዱ አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡

ልምምድ

(10 min)

የጌታ እራት

የQR ኮድን ቃኙ።

ቀጣዮቹን 10 ደቂቃዎች ከቡድናችሁ ጋር የጌታን እራት በማክበር አሳልፉ።

እንደ ኢየሱስ ተከታዮች በምትሰበሰቡበት ጊዜ፦

1. በጸጥታ በማሰላሰል፣ በጸጥታ በማሰብና ኃጢአታችሁን በመናዘዝ ጊዜ አሳልፍ።
2. ዝግጁ ስትሆኑ፣ አንድ ሰው የሚከተለው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ያንብብ -- እኔ ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ ዐልፎ በተሰጠባት ሌሊት እንጀራን አንሥቶ ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ "ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት" አለ። (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥23-24)
3. ለቡድናችሁ ያዘጋጃችሁትን እንጀራ አቅርቡና ተመገቡ።
4. ማንበብ ቀጥሉ -- እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፣ ‹‹ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ ከጽዋው በምትጠጡበት ጊዜ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት›› አለ። (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥25)
5. ለቡድናችሁ ያዘጋጃችሁትን ጭማቂ ወይም ወይን አካፍሉና ጠጡ።
6. ንባቡን ጨርሱ፦ ይህን እንጀራ በምትበሉበት ጊዜ፣ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ። (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥26)

በጸሎት ወይም በመዝሙር እግዚአብሔርን አክብሩ። በጌታ እራት ተካፍላችኋል። እናንተ የእርሱ ናችሁ እርሱም የናንተ ነው!

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • ጅምር (እንደ ትንሽ ዳክዬ ያለ) ደቀ መዝሙርነት – ወዲያውኑ መምራት
  • መንግሥቱ የሌለበትን የሚመለከቱ አይኖች
  • የጌታ እራት እና እንዴት አንዲከናወን ማድረግ እንደሚቻል

NEXT STEP

ታዘዙ

ቤተሰባችሁ አማኞች ከሆኑ እና በአካባቢው የሚኖሩ ከሆነ፣ የጌታን እራት አብራችኋቸው ምሩ። አለበለዚያ፣ ክህሎቱን ከአማኝ ጓደኛ ጋር ተለማመዱ።

አካፍሉ

ጌታ ወደ ልባችሁ ለሚያመጣቸው ሰዎች ሰዎች ሁሉ "ጅምር ደቀ መዝሙርነት" እና "መንግሥቱ የሌለበትን የሚመለከቱ አይኖች" አካፍሉ። ከዚያ ለሌላ ሰው ማካፈል እንዲችሉ አስታጥቁዋቸው።

ክፍለ ጊዜ 11

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 9434

ፀልዩ

(5 min)

በጸሎት መመላለስ እንቅስቃሴያችሁ ላይ ከመውጣታችሁ በፊት አብራችሁ ጊዜያችሁን ለመዝጊያ ከቡድናችሁ ጋር መጸለይን ያረጋግጡ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • በጸሎት መመላለስ እና እንዴት ማድረግ እንደሚቻል

READ

(5 min)

በፀሎት መመላለስ

Zume Toolkit የጉዞ ጸሎት የእግዚአብሔር ቃል እንደዚህ ይላል፡- "እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።" የጉዞ ጸሎት ስለሌሎች በመጸለይ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መፈጸሚያ ቀላል መንገድ ነው፡፡ የጉዞ ጸሎት ማለት በአጭሩ እየተጓዙ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ዓይናችንን በመጨፈን እና አንገታችንን ዝቅ በማድረግ ፋንታ፣ ዓይናችንን ከፍተን እና አካባቢያችንን እየቃኘን፣ በተሰበረ ልብ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ የምንለምንበት የጸሎት ዓይነት ነው፡፡ የጉዞ ጸሎትን ሁለት ወይም ሦስት በመሆን በቡድን ማድረግ ትችላላችሁ፤ ወይም ደግሞ በግላችሁም ልታደርጉት ትችላላችሁ፡፡ በቡድን ከወጣችሁ፣ የቡድኑ አባላት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲጸልዩ አድርጉ፤ ሁሉም በሚያየው እና እግዚአብሔር ወደ ልቡ እንዲያመጣው በሚፈልገው ነገር ላይ ከእግዚብሔር ጋር ንግግር ያድርግ፡፡ ለብቻችሁ የምትሄዱ ከሆነም፣ በጸጥታ ጸልዩ፤ ወይም በመንገዳችሁ አብሮኣችሁ የሚጸልይ በመንገድ ያጋጠማችሁ እንደሆነም፣ በሚሰማ ድምጽ ልትጸልዩ ትችላላችሁ፡፡ በጉዞ ጸሎታችሁ ወቅት የምትጸልዩበትን ነገር ልትረዱ የምትችሉባቸው አራት መንገዶች ከዚህ ቀጥሎ ተጠቅሰዋል፡- ምልከታ፡- ምን ታያላችሁ? በጉዟችሁ ላይ የልጅ አሻንጉሊት የምታዩ ከሆነ፣ ምናልባት ስለጎረቤታችሁ ልጆች ወይም ስለቤተሰቡ ወይም በአካባቢው ስላሉ ትምህርት ቤቶች የመጸለያ ሃሳብ መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥናት፡- ምን ታውቃላችሁ? ስለ ጉርብትና አንብባችሁ ከሆነ፣ ባነበባችሁት አካባቢ ስላሉ ሰዎች የተወሰነ ነገር፣ ለምሳሌ አካባቢው በወንጀል እና ፍትህ በማጣት ጉዳዮች እንደሚሰቃይ መገንዘብ ችላችኋል እንበል፤ ስለእነዚህ ሰዎች በመጸለይ የእግዚአብሔን ጣልቃ ገብነት እንጠይቃለን ማለት ነው፡፡ መገለጥ፡- መንፈስ ቅዱስ ልባችሁን በማነሳሳት ወይም ሃሳብ በልባችሁ በማምጣት አካባቢው በሚያስፈልገው ጉዳይ ላይ እንድትጸልዩ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ አዳምጡ እና ጸልዩ! ቅዱሳት መጻሕፍት፡- ለጉዞ ጸሎት ዝግጅት ስታደርጉ ወይም በጉዞ ጸሎት ላይ እያላችሁ የእግዚአብሔርን ቃል የተወሰነ ክፍል ልታነቡ ትችላላችሁ፤ መንፈስ ቅዱስም ቃሉን በልባችሁ ያበራል፡፡ የምታነቡት ክፍል ግን እንዴት በዚያ አካባቢ ሰዎች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ሊያደርግ እንደሚችል እንድትረዱ ጸልዩ፡፡ በጉዞ ጸሎት ወቅት አትኩሮት ልታደርጉባቸው የሚገቡ እና ተጽዕኖ ሊደረግባቸው የሚገቡ አምስት ክፍሎች እነዚህ ናቸው፡- መንግሥት፡- እንደ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፀረ-ሙስና ላሉ የመንግሥት ማዕከላት ወይም የሕግ አስፈጻሚ ተቋማት በዓላማ ጸልዩ፡፡ ስለአካባቢው ደኅንነት፣ ፍትህ እንዳይጓደል እንዲሁም መሪዎች ከእግዚአብሔር በሆነ ጥበብ እንዲሠሩ ጸልዩ፡፡ ከእግዚአብሔር በሆነ ጥበብ እንዲሠሩ ጸልዩ፡፡ ብዙ ብር የሚንቀሳቀስባቸውን እንደ ንግድ ማዕከላት እና የሽያጭ ቦታዎች ያሉትን አስባችሁ ጸልዩ፡፡ የሃብቱ ፈሰስ የተቀደሰ እንዲሆን እና የሚያስተዳድሩ ሰዎች በባለአደራነት እንዲያስተዳድሩ ጸልዩ፡፡ ስለ ምጣኔ ሃብታዊ ክፍፍል ፍትሃዊነት እና ባለሃብቶች ከገንዘብ ትርፍ ይልቅ የሰው ልጆችን በክብር የሚያዩ በንጽህና በልግስና የሚሰጡ እንዲሆኑም ጸልዩ፡፡ ትምህርት፡- እንደ ትምህርት ማዕከላት እና የትምህርት አስተዳደር ህንጻዎች፣ እንደ ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ እንደ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ያሉትን የትምህርት ተቋማት አስባችሁ ጸልዩ፡፡ ትጉህ መምህራን እንዲኖራቸው እና የእግዚአብሔርን እውነት በተማሪዎቻቸው አእምሮ እንዲያሰርጹ እንዲሁም የተማሪዎች አእምሮ እንዲጠበቅ ጸልዩ፡፡ የትኛውንም ዓይነት ውሸት እና ግራ ማጋባት እንዳይዘሩ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባም ጸልዩ፡፡ እነዚህ ሥፍራዎች የእግዚአብሔር ልብ ያላቸውን መሪ ዜጎችን የሚያፈሩ እንዲሆኑም ጸልዩ፡፡ ብዙሃን መገናኛ፡- በሬድዮ፣ ቴሌቪዥን እና ጋዜጣ ዝግጅት ላይ የተሠማሩን የብዙሃን መገናኛ ማዕከላትን አስባችሁም ጸልዩ፡፡ የእግዚአብሔር ታሪክ እና የተከታዮቹ ምስክርነቶች በከተሞች እና በዓለም ሁሉ የሚተላለፍባቸው እንዲሆኑም ጸልዩ፡፡ በእነዚህ የሰዎች ለሰዎች ግንኙነት መሣሪያዎች የእግዚአብሔር መልዕክት ለብዙዎች እንዲተላለፍ እና ሰዎች በሥራ ሥፍራዎች ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲመለከቱ ጸልዩ፡፡ መንፈሳዊነት፡- እንደ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎች፣ መስጊዶች እና እንደ ቤተ መቅደሶች ላሉ የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መካሄጃ ማዕከላትን አስባችሁ ጸልዩ፡፡ መንፈሳዊ እውነትን ፈላጊዎች በኢየሱስ ያለውን ሰላም እና መጽናናት እንዲያገኙ እና በውሸት የሃይማኖት አሠራሮች ካለው ግራ መጋባት እና ተስፋ መቁረጥ እንዲወጡም ጸልዩ፡፡ በመጨረሻም፣ በጉዞ ጸሎት ወቅት ስለምታገኟቸው ሰዎች የምትጸልዩባቸውን አምስት መንገዶች ተመልከቱ፦ እየተጓዛችሁ ስትጸልዩ እድሎችን ልብ በሉ፤ ከፊታችሁ ለምታገኟቸው ሰዎች እና ቡድኖች መጸለይ እንድትችሉ ለእግዚአብሔር መንፈስ ጥቆማ የነቃችሁ ሁኑ፡፡ "ለማኅበረሰባችሁ እየጸለይን ነው፤ በተለየ ሁኔታ እንድንጸልይላችሁ የምትፈልጉት ጉዳይ ይኖር ይሆን?" ብላችሁም መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ ወይም ደግሞ "ስለዚህ አካባቢ እየጸለይኩ ነው፤ በተለየ ሁኔታ እንዲጸለይበት የምትፈልገው/ የምትፈልጊው ነገር ይኖር ይሆን?" በማለትም መጠየቅ ይቻላል፡፡ ምላሻቸውን ከሰማችሁ በኋላም ምላሹን የሰጠውን በተለየ ሁኔታ የሚያስፈልገው የጸሎት ጥያቄ ካለ ጠይቁ፡፡ የጸሎት ጥያቄ ካለ፣ ወዲያውኑ ጸልዩላቸው፡፡ እግዚአብሔር ከመራችሁም ስለሌሎች ጉዳዮችም መጸለይ ትችላላችሁ፡፡ ልትጸልዩ የምትችሉባቸውን 5 መንገዶች ለማስታወስም አ.ገ.ስ.ማ.መ. የሚለውን ቃል አስቡ፡- አካላዊ [ጤና] ገቢራዊ [የገቢ ምንጭ የሚያገኙበት ሥራ እና ገንዘብ] ስሜታዊ [ተነሳሽነት] ማኅበራዊ [ግንኙነቶች] መንፈሳዊ በብዙ አጋጣሚዎች እንዳየሁት ሰዎች እንደምታስቡላቸው እና እንደምትጸልዩላቸው ሲረዱ ይደሰታሉ፡፡ የሚጸለይለት ሰው ክርስቲያን ካልሆነ/ካልሆነች፣ እንደምትጸልዩላቸው መግለጻችሁ በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ መንገድ ከፋች ይሆናል፡፡ ይህም ደግሞ ታሪካችሁን እና የእግዚአብሔርን ታሪክ ለማካፈል እድል ይሰጣል፡፡ እነዚህን ሰዎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድናችሁ ወይም ወደ ቤታቸው ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፡፡ የሚጸለይለት ሰው ክርስቲያንም ከሆነ ወደ ጉዞ ጸሎት ቡድናችሁ ልትጋብዙት ወይም እንዴት የጉዞ ጸሎት ማድረግ እንደሚቻል ልታሰለጥኑት ትችላላችሁ፡፡ በዚህም በቀላሉ በማኅበረሰቡ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ሥፍራዎች ላይ መጸለይን ወይም ከላይ የተመለከትነውን የአ.ገ.ስ.ማ.መ.ን የጸሎት መርህ በመከተል የእግዚአብሔርን ቤት የበለጠ ስለማሳደግ ልታሰለጥኑ ትችላላችሁ፡፡ የጉዞ ጸሎት በZume የመሣሪያዎች ቋት ውስጥ ካሉ ቀላል መሣሪዎች አንዱ ነው፡፡

ልምምድ

(90 min)

በፀሎት መመላለስ

የQR ኮድን ቃኙ።

በሁለት ወይም በሦስት ቡድን ተከፍላችሁ ወደ ማህበረሰቡ ውጡና በጸሎት መመላለስን ተለማመዱ።

ቦታን መምረጥ አሁን ካላችሁበት ወደ ውጭ መራመድን ያህል ቀላል ሊሆን ይችላል ወይም ወደ አንድ የተወሰነ መድረሻ ለመሄድ ማቀድ ትችላላችሁ።

እግዚአብሔር እንደሚመራችሁ ሂዱና በዚህ ተግባር ከ60-90 ደቂቃዎችን ለማሳለፍ አቅዱ።

ይህ ክፍለ ጊዜ የሚጠናቀቀው በጸሎት በመመላለስ እንቅስቃሴ ነው።

ጸሎታችሁን ሊመሩ የሚችሉ አራት ግብዓቶች፦

1. ምልከታ ምን አያችሁ? የልጅ መጫወቻ በጓሮ ውስጥ ከተመለከታችሁ፣ ለሰፈሩ ልጆች፣ ለቤተሰቦች ወይም በሰፈሩ ውስጥ ላሉ ትምህርት ቤቶች ለመጸለይ ልትነሳሱ ትችላላችሁ።
2. ምርምር ምን ታውቃላችሁ? ስለ ሰፈሩ ካነበባችሁ፣ በውስጡ ስለሚኖሩ ሰዎች ወይም ሰፈሩ በወንጀል ወይም በፍትሕ መጓደል የሚቸገር ከሆነ ስለ የሆነ ነገር ልታውቁ ትችላላችሁ። ስለ እነዚህ ነገሮች ጸልዩና እግዚአብሔር እንዲሰራ ጠይቁት።
3. መገለጥ መንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ሊነካ ወይም ለአንድ ልዩ የጸሎት ፍላጎት ወይም ርዕስ ሀሳብን ወደ አእምሮአችሁ ሊያመጣ ይችላል። አዳምጡ ከዚያም ጸልዩ!
4. ቅዱሳት መጻሕፍት ለመራመድ ስትዘጋጁ ወይም ስትራመዱ የእግዚአብሔርን ቃል በከፊል አንብባችሁ ሊሆን ይችላል፣ መንፈስ ቅዱስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ሀሳቦች ሊመጣላችሁ ይችላል። ስለዚህ ምንባብ እና በዚያ አካባቢ ያሉትን ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥር ጸልዩ።

በጸሎት ላይ ትኩረት መድረግ ያለባቸው አምስት የተፅዕኖ ዘርፎች፦

1. መንግስት እንደ ፍርድ ቤቶች፣ የኮሚሽን ህንፃዎች ወይም የህግ አስከባሪ ቢሮዎች ባሉ የመንግስት ማዕከላት አስቡና ጸልዩ። ለአካባቢው ጥበቃ፣ ለፍትህና ለመሪዎቹ መንፈሳዊ ጥበብ እንዲሰጥ ጸልዩ።
2. ** ቢዝነስ እና ንግድ እንደ የፋይናንሺያል ዲስትሪክቶች ወይም የመገበያያ ቦታዎች ያሉ የንግድ ማዕከላት አስቡና ጸልዩ። ለትክክለኛ ኢንቨስትመንቶች እና ለግብዓቶች ጥሩ ባለ አደራነት ጸልዩ። ለኢኮኖሚ ፍትህ እና ተጠቃሚነት እንዲሁም ከጥቅም ይልቅ ሰዎችን የሚያስቀድሙ ለጋስ እና ፈሪሃ እግዚአብሔር ሰጪዎች እንዲኖሩ ጸልዩ።
3.
ትምህርት እንደ ትምህርት ቤቶችና የአስተዳደር ህንጻዎች፣ የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ የማህበረሰብ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ባሉ የትምህርት ማዕከላት አስቡና ጸልዩ። በጽድቅ አስተማሪዎች የእግዚአብሔርን እውነት እንዲያስተምሩና የተማሪዎቻቸውን አእምሮ እንዲጠብቁ ጸልዩ። ሽንግልና ወይም ግራ መጋባትን ለማስፋፋት የሚደረገው ሁሉ እግዚአብሔር እንዲያስወግድ ጸልዩ። በእንደዚህ ቦታዎች ላይ ያላ ሰዎች ለማገልገልና ለመምራት አስተዋይ ዜጎችን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።
4.
መገናኛ እንደ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና የጋዜጣ አሳታሚዎች ያሉ የመገናኛ ማዕከላትን አስቡና ጸልዩ። የእግዚአብሔር ታሪክና የተከታዮቹ ምስክርነት በመላው ከተማና በአለም ዙሪያ ሁሉ እንዲሰራጭ ጸልዩ። መልዕክቱ በመገናኛው በኩል ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ እና በሁሉም ስፍራ ያሉ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያዩ ጸልዩ።
5.
መንፈሳዊነት** እንደ ቤተ ክርስቲያን ህንጻዎች፣ መስጊዶች ወይም ቤተ-መቅደሶች ባሉ መንፈሳዊ ማዕከሎች ተመልከቱና ጸልዩ። እያንዳንዱ መንፈሳዊ ፈላጊ በኢየሱስ ሰላም እና መጽናኛ እንዲያገኝ እና በየትኛውም ሐሰተኛ ሃይማኖት እንዳይረበሽ ወይም እንዳያደናግር ጸልዩለት።

ፀልዩ

(5 min)

በጸሎት መመላለስ እንቅስቃሴያችሁ ላይ ከመውጣታችሁ በፊት አብራችሁ ጊዜያችሁን ለመዝጊያ ከቡድናችሁ ጋር መጸለይን ያረጋግጡ።

የጠፋውን፣ የመጨረሻውን እና ትንሹን - እኛን ጨምሮ ስለሚወድ እግዚአብሔርን አመስግኑት!

በምትመላለሱበት ጊዜ ለስራው የተሰጣችሁ እንድትሆኑ ልባችሁን እና የምታገኗቸውን ሰዎች ልብ እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔርን ጠይቁት።

ክፍለ ጊዜ 12

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 2348

ፀልዩ

(5 min)

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ስላደረገው ነገር ወደ እግዚአብሔርን ጸልዩ እና አመስግኑት፣ ለመታዘዝ ከባድ ሲሆንባችሁ እንዲረዳችሁ ለምኑት፣ እና በጋራ ጊዜያችሁ እንዲመራችሁ እንዲመራ ቅዱስ መንፈሱን ጋብዙ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ, ይህንን ጽንሰ-ሐሳብ እንሰማለን እና እንነጋገራለን-

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የሰላም ሰው እና ይህንን ሰው እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
  • የBLESS ጸሎት ንድፍ

READ

(5 min)

የሰላም ሰው

ወደ ዙሜ ሥልጠና በድጋሚ እንኳን በሰላም መጣችሁ፡፡ ቀደም ባለው ክፍለ-ጊዜ "የሰላም ልጅ" ወይም የሰላም ሰው ከሚለው ሃሳብ ጋር ትውውቅ አድርጋችኋል፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜም ያ ሰው እና እንዴት ያለ እንደሆነ እንዲሁም መታወቂያዎቹ ምን ምን እንደሆኑ የበለጠ ጠለቅ ባለ መንገድ እንመለከተዋለን፡፡ የሰላም ሰው የኢየሱስ ተከታዮች ጥቂት በሆኑበት ወይም በቅርብ በሌሉበት ሁኔታም እንኳን ደቀ መዛሙርትን በማባዛት ረገድ ድጋፍ ሰጪ ሆኖ ሊከሰት ይችላል፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አማኞች ወደሌሉበት ግዛት ደቀ መዛሙርትን እንዲያፈሩ በላከ ጊዜ፣ ለማድረግ ቀላል የሆነ፣ ግን ደግሞ የከበረን ትዕዛዝ እንዲህ በማለት ሰጥቷቸዋል፡- "በብርም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ …በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ። ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል። በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።" ሆኖም ይህ ምን ማለት ነው? ደቀ መዛሙርትን ማፍራት ሲታሰብ በመጀመሪያ ደረጃ የሚታየው የበጀት - የገንዘብ ጉዳይ ነው፤ ጥሎም በተገቢው ሁኔታ የተቀመጠ ዝርዝር ግብ፣ እንዲሁም በግልጽ ሊተገበር የሚችል እቅድ መኖሩ ነው፡፡ ኢየሱስ "ሂዱ" ካለ ግን የሚሻለው መሄድ እና መሄዳችንንም መቀጠል ነው፡፡ ከዚያም ለሰው ልጅ ሁሉ፣ በየትኛውም ሥፍራና ጊዜ የምሥራቹን ወንጌል መናገር ነው፡፡ የኢየሱስን ትዕዛዝ ስናየው የለበጀት ወይም የብርን ጉዳይ ከግምት ያስገባ አይደለም፡፡ የትዕዛዙ ዋነኛ ማነጣጠሪያ ደቀ መሙዛርት ትኩረታቸውን ጠብቀው መሄዳቸው ነው፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ያስጠነቀቃቸው የሰላምን ሰው እንዲፈልጉ እና በእርሱም ላይ ያላቸውን መንፈሳዊ ሃብት ፈሰስ እንዲያደርጉ ነው፡፡ ብዙ አማኝ ወይም ከነአካቴው ምንም አማኝ በሌለበት ሁኔታ ደቀ መዛርትን ማፍራት ሲያስፈልግ በጣም ወሳኙ ነገር የሰላምን ሰው ፈልጎ ማግኘቱ ነው፡፡ ሰላም ሰው ታሪካችሁን እና የእግዚአብሔርን ታሪክ እንዲሁም የኢየሱስን የምሥራች ወንጌል ለመስማት የተከፈተ ልብ ያለው ሰው ነው፡፡ የሰላም ሰው ወደ ቤቱ ወይም ወደ ሥራ ሥፍራው በሄድን ጊዜ እንድንገባ ወይም በቤተሰቡ እና በጓደኞቹ መካከል እንድንቀላቀል በትሕትና የሚቀበል ዓይነት ሰው ነው፡፡ የሰላም ሰው ብዙ ሰዎችን የሚያውቅ ወይም በሰዎች ዘንድ የታወቀ ሰው ነው፡፡ የሰላም ሰው ሰዎችን በቡድን ወይም በጉባኤ ደረጃ ለመሰብሰብ እና ለማግኘት በደስታ የሚፈቅድ ነው፡፡ ሰላም ሰው ታማኝ እና የተማረውን ደቀ መዛሙርት ከአካባቢው ከሄዱም እንኳን በኋላ ለሌሎች ለማካፈል የታመነ ሰው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የሰላምን ሰው ባልተጠበቀ ሥፍራ እንዳገኙት እናነባለን፡፡ በጌርጌሴኖን የመቃብር ሥፍራ በርኩስ መንፈስ ተይዞ፣ በሰንሰለት ታስሮ ከሰዎች ተገልሎ የሚኖር ሰው አገኙ፡፡ ይህን ሰው በፍጹም እንደ ሰላም ሰው ልናስበው አንችልም፡፡ ይህ ሰው ግን ኢየሱስን ለመስማት ልቡ የተከፈተ ሆነ፡፡ በሚኖርበትም ሥፍራም ኢየሱስን እጆቹን ዘርግቶ ተቀብሎታል፡፡ በዚያ ጠበኛ እና ሰውን ለመጉዳት በተዘጋጀ ሁኔታውም ሆኖ እንኳን በሰዎች ዘንድ ታዋቂ እና በቀላሉም ሰዎችን በዙሪያው መሰብሰብ የሚችል ነበር፡፡ ኢየሱስም ይህን ሰው እንደ ታማኝ የሰላም ሰው ቆጠረው፡፡ የሰላምን ወንጌል ለቤተሰቦቹ፣ ለማኅበረሰቡ እና ለአገሩ ይሰብካል ብሎም አመነው፡፡ ኢየሱስ በሌላ ጊዜ ወደዚህ ሥፍራ በተመለሰ ጊዜም ይህም ሰው ታዲያብዙ ሰዎች ኢየሱስን በደስታ ለመስማት እንዲሰበሰቡ ማድረግ ችሏል፡፡ በሰማርያ የውሃ መቅጃ ጉድጓድ አጠገብ ኢየሱስ አንዲት ሳምራዊት ሴት አግኝቶ ነበር፡፡ ይህች ሴት የኢየሱስን የውሃ አጠጭኝ ጥያቄ ለመቀበል ልቧ የተከፈተ ነበር፡፡ ለመቀበል ልቧ የተከፈተ ነበር፡፡ ይህች ሴት ባሎች እንደነበሯት እና አሁን ግን ባሏ ካልሆነ ሰው ጋር በመኖር ላይ እንዳለችም እናነባለን፡፡ በዚህም ምክንያት የምትኖረው በትንሽ ከተማ እንደመሆኑ በሰዎች ዘንድ ትታወቅ እንደነበረች በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን፡፡ ኢየሱስ የተናገራትንም በፍጥነት ለብዙዎች ለመናገር የታመነች ሆና እናያታለን፡፡ ከእርሷ የተነሳም የሰማርያ መላው ሕዝብ ማለት ይቻላል ከእነርሱ ጋር እንዲሆን እና እንዲያስተምራቸው ጠይቀውታል፡፡ ኢየሱስም አስተምሯቸዋል፡፡ የሰላም ሰው በሁሉም ሥፍራ ሊኖር የሚችል፣ የትኛውንም ነገር እያደረገ ልናገኘው የምንችል፣ እና የትኛውም ሰው ሊሆን የሚችል ከሆነ፣ ታዲያ ይህን ሰው ልንለየው የምንችለው እንዴት ነው? ሦስት ቀላል መንገዶች አሉ፡- 1ኛ. ከማኅበረሰቡ አስተያየት ተቀብለን ልንለየው እንችላለን፤ በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ የተማነ የሚባለው ሰው ማነው? በማኅበረሰቡ ውስጥ ከራሱ ይልቅ ሌሎችን የሚያስቀድም ይኖር ይሆን? ለዚህ ጥያቄ እንደምላሽ በተዳጋጋሚ አንድ ዓይነት ስም የሰማን ከሆነ፣ ያን ሰው ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን፡፡ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን ሃሳብ በመንገር፣ ይህን እውነት ለመስማት ልቡ የተከፈተ እንደሆነ እና ይህንኑም ለሌሎች ለማካፈል ፈቃደኛ ስለመሆኑ እንመለከታለን፡፡ 2ኛ. አንድ ሰው እንዲጸልይ እንጋብዛለን፤ ወይም ደግሞ የጉዞ ጸሎት እንዲደረግ ወይም በሥራ ሥፍራ ወይም ደግሞ በጨዋታ መሃል እንደጸለይ እናደርጋለን፡፡ ያንንም ጸሎት የመንፈሳዊ ንግግር መክፈቻ በር እናደርገለን፡፡ በእያንዳንዱ ንግግራችንም ከመንፈሳዊ እውነት ሃሳቦች ጋር፤ እግዚአብሔር በሰው ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደሚሠራ እናስተዋውቀዋለን፡፡ እንዲሁም፣ 3ኛ. ለዚህ ሁኔታ ልቡ የተከፈተ እና ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነ፣ በዛ ባለ ሁኔታ ሰዎችን እንዲሰበስብ እና ሀሳቡን የበለጠ ለማስተዋወቅ እንጠይቀዋለን፡፡ ከሰዎች አስተያየት መቀበል፣ የጸሎት ግብዣ ማድረግ እና የወንጌልን እውነት ማስተዋወቅ ሁልጊዜም የሰላምን ሰው ለማግኘት መንደርደሪያችን ናቸው፡፡ የሰላምን ሰው በምንም ሁኔታ ልናግኘው እንችላለን፡፡ ልብ አድርጉ፣ ኢየሱስ እንዳለው ብዙውን ደቀ መዝሙር የማድረግ ጊዜያችንን የምናጠፋው በሰላም ሰው ላይ ነው፡፡ ለብዙ ሰዎች የተወሰነውን ጊዜያችንን በእኩል ሁኔታ ለመስጠት ማሰብ ቀላል ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው እና እንዳሳየውም በሁሉም ሰው ፊት የጠለቀውን ነገር ማቀረብ የለብንም፡፡ ለጥቂቶች ግን የጠለቀውን መንፈሳዊ እውነቶች ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች በኢየሱስ ዙሪያ ይሰበሰቡ ነበር፡፡ ይሁንና፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ እንደሚነግረን ኢየሱስ ራሱን ከዚህ የሰው ክምችት ያገልል ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜውንም ያጠፋ የነበረው የቅርቦቹ ከሆኑት ከ12ቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር ነበር፡፡ ኢየሱስ ከእነዚህም መርጦ ደግሞ ከሦስቱ ጋር ጊዜ ይወስድ የነበረው ብዙ ጊዜ ነበር፡፡ ኢየሱስ ብዙ ኃይል፣ ብዙ ጉልበት፣ ብዙ ሥልጣን፣ የሕይወት ሥርዓት፣ ጥበብ፣ እውቀት፣ ማስተዋል እና ርህራሔ እያለውም ብዙውን ጊዜውን ለማጥፋት የመረጠው ከጥቂቶቹ ጋር ነው፡፡ እንደ ደቀ መዛሙርት ተመሳሳይ ነገር እንድናደርግም ነው የነገረን፡፡ ይህንን ፍጹም የሆነውን የእርሱን መንገድ መከተሉ ትርጉም ይሰጥ ይሆን? የሰላምን ሰው ማግኘት እንዲህ ቀላል አይደለም፤ ምናልባትም ከሺዎች አንዱ ሰው ነው፡፡ ሆኖም እንዲህ ያለው ሰው የተደበቀ የእግዚአብሔር ሃብት ነው፡፡ ስለዚህም በብርቱ ሊፈለግ የተገባው ነው፡፡ እንዲህ ባለው ሰው በኩል ነው በምንም የማይተመነው የእግዚብሔር ቤተሰብ የሚያድገው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. አንድ ሰው “መጥፎ ዝና” ያለው (እንደ ሳምራዊቷ ሴት ወይም ጋኔን ያደረባት በጌርጌሴኖን) በእርግጥ የሰላም ሰው ሊሆን ይችላል? ለምን ወይም ለምንስ አይሆንም?
  2. ጥቂት (ወይም ምንም) የመንግሥቱ መገኘት ያለው የሚመስለው በአቅራቢያዎ ያለ ማህበረሰብ ወይም የህብረተሰብ ክፍል ምንድን ነው?
  3. የሰላም ሰው (ቀና፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ሌሎችን የሚያውቅ እና የሚያካፍል) የወንጌልን ስርጭትን በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊያፋጥን የሚችለው እንዴት ነው?

ልምምድ

(10 min)

የBLESS ጸሎት

የQR ኮድን ቃኙ።

በሁለት ወይም በሶስት ቡድን ተመድባችሁ አምስቱን የ B.L.E.S.S. ዘርፎችን መጸለይን ተለማመዱ። አንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ።

የBLESS ጸሎት ንድፍ

የBLESS ጸሎት ንድፍ በማንኛውም ጊዜ ለምታገኛቸው ሰዎች በተለይም በጸሎት ስትመላለሱ መጸለይ የምትችሉባቸውን አምስት መንገዶች ይሰጣችኋል።

  • አካል - ጤና
  • ጥረት - ሥራ እና ፋይናሶች
  • ስሜታዊ - ሞራል
  • ማህበራዊ - ግንኙነቶች
  • መንፈሳዊ - እግዚአብሔርን የበለጠ ማወቅና መውደድ

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው ሀሳብ፡-

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • የሰላም ሰው እና ይህንን ሰው እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
  • የBLESS ጸሎት ንድፍ

NEXT STEP

ታዘዙ

በዚህ ሳምንት የBLESSን ንድፍን በመጠቀም ለአንድ ሰው ባለበት ጸልዩ።

አካፍሉ

የBLESS ንድፍ በመጠቀም ሌላ ሰው ለሌሎች እንዲጸልይ አስታጥቁት እና ይህን እያደረገ እያለም አብራችሁት ሁኑ።

ክፍለ ጊዜ 13

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 6785

ፀልዩ

(5 min)

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ስለተማራችሁት ነገር ጸልዩ እና እግዚአብሔር አመስግኑት። የተማራችሁትን ሁሉ በተግባር ለማዋል ታማኝ እንድትሆኑ እንዲረዳችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲረዳችሁ ጸልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

  • ታማኝነት ከእውቀት ይልቃል
  • የ3/3 ቡድን ስብሰባ ንድፍ

READ

(5 min)

ታማኝነት

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ፣ ታማኝነት ከዕውቀት እና ከሥልጠና ይልቅ እጅግ የበለጠ የመንፈሳዊ ብስለት መለኪያ ስለመሆኑ እንማራለን፡፡ በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌለው ችግር የፈጠሩ ሁለት ጉዳዮች አሉ፤ እነርሱም፡- አንደኛው ነገር መንፈሳዊ ብስለት የሚለካው አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ባወቀበት ልክ መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች በትክክለኛው የእምነት ደረጃ ላይ እንዳሉ ተደርገው ይታሰባሉ፤ ይህም የአንድ ሰው አማኝነት ጥሩ መለኪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አንድ ሰው አገልግሎት ውስጥ ከመግባቱም በፊት ቢሆን ለመምራት ብቃቱ እንደ መለኪያ የሚቀመጠው "ሙሉ ሥልጠና" የወሰደ መሆኑ ነው፡፡ ሥልጠና ማግኘቱ እውቀቱን ፍጹም እንደሚያደርግለት መታሰቡ ነው፤ መሠልጠኑ እንደሚገባው የማገልገሉ ጥሩ መለኪያ ሆኖ መታሰቡ ነው፡፡ የመጀመሪያው ሃሳብ "ትክክለኛ እምነት" መምሰሉ ስህተት ነው፡፡ ሰይጣን ራሱም ቢሆን ከማንም ሰው በላይ የእግዚአብሔርን ቃል አዋቂ መሆኑ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል:- "እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።" የአንድ ሰው የተሻለው መንፈሳዊ ብስለት መለኪያ "ትክክለኛ ድርጊቱ እና ልምምዱ" ነው፡፡ ታማኝነትን ከእግዚአብሔር የተማረውን በመታዘዝ እና በማካፈል ፈንታ በምናውቀው ብቻ መለከታችን የበለጠ አሳሳቢ ነው፡፡ ከሁለተኛው ሃሳብ ጋር የተያያዘው ችግር ይህ ነው፡- ከመምራቱ በፊት እንደሚገባው የሰለጠነ መሆን ይገባዋል ብለን የምናስበው ማንም ሰው፣ ሙሉ በሙለ ሰለጠነ አወቀ የሚባል ፈጽሞ አለመኖሩ ነው፡፡ ኢየሱስም እንኳን ለተልዕኮ ያሰለፋቸው በወቅቱ ብዙ ነገሮች የነበራቸው ወጣት መሪዎች፣ ማለትም ደቀ መዛሙርቱ በመንግሥቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ገና ብዙ የሚማሩ ነበሩ፤ ይህን በማድረጉ በምሳሌ አሳይቷል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- "አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።" ልብ አድርጉ፣ እነዚህ ሰዎች እኛ እንደ እምነት መሠረት የምንቀበለውን ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ጴጥሮስ ለሌሎች ከመመስከሩ በፊት ነው ኢየሱስ የላካቸው፡፡ ለተልዕኮ ከላካቸውም በኋላ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ጴጥሮስን ስለስህተቱ ገስጾታል፡፡ ጴጥሮስም ቢሆን ኢየሱስን እስከመካድ ያለውን ፍጹም ስህተት ፈጽሟል፡፡ ሌሎቹም ደቀ መዛሙርት ቢሆኑ ከእነርሱ ማን ታላቅ እንደሆነ በመጪዋ የእግዚአብሔር መንግሥት ስለሚኖራቸው ሚናም ይከራከሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ገና ብዙ የሚማሩት ነገር ነበራቸው፤ ኢየሱስ ግን የሚያቁትን በማካፈል ሥራ ላይ አሠማራቸው፡፡ ታማኝነት አንድ ሰው ገና ኢየሱስን መከተል ሲጀምር ከዕውቀትም በላይ በሕይወቱ መታየት የሚጀምር ነገር ነው፡፡ ታማኝነት ከሥልጠናም በላይ በተሰጠን ነገር ምን እንዳደረግን የምንለካበት - የምንመዘንበት ነገር ነው፡፡ የሰማነውን ለሌሎች ለማካፈል ታዛዥ ከሆንን ታማኝ ነን፡፡ የሰማነውን ለማካፈል እምቢ ማለት ደግሞ ታማኝነትን ማጉደል ነው፡፡ ስለዚህ ደቀ መዛሙርትን ስናበዛ የምንለካውም ነገር ትክክለኛ ስለመሆኑ አረጋግጠን ሊሆን ይገባል፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. እስቲ አስቀድማችሁ የምታውቋቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አሰላስሉ። እነዚህን ነገሮች በመታዘዝ እና በማካፈል ላይ ምን ያህል "ታማኞች" ናችሁ?

READ

(5 min)

3/3 ቡድን ስብሰባ

Zume ስልጠና እንኳን ተመለሳችሁ። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የ3/3ኞች ቡድን የኢየሱስ ተከታዮች ይበልጥ ኢየሱስን በቅርበት ለመከተል አንዳቸውን ለአንዳቸው እንዲረዳዱ የሚያግዝ የስብሰባ ዘዴ የሆነው እንዴት እንደሆነ እንማራለን። ኢየሱስ እንዲህ አለ -- ‹‹ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።›› ያ ብርቱ ተስፋ ነው፣ እያንዳንዱ የኢየሱስ ተከታይ ሊጠቀምበት የሚገባም ነው። እንደ ቡድን ስትሰባሰቡ ግን ጊዜያችሁን እንዴት ልታሳልፉ ትችላላችሁ? የ3/3ኞች ቡድን ጌታ ኢየሱስ ያዘዛቸውን አንዳንድ በጣም ወሳኝ ነገሮችን መታዘዝ የሚለማመዱበትን የጋራ ጊዜያቸውን በ3 ክፍሎች የሚከፍል ነው። የሚሆነው እንዲህ ነው፦ የቡድኑ የመጀመሪያ ሲሶ ጊዜ የሚያልፈው አብረን ከሆንን ጀምሮ አንስቶ የሆነውን ወደ ኋላ በመመልከት ነው። የቡድኑ መካከለኛ ሲሶ ጊዜ የሚያልፈው በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በውይይት እና በጸሎት የእግዚአብሔርን ጥበብ እና ምሪትን በመፈለግ ነው። የቡድኑ የመጨረሻ ሲሶ ጊዜ የሚያልፈው እያንዳንዳችን የተማርነውን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እና መታዘዝ እንደምንችል ለማወቅ በመፈለግ ነው። በዚህ ክፍለ ጊዜ ቡድናችሁ በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ለሙሉ ስሪት ለማዘጋጀት እንዲረዳችሁ በ3/3ኞች ቡድን አጭር ስሪት በኩል ይመራል። በመንፈሳዊ አተነፋፈስ ላይ ያለውን ክፍለ-ጊዜ አስታወሳችሁ? አየር ሳቡ፣ ከእግዚአብሔር ስሙ። ወደ ውጭ ተንፍሱ፣ የሰማችሁትን ታዘዙ እናም ለሌሎች አካፍሉ። የ3/3ኞች ቡድን ማለት ይህ ነው። የ3/3ኞች ቡድን እግዚአብሔርን በመስማት መታዘዝ እንዲችሉና ኢየሱስ ያዘዛቸውን አንዳንድ በጣም ወሳኝ ነገሮች መታዘዝ እና ማካፈል እንዲችሉ አብረው የሚያሳልፉት ጊዜያቸውን በ3 ክፍሎች የሚከፍል ነው። ይህ የልምምድ ክፍለ-ጊዜ ከአንድ ሰዓት ጥቂት ለበለጠ ጊዜ ይቆያል እና በፍጥነት ያልፋል። ትልቅ ቡድን ወይም ጥልቅ ውይይቶችን ማከናወን የሚፈልጉ ቡድን ካላችሁ፣ ከቡድኑ አባላት ውስጥ አንዱ በሰዓት ወይም በሰዓት ቆጣሪ መከታተል ላይ እንዲረዳችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። በእውነተኛ ህይወት ውስጥ እነዚህ እርምጃዎች በእርጋታ ያልፋሉ፣ እየተለማመዳቹኋቸው እያላችሁ ግን ጊዜ እንዳይጣበብባችሁ መቀጠላችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ሁሉም አስፈላጊ ስለሆኑ ምንም አይነት እርምጃዎችን አትዝለሉ! 3/3ኞች ቡድን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር ተመሳሳይ እንዳልሆነ - ያም ታስቦ የተደረገ እንደሆነ አስታውሱ! የምትገናኙበት አዲስ መንገድ ለመማርና እግዚአብሔር በጋራ ለሚኖረን ጊዜ ምን መልካም ነገር እንዳቀደ ለመመልከት እንደ እድል ለመጠቀም ይህንን ተሞክሮ ሞክሩት። ለመቀጠል ዝግጁ ናችሁ? እስቲ እንጀምር! የመጀመሪያውን ሲሶ ጊዜያችንን ወደኋላ በመመልከት እርስ በእርሳችን በመተሳሰብ ምስጋናዎችን በመሰጣጠት፣ የሚያስቸግሩንን ነገሮች በማካፈልና ለሌሎች የቡድናችን አባላት በመጸለይ እናሳልፈዋለን። በቡድኑ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ለመጨረሻ ጊዜ አብረን በነበርንበት ወቀት የተማረውን የሚታዘዝበት እና የሚያካፍልበትን እድሉን ማግኘቱንም እንፈትሻለን። እርምጃ አንድ - ‹‹ምስጋናዎችን ስጡ።›› እያንዳንዱ ሰው የሚያመሰግንበትን ነገር የሚያካፍልበት የተወሰነ ጊዜ ይኑራችሁ። በዚህ ቪዲዮ ላይ ለአፍታ አቁም (pause) የሚለውን ተጫኑና አሁኑኑ አድርጉት… አሁንም እዛው ናችሁ? እባካችሁን፣ ቪዲዮውን ለአፍታ አቁማችሁ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔርን የምታመሰግኑበትን ነገር እንዲያካፍል እንፈልጋለን። ጨርሳችሁ ስትመለሱ እዚሁ እንጠብቃችኋለን። እርምጃ ሁለት - ‹‹የሚያስቸግሯችሁን ነገሮች ተናገሩ›› እና ‹‹እርስ በርስ ፀልዩ።›› አሁን በቡድናችሁ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው እየተቸገረበት ያለውን ነገር በአጭሩ ያካፍል። ስለሚያካፍለው ነገር ሌላ ሰው እንዲጸልይለት አድርጉ። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጫኑ፣ ከዚያ አካፍሉ እና ጸልዩ። እርምጃ ሦስት - "በቡድኑ ላይ ማተኮር።" በተገኛችሁ ቁጥር፣ ጊዜ ወስዳችሁ ለምን አብራችሁ እንደሆናችሁ - እግዚአብሔርን ለመውደድ፣ ሌሎችን ለመውደድ፣ ስለ ኢየሱስ ለማካፈል እና ሌሎችም እሱን እንዲካፍሉ ለመርዳት እንደሆነ ለማስታወስ ትፈልጋላችሁ። ቡድኑ ትኩረቱን በተልዕኮ ላይ እንዲያደርግ የሚያደርጉ በርካታ መንገዶች ቢኖሩም ለዚህ የልምምድ ክፍለ ጊዜ የሚሆነንን በማቴዎስ 22፥37-38 ላይ ያለውን ምንባብ አንድ ሰው ጮክ ብሎ ለቡድኑ ያንብብልን። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጫኑና አንብቡ። እርምጃ አራት - ‹‹ተፈትሾ መግባት።›› ይህ አንዳንድ ጊዜ ሊከብዱ የሚችሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ስለሚሆን አንዳንድ ቡድኖች መዝለል የሚፈልጉት ክፍል ነው። እባካችሁ አትዝለሉት። ኢየሱስ ተከታዮቹን ከባድ ጥያቄዎችን እስከመጠየቅ ያደረሰው መውደድ ነበረው። እንደ ኢየሱስ መሆን የምንፈልግ ከሆነ፣ ይህን ለማድረግ እርስ በርሳችን መዋደድ አለብን። በዚህ እርምጃ፣ በቡድኑ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው አብራችሁ ለመጨረሻ ጊዜ በነበራችሁበት ጊዜ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ሲጠይቀው የሰማውን ነገር መታዘዙን እንዲናገር ታደርጋላችሁ። በእያንዳንዱ የZume ክፍለ ጊዜ፣ እንድትታዘዙ፣ እንድታካፍሉና እንድትጸልዩ በጠይቅናችሁ ወደፊት የመመልከት እርምጃ እነዚህን ቁርጠኝነቶች ሞዴል አድርገናል። በተመሳሳዮቹ ቁርጠኝነቶች እንድትገቡ በምንጠይቅበት ወደኋላ የመመልከት እርምጃችን ተጠያቂነትን ሞዴል እናደርጋለን። በስልጠናው ላይ በእነዚህ እርምጃዎች ላይ በቂ ጊዜ ካላሳለፋችሁ፣ ይህ የምትጀምሩበት ጥሩ ጊዜ ነው። እግዚአብሔርን የመውደድ አንዱ አካል የሚነግረንን መታዘዝ ነው። እርስ በርስ መዋደድ ማለት አንድ ሰው ከእግዚአብሔር የሰማውን እንዲታዘዝ ማገዝ ማለት ነው። መዋደድ ማለት የአንድን ሰው ቁርጠኝነቶች ማክበር እና ፍቅርን ያለመሰሰት ማሳየት - ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ ማለት ነው። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጭናችሁ እያንዳንዱ ሰው የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲመልስ አድርጉ፦ እስካሁን የተማርከውን የታዘዝከው እንዴት ነው? ስለተማርከው ነገር ማንን አሰልጥነሃል? በቡድን አብረን ከሆንን ጊዜ አንስቶ ታሪክህን ወይም የእግዚአብሔርን ታሪክ ከማን ጋር ተካፍለሃል? የ3/3ኞች ቡድናችንን ወደኋላ መመልከትን ክፍል ስንጨርስ፣ ክፍለ ጊዜዎቻችሁ በተሻለ ሁኔታ እንዲከናወኑ የሚያግዝ ነገር እነሆ፦ ZUME የማሰልጠኛ ጠቃሚ ምክር አንዳንድ ጊዜ በቡድን ውስጥ ብዙ ጊዜ ማውራት የሚፈልግ እና የሚያወራ አንድ ሰው ሊኖር ይችላል። ይህ እንዲሆን አትፍቀዱ። በቡድኑ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ቦታ የሚሰጠው ነው፣ ሁሉም ሰው የሚያካፍልበት እድል ማግኘቱን አረጋግጡ። ሌሎች የመናገር እድል እያገኙ ካልሆነ፣ እያንዳንዱ ሰው መደመጥ እንዳለበት ብዙ እየተናገረ ያለውን ሰው በእርጋታ አስታውሱት። በጋራ በነበረን መካከለኛው ሲሶ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ እንድንረዳ ቡድናችንን እንዲመራ ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ እንጋብዘዋለን። የእግዚአብሔርን ዓላማ እና እቅድ በአፅንዖት ለመመርመርና ለመረዳት የሚረዳንን ምንባብ ከመጽሐፍ ቅዱስን ጮክ ብለን እናነባለን እናም እንደ ቡድን አንዳንድ ቀላል ጥያቄዎችን እንጠያየቃለን። እርምጃ አንድ - የእግዚአብሔር ቅዱሱ መንፈስ እንዲመራችሁ ጋብዙት ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ውሰዱ። ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉና በጥቂት ቃላት ተነጋገሩ። ልታነቡት ካሰባችሁት ምንባብ እንዲያስተምራችሁ መንፈስ ቅዱስን ለምኑት። ለአፍታ አቁም የሚለው ተጫኑና ጸልዩ። እርምጃ ሁለት - የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ እና ጥያቄዎችን ጠይቁ በቡድኑ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ አድርጉ። ለዚህ የልምምድ ክፍለ-ጊዜ፣ ሉቃስ 18፥9-14ን አንብቡ። አንብባችሁ ስትጨርሱ፣ እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ቡድኑ መመለስ ይኖርበታል፦ ከዚህ ምንባብ ምኑን ወደዳችሁት? ምን አዳጋች ወይም ለመገንዘብ የሚያስቸግር ሆኖ አገኛችሁት? በቡድናችሁ ውስጥ የቃል ተማሪዎች - ማለትም በሚገባ የማያነቡ ወይም በመስማት ብቻ መማርን የሚመርጡ ሰዎች ካሉ፣ ምንባቡን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ማንበባችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጭናችሁ ጥያቄዎቹን አንብቡና መልስ ስጡባቸው። አሁን ደግሞ ሌላኛው ሰው ተመሳሳዩን ምንባብ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲያነብና ቡድኑ ለእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ አድርጉ፦ ከዚህ ምንባብ ስለ ሰዎች ምን እንማራለን? ከዚህ ምንባብ ስለ እግዚአብሔር ምን እንማራለን? ከምንባቡ ባለመውጣትቀላል ማድረግዎን አስታውሱ! ያ የ3/3 ቡድኖችን ወደፊት የመመልከት ክፍል ማብቂያ ነው፤ ስለዚህ ክፍለ ጊዜዎቻችሁ በተሻለ ሁኔታ እንዲከናወኑ የሚያግዝ ነገር እነሆ፦ ZUME የማሰልጠኛ ጠቃሚ ምክር የእግዚአብሔርን ቃል በምታጠኑበት ጊዜ፣ ከሌሎች መጻሕፍት፣ አስተማሪዎች ወይም አመለካከቶች ይልቅ በቃሉ ላይ ብቻ አተኩሩ። ‹‹ይህ ምን ማለት ይመስላችኋል?›› ብላችሁ ከመጠየቅ ይልቅ፣ ‹‹ይህ ምንባብ ምን ይላል?›› ብላችሁ ጠይቁ። በቡድናችሁ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ማስተማር የሚወድ ከሆነ፣ ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስና እንከን የለሽ ቃል ቡድኑን እንደሚያስተምር በእርጋታ አሳስቡት። ሁላችንም አብረን ለመማር በዚሁ አለን። እና በውይይቱ ወቅት ለአፍታ ዝምታን አሊያም ቆም ማለትን አትፍሩ። እግዚአብሔር በጸጥታም እየሰራ ነው። በቃሉ ላይ ትኩረታችሁን ቀጥሉ፣ ከምንባቡ አትውጡ፣ የቀረውን እግዚአብሔር እንደሚያሟላ እመኑ። በጋራ ጊዜያችን የመጨረሻው ሲሶ ላይ ከእግዚአብሔር ቃል በተማርነው እንዴት መታዘዝ እና ሌሎችን ማሰልጠን እንደምንችል ለማወቅ ወደፊት መመልከት ላይ እናተኩራለን። እያንዳንዱ የቡድኑ አባል እግዚአብሔርን ጥቂት ቀላል ጥያቄዎች ይጠይቃል እና ከዚያም መልሱን በጸሎት ይጠባበቃል። ቀጥሎ ቁርጠኝነቶቻችንን እንካፈላለን እንዲሁም እንለማመዳለን፣ ከዚያ የጋራ ጊዜያችንን ለማገባደድ እንጸልያለን። እርምጃ 1 - ስለ እግዚአብሔር ዓላማ መጸለይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው በለሆሳስ እንዲጸልይና እግዚአብሔርን እነዚህን ጥያቄዎች እንዲጠይቅ አድርጉ፦ እግዚአብሔር ሆይ፣ የምታስተምረኝን ልታዘዝ እና ተግባራዊ ላደርግ የምችለው እንዴት ነው? ከዚህ ምንባብ አንተን መታዘዝ እና መውደድ እንዲማር ማንን ማሰልጠን እችላለሁ? ምስክርነቴን ወይም የኢየሱስን ምሥራች ለማን እንዳካፍል ትፈልጋለህ? ለአፍታ አቁም የሚለው ተጫኑና ጸልዩ። የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቀጥተኛ መልሶችን፣ ቀጥተኛ ስሞችን እና ቀጥተኛ እርምጃዎችን በአሁን ጊዜ እና ቡድናችሁ እንደገና በሚገናኝበት ጊዜ እንዲሰጣችሁ ጠይቁ። እርምጃ 2 - ቁርጠኝነቶች ማሰባሰብ በቡድናችሁ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ሰው የሚከተለውን ጠይቁ o ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከጌታ የሰማውን እንዲያካፍል። የሆነ ሰው በአንዱ፣ በሁለቱም ወይም በሶስቱም ጥያቄዎች ላይ ከጌታ ምንም ነገር አልሰማ ይሆናል። ምንም እንዳልሰሙ በቀላሉ ሊናገሩ ይችላሉ። ቢሆንም ቡድኑ ከጌታ መስማት እንዳለበት አስታውሱ። ኢየሱስ እንዲህ አለ - ‹‹በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ።›› እና ለመታዘዝ የምታደርጓቸው እርምጃዎቻችሁ ይበልጥ ግልፅ በሆኑ መጠን፣ እንደገና ከመገናኘታችን በፊት የመታዘዛችሁ ነገር ይበልጥ የቀለለ ይሆናል። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጫኑና ከዚያ የሰማችሁትን አካፍሉ። እርምጃ 3 - እቅዳችሁን መለማመድ የጋራ ጊዜያችሁን ከማጠናቀቃችሁ በፊት የ3/3ኞች ቡድናችሁ በሁለት ወይም በሦስት አነስተኛ ቡድኖች እንዲከፋፈል እና ጌታ እንዲያደርግለት ሲጠይቅ የሰማውን እንዲለማመድ ያድርጉ። አስታውሱ - ልምምድ ማለት መታዘዝ፣ ማሰልጠን ወይም ማካፈል አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ዝግጁ መሆን እንጂ። እያንዳንዱ አነስተኛ ቡድን የጋራ የልምምድ ጊዜውን በጸሎት እንዲያጠናቅቅ ያድርጉ። እግዚአብሔር በልባችሁ ላይ ላስቀመጣቸው ሰዎች እና እቅዶቻቸው ጸልዩ። በቡድኑ ውስጥ የቃል ተማሪዎች ካሏችሁ፣ ቀደም ብላችሁን ያነበባችሁትን የእግዚአብሔር ቃል ምንባብ እንደገና የምታነቡበትን የልምምድ ጊዜያችሁን መድቡ። ይህም ጊዜ መላው ቡድን በስብሰባዎች መካከል ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ለመካፈል ዝግጁ እንዲሆን ይረዳዋል። ለአፍታ አቁም የሚለውን ተጫኑና ለመለማመድ እና ለመጸለይ በቡድን ተከፋፈሉ። ልዩ ቁርጠኝቶች የሌሉት ማንኛውም ሰው የምስክርነት ታሪኩን ወይም የእግዚአብሔርን ታሪክ ማካፈልን መለማመድ ይኖርበታል። ቡድናችሁን እያሰባሰባችሁ እያለ፣ ለመደሰት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ። ወደፊት መመልከት የሚለውን ክፍል አጠናቅቃችኋል እና አሁን ሁሉንም የ3/3ኞች ቡድን ቅርጸት ተለማምዳችኋል። ቡድናችሁ በቀጣይ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ያለዚህ የቪዲዮ መመሪያ ልምምዱን ይቀጥላል። ሌሎችም ሰዎች ቡድኑን በሂደቱ ውስጥ እንዲመሩ ተራ እንዲያገኙ መፍቀዳችሁን እርግጠኛ ሁኑ። የግድ ተሰጥኦ ያለው አስተማሪ መሆን አያስፈልጋችሁም፣ እነዚህን ቀላል እርምጃዎች ብቻ ተከተሉ። ወደ እርምጃዎቹ ከመቀጠላችሁ በፊት ክፍለ ጊዜዎቻችሁ ይበልጥ የተሳለጡ እንዲሆኑ ለማገዝ አንድ ተጨማሪ ጥቆማ እነሆ፦ ZUME የማሰልጠኛ ጠቃሚ ምክር በመላው አለም ዙሪያ፣ 3/3ኞች ቡድኖች አብረው በሚያሳልፉበት ጊዜ የጌታን እራት ወይም ማዕድ እና ተጨማሪ አልፎ አልፎ የሚደረጉ ውይይቶችን ይካፈላሉ። እግዚአብሔር እንድንጠነክር፣ እንዲያበረታን እና ልጁን፣ ኢየሱስን እንድንመስል እንድናድግ በአላማ መማር እና እድገት እና በአላማ መኖር እና ግንኙነት ያለበትን ይህን አይነቱን ህብረት ሰጥቶናል። እና ህብረቱ ይኸው ነው - ቡድናችሁ አሁን ሶስቱን ክፍሎች ተለማምዷል -- ለመጨረሻ ጊዜ ከተገናኘንበት ጊዜ አንስቶ ያሳካናቸውን ጉዳዮች ለመቃኘት ወደ ኋላ መመልከት፣ በዚህ ጊዜ አብረን እንድንማር እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን ነገር ለመረዳት ወደ ላይ መመልከት፣ እና አብረን ባልነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በልባችን ላይ ያስቀመጠውን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ወደፊት መመልከት። 3/3 ቡድኖች ኢየሱስን እንድንመስል የሚያግዘን ቀላልና ተግባራዊ የመገናኛ ዘዴ ናቸው።

ተወያዩ

(10 min)

  1. ከዚህ ቀደም አባል በነበራችሁበት (ወይም በሰማችሁት) በ3/3 ቡድን እና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአነስተኛ ቡድን መካከል መካከል ልዩነት እንዳለ አስተውላችኋል? አስተውላችሁ ከሆነ፣ እነዚህ ልዩነቶች በቡድኑ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ምንድነው?
  2. 3/3 ቡድን ቀላል ቤተክርስቲያን ተደርጎ ሊወሰድ ይችላልን? ለምን ወይም ለምንስ አይሆንም?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

  • ታማኝነት ከእውቀት ይልቃል
  • የ3/3 ቡድን ስብሰባ ንድፍ

NEXT STEP

ታዘዙ

በ3/3 የቡድን ልምምዳችሁ ወቅት በገባችሁት ቁርጠኝነቶች መሰረት በዚህ ሳምንት በመታዘዝ፣ በማሰልጠን እና በማካፈል ጊዜ አሳልፉ።

አካፍሉ

ቡድናችሁ እንደገና ከመገናኘቱ በፊት 3/3 የቡድን ቅርጸት እንዲያካፍሉ ይፈልጋልና ወደ እግዚአብሔርን ጸልዩ እና ጠይቁት። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 14

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 9872

ፀልዩ

(5 min)

ቡድኑ ኢየሱስን በታማኝነት ለመከተል ስላደረገው ቁርጠኝነት እግዚአብሔርን አመስግኑት እና የአብሮነት ጊዜያችሁን እንዲመራ መንፈስ ቅዱስን ጋብዙ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

ልምምድ

(45 min)

3/3 ቡድን ስብሰባ

የQR ኮድን ቃኙ።

ወደኋላ ተመልከት - እርስ በእርስ ክትትል ለማድረግ ያለፈውን ክፍለ ጊዜን ታዘዝ፣ ሰልጥን እና አካፍል ጥያቄዎችን ተጠቀሙ። (15 ደቂቃ)

ወደላይ ተመልከት - ማርቆስ 5፥1-20ን እንደ የቡድናችሁ የንባብ ክፍል ተጠቀማችሁ በወደላይ ተመልከቱ ክፍል ውስጥ ከ1-4 ያሉ ጥያቄዎችን መልሱ። (15 ደቂቃ)

ወደፊት ተመልከት - የምትታዘዙበትን፣ የምታሰለጥኑበትን እና የምታካፍሉበትን መንገድ ለማዳበር ወደፊት ተመልከት በሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች 5፣ 6 እና 7 ተጠቀሙ። (15 ደቂቃ)

ወደኋላ መመልከት

እርምጃ 1 - ምስጋናዎችን ስጡ

እያንዳንዱ ሰው የሚያመሰግንበትን ነገር የሚያካፍልበት የተወሰነ ጊዜ ውሰዱ።

እርምጃ 2 - የሚያስቸግሯችሁን ነገሮች ተናገሩ እና እርስ በእርስ ፀልዩ

በቡድናችሁ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው የሚቸገርበትን ነገር በአጭሩ እንዲያካፍል አድርጉ። ስለሚያካፍለው ነገር ሌላ ሰው እንዲጸልይለት አድርጉ።

እርምጃ 3 - በቡድኑ ላይ ማተኮር

ጊዜ ወስዳችሁ ለምን አብራችሁ እንደሆናችሁ አስታውሱ - እግዚአብሔርን ለመውደድ፣ ሌሎችን ለመውደድ፣ ስለ ኢየሱስ ለማካፈል እና ሌሎችም እሱን እንዲካፈሉ ለመርዳት።

እርምጃ 4 - ማረጋገጥ

እያንዳንዱ ሰው የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲመልስ ጠይቁት፦

  • እስካሁን የተማርከውን የታዘዝከው እንዴት ነው?
  • ስለተማርከው ነገር ማንን አሰልጥነሃል?
  • በቡድን አብረን ከሆንበት ጊዜ ጀምሮ ከማን ጋር ታሪክህን ወይም የእግዚአብሔርን ታሪክ ተካፍለሃል?)

ወደላይ መመልከት

እርምጃ 1 - የእግዚአብሔር ቅዱሱ መንፈስ እንዲመራችሁ ጋብዙት

ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ውሰዱ። ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉና በጥቂት ቃላት ተነጋገሩ። ልታነቡት ካሰባችሁት ምንባብ እንዲያስተምራችሁ መንፈስ ቅዱስን ለምኑት።

እርምጃ 2 - የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ እና ጥያቄዎችን ጠይቁ

በቡድኑ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ አድርጉ። አንብበው ሲጨርሱ፣ ቡድኑ የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች መመለስ አለበት፦

  • ከዚህ ምንባብ ምኑን ወደዳችሁት?
  • ምን አዳጋች ወይም ለመገንዘብ የሚያስቸግር ሆኖ አገኛችሁት?

ያንኑ ምንባብ ለሁለተኛ ጊዜ አንብቡና ቡድኑ የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች እንዲመልስ ጠይቁ፦

  • ከዚህ ምንባብ ስለ ሰዎች ምን እንማራለን?
  • ከዚህ ምንባብ ስለ እግዚአብሔር ምን እንማራለን?

ከምንባቡን አለመውጣት እና ቀላል ማድረግን አስታውሱ!

ወደፊት መመልከት

እርምጃ 1 - ስለ እግዚአብሔር ዓላማ መጸለይ

በቡድናችሁ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው በእርጋታ እንዲጸልይ አድርጉ እና የሚከተሉተን ጥያቄዎች እግዚአብሔርን ጠይቅ፦

  • እግዚአብሔር ሆይ፣ የምታስተምረኝን ልታዘዝ እና ተግባራዊ ላደርግ የምችለው እንዴት ነው?
  • ከዚህ ምንባብ አንተን መታዘዝ እና ይበልጥ መውደድ እንዲማር ማንን ማሰልጠን እችላለሁ?
  • ምስክርነቴን ወይም የኢየሱስን ምሥራችን ለማን እንዳካፍል ትፈልጋለህ?

በአሁን ጊዜ እና ቡድናችሁ እንደገና በሚገናኝበት ጊዜ እንድትጠቀሙት የተወሰኑ መልሶችን፣ ስሞችን እና እርምጃዎችን እንዲሰጣችሁ ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ ጠይቁ።

እርምጃ 2 - ቁርጠኝነቶችን ማሰባሰብ

በቡድናችሁ ውስጥ ያለ እያንዳንዱን ሰው ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከጌታ የሰማውን እንዲያካፍል ጠይቁ። የሆነ ሰው በአንድ፣ በሁለት ወይም በሶስቱም ጥያቄዎች ከጌታ ዘንድ ምንም አልሰማ ይሆናል። ምንም እንዳልሰሙ በቀላሉ ሊናገር ይችላል።

ቢሆንም ቡድኑ ከጌታ መስማት እንዳለበት አስታውሱ። ጌታ ኢየሱስ ‹‹በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ›› ብሏል። እና የመታዘዝ እርምጃዎቻችሁ ይበልጥ በታወቁ መጠን፣ እንደገና ከመገናኘታችን በፊት እነሱን መታዘዝችን ቀላል ይሆናል።

እርምጃ 3 - እቅዳችሁን መለማመድ

የአብሮነት ጊዜያችሁን ከማብቃታችሁ በፊት የ3/3 ቡድናችሁ በሁለት ወይም በሦስት አነስተኛ ቡድኖች እንዲከፋፈል አድርጋችሁ ጌታ እንድታደርጉት ሲጠይቅ የሰማችሁት ተለማመዱ።

ይከልሱ

(1 min)

NEXT STEP

ታዘዙ

እግዚአብሔር 3/3 ቡድን እንድትፈጥሩ ከፈለገ ጸልዩ እና ጠይቅ። የሚፈልግ ከሆነ፣ የ100 ዝርዝራችሁን ተመልከቱ እና ማንን እንዲቀላቀል መጋበዝ እንዳለባችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ። ከዚያም በዚህ ሳምንት ያንን ሰው ጋብዙት እና እግዚአብሔር ቡድኑን እንደሚገነባ እመኑት።

አካፍሉ

ቡድናችሁ እንደገና ከመገናኘቱ በፊት የ3/3 ቡድን ቅርፀቱን የምታካፍሉትን ሰው አግኙ። ከመሄዳችሁ በፊት የዚህን ሰው ስም ለቡድኑ አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 15

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 4327

ፀልዩ

(5 min)

በቡድኑ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ሰው በቡድኑ እንዲጸልይለት የሚፈልግበትን ልዩ ፍላጎቶች ያሉት እንደሆነ ጠይቁ። የእግዚአብሔር ህዝቦች ሲጸልይ እንደሚሰማቸው እና እንደሚሰራ በቃሉ ተስፋን ስለሰጠን እግዚአብሔርን አመስግኑ። ቆይታችሁን እንዲመራላችሁ የእግዚአብሔር ቅዱሱ መንፈስን ጠይቁ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

  • የስልጠና ዑደት ለበሰሉ ደቀ መዛሙርት
  • የአመራር ክፍሎች

READ

(5 min)

የስልጠና ዑደት

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ደቀ መዛሙርት ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የወንጌልን ተልዕኮ ከፍ ወዳለ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴነት የሚለውጡበትን ዓይነት የሥልጠና ዑደት እንማራለን፡፡ ቢስክሌት (ወይም ሳይክል) የመንዳት ትምህርት ተምራችሁ ታውቃላችሁ? ወይም ደግሞ ቢስክሌት መንዳት የሚማርን ሰው ደግፋችሁ ታውቁ ይሆን? እንደዚያ ከሆነ፣ የዚህን የሥልጠና ዑደት የመረዳት እድሉን ቀድማችሁ አግኝታችሁታል ማለት ነው፡፡ እንደ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ ያለ ቀላል ነገር ነው፡፡ እስቲ አስቡ፣ ቢስክሌት ከመንዳታችሁ በፊት፣ በመጀመሪያ ምናልባትም የሆነ ሰው ሲነዳ ተመልክታችሁታል፤ አነዳዱን አሳይቷችኋል፡፡ ስለዚህ ማሳየት ማለት ያ ነው፡፡ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ ማሳየት ቀለል ባለ አገላለጽ ለአንድ ለሌላ ሰው አንድ ነገር እንዴት እንደሚተገበር ማሳየት ነው፡፡ አንድ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው ቢስኪሌት ሲነዳ ቢመለከት፣ በቀጥታ ቢስኪሌቱን የመንዳቱን ሃሳብ ያገኛል፡፡ ማሳየት እንደዚያ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ማሳየት ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢስክሌት የነዳችሁበትን ጊዜ መለስ ብላችሁ አስቡት፤ በቃ ዝም ብላችሁ ማየት ነበር የፈለጋችሁት? ወይስ እናንተም ሳይክሉ ላይ ወጥታችሁ የመንዳት ሃሳብ መጣባችሁ? ያንን እድል የሚሰጣችሁ ፈጽሞ ባታገኙስ ኖሮ? እጅግ ብዙ ማሳየት በእርግጥ የሥልጠናውን ሂደት ይጎዳዋል፡፡ ማሳየት ለአንድ ሰው ጥቂት ነገር መጠቆም ነው፤ ከዚያም ተመልካቹ እንዲሞክረው ማበረታታት ነው፡፡ በዚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢስክሌት በነዳችሁበት አጋጣሚ ምን ተከሰተ? በቃ የሆነ ሰው ቢስክሌቱን ሰጥቷችሁ ሄደ? ምናልባትም እንደዚያ አልሆነም፡፡ ብዙ ሰዎች ቢስክሌት መንዳት ሲማሩ፣ የመጀመሪያዎቹን የመንዳት ደረጃዎች እስኪለማመዱ ድረስ ደጋፊ ሰው አብሯቸው ይሆናል፡፡ ያም ሰው ከለማጆቹ ጎን የሚሆን እና ሚዛናቸውን ስተው እንዳይወድቁ የሚረዳ ነው፡፡ መደገፍ ማለትም ይህ ነው፡፡ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ መደገፍ ተለማማጁ የመንዳትን ክሕሎት እንዲለማመድ የሚፈቅድ እና ለማጁ በሚወድቅም ጊዜ አወዳደቁ የከፋ መሆን እና አለመሆኑን የሚከታተል ነው፡፡ መደገፍ ከማሳየት የበለጠ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ሆኖም የተጋነነ ረጅም ጊዜ ግን አይወስድም፡፡ እጅን የማስያዣ፣ አቅጣጫ የማስያዣ እና ጥቂትም መንገድ የማሳያ ጊዜ ይፈልጋል፤ ነገር ግን መሠረታዊ የአነዳድን ክሕሎት ማስጨበጫ ነው፡፡ ተለማማጁ ፍጹም ባለክሕሎት እስኪሆን ድረስ ግን አይደለም፡፡ የቢስኪሌቱን መርገጫ ፔዳሎች እንዴት እንደሚያሽከረክር መምሪያ ነው፡፡ ቢስክሌት መንዳት በጀመራችሁ ጊዜ ፔዳሉን ዘውራችሁ፣ ፍጥነት ጨምራችሁ እስክትነዱ ድረስ ከጎናችሁ የሚሮጠውን ሰው በአእምሮኣችሁ ማሰብ ትችላላችሁ? አብረዋችሁ ብዙ አልዘለቁም፤ ቢቀጥሉ ኖቶ ሚዛናችሁን መጠበቅን ፈጽሞ ሳትማሩ ትቀሩ ነበር፡፡ መደገፍ አንድ ሰው ቢስክሌቱን በራሱ እየነዳ እንዲሄድ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ተለማማጁ መንቀሳቀስ ሲጀምር፣ ለቀጣዩ ቢስክሌት ነጂ የቢስክሌትን አነዳድ እያሳየም ጭምር ነው፡፡ በቢስክሌቱ ላይ የሌላ ተጨማሪ ሰው እጆች በሌሉ ጊዜ እንኳን፣ ብቻችሁን ናችሁ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው አነዳዳችሁን በአንክሮ እየተመለከተ ነው፤ ሆኖም የሚመለከተው ከሩቅ ሆኖ ነው፡፡ መመልከት የሚባለው ይህ ነው፡፡ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ መመልከት ተለማማጁ ራሱን ችሎ መንዳት እስኪችል ድረስ መምራት ነው፤ ይኸውም በተለማማጁ ልምምድ ውስጥ ጣልቃ ሳይገባ እና ልቆጣጠርህ ሳይለው የሚሆን ነው፡፡ በቢስክሌት መንዳት ሂደት አንድ ሰው ቢስኪሌቱን ራሱ አስነስቶ በፍጥነት ሊያሽከረክር ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን የአነዳዱን ሕግጋት ጠንቅቆ አውቋል ማለት አይደለም፡፡ መመልከት ማለት ቢስክሌት ተለማማጁ በመንገድ ላይ ማንም በሌለ ጊዜም እንኳን በጥንቃቄ መንዳቱን ማረጋገጥ ነው፡፡ መመልከት ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር እንዴት እንደሚያደርግ እንዲያውቀው ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ሌላ ሰው በማይመለከተው ጊዜም እንኳን በትክክል ማድረግ መቻሉን ማረጋገጥ ነው፡፡ በዚህ የሥልጠና ዑደት ደረጃ ላይ፣ ተለማማጁ ያድጋል፡፡ የእድገትንም መንገድ ለሌሎች ያስተምራል… ያስተማራቸውም ሌሎች የሚያድጉበትን መንገድ ያስተምራሉ፡፡ … እነዚያ የተማሩትም የዕድገትን መንገድ ለሌሎች ያስተምራሉ፡፡ ደቀ መዛሙርትን የሚፈሩ ደቀ መዛሙርትንም ይበዛሉ፤ የበዙትም እንዲሁ የሚያፈሩ ደቀ መዛሙርትን ያፈራሉ፡፡ ይህም እስከ ሦስት እና አራት ትውልድ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ መመልከት ተለማማጁ በክህሎት እንዲበስል የማድረጉን ሥራ ለመሥራት የሚፈቅድ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎችን ለመርዳት የሚችልም ነው፡፡ መመልከት ጥቂት ጊዜ የሚወስድ ሥራ ነው፡፡ ምናልባትም ማሳየት እና መደገፍ በጋራ ከሚወስዱት አሥር እጥፍ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ ረጅም ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ጊዜ መውሰዱ የሚገባው ነው፡፡ ምክንያቱም በመጨረሻ ቢስኪሌት ነጂው እንደሚገባው መንዳት የሚያስችለው ሂደት ነው፡፡ መልቀቅ ማለት ይህ ነው፡፡ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ፡፡ መልቀቅ ልክ እንደ መመረቂያ ክብረ በዓል ነው፡፡ ተማሪው አስተማሪ የሚሆንበት ነው፡፡ ሠራተኛው አብሮ-ሠራተኛ የሚሆንበት ነው፡፡ ደቀ መዝሙር ጓደኛ - ወዳጅ የሚሆንበት ነው፡፡ በቢስክሌት መንዳት ሂደት፣ መንዳትን የሚያስተምራችሁ ሰው ቢስክሌት በነዳችሁ ቁጥር አብሯችሁ አይሆንም፡፡ አልፎ አልፎ አብሯችሁ ሊያሽከረክር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ለብቻችሁ ታሽከረክራላችሁ፡፡ ከሌሎች ጋር ወይም ብቻችሁን ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ መልቀቅ ልክ ለአንድ ለምትወዱት ሰው የመጨረሻ ጊዜ ስጦታችሁን እንደመስጠት ነው፤ ያም የነጻነት ስጦታ ነው፡፡ መልቀቅ እናንተ ቀድማችሁ ወደሄዳችሁበት ሥፍራ እንዲሄድ አስታጥቆ መሸኛ ነው፤ ግን ደግሞ እናንተ መሄድ ወዳልቻላችሁበትም ሥፍራ እንዲሄድ አበረታታችሁ የምትለቁበትም ነው፡፡ ማሳየት፣ መርዳት፣ መመልከት እና መልቀቅ፤ ከአንድ ወደ ብዙዎች፤ ከተልዕኮ ወደ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. የስልጠና ዑደት አካል ሆናችሁ ታውቃላችሁ?
  2. ማንን ነው ያሰለጠናችሁት? ወይንስ ማን አሰለጠናችሁ?
  3. የተለያዩ ክህሎቶችን በሚማርበት ጊዜ ይኸው ሰው በተለያዩ የስልጠና ዑደት ክፍሎች ውስጥ ሊሆን ይችላል?
  4. እንደዚህ አይነት ሰው ማሰልጠን ምን ይመስላል?

READ

(5 min)

የአመራር ክፍሎች

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ትንንሽ የመሪነት ቡድኖች እንዴት የኢየሱስ ተከታዮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕይወት ዘመን መሪዎች እንደሚያደርጓቸው እንማራለን፡፡ በዚህም ሂደት አንዱ ሁለት ይሆናል፡፡ ሁለቱ አራት ይሆናሉ፡፡ አራቱ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ግለሰቦች ይባዛሉ፡፡ ይህም ትውልዳዊ ብዜትን ይወልዳል፡፡ ይህም ደግሞ ከፍተኛ አሃዛዊ ዕድገትን ያመጣል፡፡ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ ያነጸው የማብዣ ስልትም ይኸው ነው፡፡ የእግዚአብሔርም ቤተሰብ እንዲያድግ እግዚአብሔር የፈለገው በዚህ መልኩ ነው፡፡ ተጠቃሚዎችን ወደ አምራችነት፣ ተማሪዎችን ወደ መሪነት፣ እንዲሁም ደቀ መዛሙርትን ወደ ደቀ መዛሙርት አድራጊነት የለወጠውን የ3 - 3ኛ አካሄድ ቀደም ሲል ተምረናል፡፡ የኋላችሁን ተመልከቱ፤ ወደ ላይ ተመልከቱ፤ የፊታችሁን ተመልከቱ፡፡ ተማሩ፤ ታዘዙ፤ የተማራችሁትንም አካፍሉ፡፡ በአማኝ ግለ-ሰቦች ሕይወት ቀጣይነት ያለውን መንፈሳዊ ዕድገት እና በኢየሱስ ተከታዮች ዘንድም እንደ ቡድን የብዜትን ዕድገት አገጣጥሞ የሚያስኬደው መንገድ ይህ ነው፡፡ የቡድን ዕድገቱ ለአጭር ጊዜ የሆነ እንደሆነስ? ዕድገታቸው እና የእግዚአብሔር መንግሥት ዕድገት ይቀጥል ይሆን? እንደ ቡድን ቀጣይነቱ ወሰን እንዳለው በምትረዱ ጊዜ፣ በመሪነት ቡድኖች ስልት የ3 - 3ኛን አካሄድ በመዘርጋት የቡድኖቹን ሥራ እንዲቀጥል የምታደርጉበት አካሄድ ነው፡፡ የመሪነት ቡድኖች በአጭር ጊዜ እያንዳንዱን አማኝ በማስታጠቅ የብዜት አካሄድን የሕይወት ዘመን አካሄድ እንዲሆን የሚያስተምር ነው፡፡ የመሪነት ቡድኖች ተማሪዎችን መሪዎች እንዲሆኑ በመርዳት አዳዲስ ቡድኖችን እንዲመሠርቱ ያደርጋል፤ ይህም አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን እና አዳዲስ የመሪነት ቡድኖች እንዲመሠረቱ በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተሰብ ያሳድጋል፡፡ የመሪነት ቡድኖች እንደሚገባው የሚሠሩት እንደ ቡድን ተንቀሳቃሽ ሲሆኑ ነው፡፡ አርብቶ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ የመከላከያ የሥራ ክፍል፣ ወቅት-መራሽ ሠራተኞች ሆነው ኢየሱስን የሚከተሉ ሲሆን፣ በመሪነት ቡድን መልክ ሲሠሩ ታላላቅ ውጤቶችን ያስገኛሉ፡፡ በባሕላቸው ምክንያት፣ በሙያቸው ወይም በሕይወት ዘይቤኣቸው ምክንያት ቀጣይነት ያለውን ቡድን መመሥረት ሊከብዳቸው ቢችልም፣ በሚንቀሳቀሱባቸው፣ በየደረሱባቸው ሥፍራዎች እንዴት ቡድኖችን መመሥረት እንዳለባቸው ቢሠለጥኑ ግን ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የመሪነት ቡድን ሌላው ውጤታማ ሥራ ሊሠራው የሚችለው በዛ ያሉ ሰዎች በአንድነት ወደ እምነት ሲመጡ ነው፡፡ ቤተሰብ፣ የጓደኞች ትሥሥር ወይም አነስተኛ መንደር ወደ እምነት ሲመጡ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሕይወት ዘመን አምራችነት ሊለወጡ የሚያስችል ስልጠና መስጠት ይቻላል፡፡ ይህም እያንዳንዳቸውን ተከታታይ ትምህርት ከማስተማርም በፊት ወይም መንፈሳዊ ሥልጠና ሳያገኙ አስቀድሞ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀደም ባለው ክፍለ - ጊዜ የ3 - 3ኛን አሠራር የመጨረሻዎቹን ሁለት ክፍሎች መለማመድን ተምረናል፡፡ አሁን ደግሞ አሠራሩን በሙሉ ተለማምደናል፤ ሦስቱንም ክፍሎች ማለት ነው፤ ወደኋላ መመልከት፣ ወደላይ መመልከት እንዲሁም ወደፊት መመልከት ማለት ይህ ነው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. አስቀድመው እየተገናኙ ያሉ ወይም ተገናኝተው የZúme ማሰልጠኛ ለመማር የአመራር ክፍል ለመመስረት ፈቃደኛ የሆኑ የምታውቋቸው የኢየሱስ ተከታዮች ቡድኖች አሉ?
  2. አንድ ላይ ለማቀራረብ ምን ያስፈልጋል?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

  • የስልጠና ዑደት ለበሰሉ ደቀ መዛሙርት
  • የአመራር ክፍሎች

NEXT STEP

ታዘዙ

በZúme ከተማራችሁት ውስጥ አንድ ክህሎት ወይም ፅንሰ-ሀሳብ ምረጡና ወደ አራተኛው ትውልድ እንዲሰራጭ አንድን ሰው አማክሩ።

አካፍሉ

በ100 ዝርዝራችሁ ውስጥ ላለ አማኝ ‹‹የስልጠና ዑደት››ን አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 16

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 2871

ፀልዩ

(5 min)

በዚህ ስልጠና ውስጥ እስካሁን ድረስ ለቡድናችሁ አቅም፣ ትኩረትና ታማኝነት ስለሰጣችሁ እግዚአብሔርን በጸሎት አመስግኑት። በቡድን ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው ያለ መንፈስ ቅዱስ ምንም ማድረግ እንደማይችል እንዲያስታውስ እግዚአብሔርን ለምኑት!

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች እንሰማለን እና እንነጋገራለን፡-

  • ቅደም ተከተል የሌለው እድገትን ጠብቁ
  • የማባዛት ፍጥነት ጉዳዮች
  • ሁሌም የሁለት አብያተ ክርስቲያናት አካል

READ

(5 min)

ቅደም ተከተል የሌለው እድገት

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ፣ ነጠላ አስተሳሰብን እንደ እግዚአብሔር መንግሥት በፍጥነት ማሳደጊያ አድርጎ ማሰብን ስለማስወገድ እንማራለን፡፡ ደቀ መዛሙርትን የሚያበዙ ደቀ መዛሙርትን በማፍራት ማድረግ በላቀ ፍጥነት በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮች ሊሆኑ እንደሚችሉና ያንን ለማድረግ የሆነ አንዳች የተሰመረ መሥመር እንደሌለ፣ ግንዛቤ መያዝ አለብን፡፡ በሰው ባልተሠመረ መሥመር የማደግን ድንቅ ገጽታ መማር ይገባናል፡፡ ሰዎች የደቀ መዛሙርትን ብዜት ውጤት ሲያስቡ፣ ደረጃ በደረጃ የመሄድ ሂደት ውጤት መሆኑ ነው የሚከሰትላቸው፡፡ በመጀመሪያ ጸሎት፤ ከዚያም ዝግጅት፤ ከዚያም መልካሙን ዜና - ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርትን ማነጽ፤ ከዚያም ቤተ ክርስቲያኖችን መመሥረት፤ ቀጥሎም መሪዎችን ማሳደግ፤ ከዚያም መባዛት፡፡ በዚህ መንገድ ስንማር የእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመከተል የቀለለ መንገድ ሆኖ ነው የሚታየው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት ለመከተል ለመከተል ቀላል መንገድ ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ቀጥታ እና ተከታታይነት ያለው ሂደት እንደሆነም ነው የምንገነዘበው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ አንዱ ችግር ከላይ የተዘረዘረው መንገድ ሁልጊዜም የሚሠራ አለመሆኑ ነው፡፡ በጣም ትልቁ ችግር ግን አንዳንዴም ቢሆን ደቀ መዛሙርትን ለማብዛት ምርጥ ሂደት አለመሆኑ ነው፡፡ እንዲህ ያለው የተሠመረ መሥመር የአንድን ሰው የሕይወት ሂደት ወካይ ሊሆን ይችላል፡፡ መጀመሪያ ተወለደ፤ የእግዚአብሔርን የምሥራች አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማ፤ አመነ፡፡ በዚህ ጊዜም ኢየሱስን ለመከተል ወሰነ፡፡ ይህ ሰው የራሱን ታሪክ እና የእግዚአብሔርን ታሪክ ማካፈል ጀመረ፡፡ ከዚያም መብዛት ጀመረ፡፡ በዚሁ የዚህ ሰው የሕይወት እድገት ይፈጸማል፡፡ (ምስል) ስለዚህ ከዚህ እስከ እዚህ ስለኢየሱስ በመጀመሪያ ከሰማበት እስከ ስለኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ እስካካፈለበት ጊዜ ድረስ ያለውን ነው እንደ አንድ መንፈሳዊ ትውልድ የምንቆጥረው፡፡ መባዛት ከመጀመራችን በፊት ይህን ያክል ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እስኪያድግ ድረስ ይህን ያክል ጊዜ፣ ደቀ መዝሙርነት ለወትሮው የሚታሰበው በዚህ መልክ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ልክ እንደ ታላቅ በረከት ባለው ሂደት ስንጠቀም ግን የሚሆነውን ተመልከቱ፡፡ አሁን አዲስ ደቀ መዝሙር በፍጥነት መባዛት ይጀምራል፡፡ የአንድ መንፈሳዊ ትውልድ የጊዜ ርዝመት ያጥራል፡፡ የምሥራቹን ዜና መስማት የሚገባው ሰው ቶሎ ይሰማል፡፡ የእግዚአብሔርም ቤተሰብ በላቀ ፍጥነት ያድጋል፡፡ ብዙ ሰዎችም ለዘላለማዊው መንግሥት የመዳንን እድል ያገኛሉ፡፡ ሁሉም ነገር ታዲያ ሲባዙ በመንቀሳቀስ የሚሆን ነው፡፡ ነገር ግን መሄዳችንን ብንቀጥልስ ምን ይሆናል? ከጊዜው ቀድሞ የሚባዛ ሰው ቢገኝስ? ገና ወንጌልን እንደሰሙ ከማመናቸው በፊት የሰሙትን በቃ በቀላሉ ማካፈል ቢጀምሩስ? ተለመደው ሂደት የንስሐ መግቢያ ሥርዓቱን ሳይከተሉ አንዳንዶች ቡድን ቢመሠርቱና ከእግዚአብሔር ቃል የተማሩትን ለጓደኞች እና ለቤተሰቦቻቸው ማካፈል ቢጀምሩስ? እንዲህ ላሉ ሰዎች ቡድን እንዴት እንደሚመሠረት እና እንዴት የተማሩትን ማካፈል እንደሚገባቸው እንዲሁም ሌሎችም እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያስተምሩ ብንመራቸው፣ … የእግዚአብሔር ቤተሰብ ከዚህም በላይ ባለ ፍጥነት ያድጋል፡፡ አሁን መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር፣ ደቀ መዝሙርነት ወደ ኢየሱስ የሚወስድ መንገድ እንጂ ከድነት በስቲያ የምንናገረው የሆነ አሠራር አይደለም፡፡ ህም ቤተሰብ፣ ጓደኞች እንዲያም ሲል መንደር ኢየሱስን ሊከተልበት የሚችል ጎዳና ነው፡፡ ሆኖም አንድ ሰው ከታሰበው ጊዜ ፈጥኖ መባዛት ቢጀምርስ? የእግዚአብሔርን ልጅ እንደሚገባው ሳያውቅ እንኳን ስለእግዚአብሔር መንግሥት መንገድ የሚናገር ቢገኝስ? አንዳንድ ጊዜ አንድ ቡድን የእግዚአብሔርን የምሥራች ዜና ቶሎ ለመስማት የማይችል ወይም ዝግጁ ያልሆነ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ቡድን የእግዚአብሔርን አሠራር እንደ ማኅበረሰብ ዕድገት ወይም የመሪነት ሥልጠና ባሉ መንገዶች ሊማር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ቡድን የእግዚአብሔርን አሠራር፡- መማር፣ መታዘዝ እና ማካፈልን እንዲሁም ሌሎች ይህንኑ አሠራር እንዲከተሉ ማስተማርን ስለኢየሱስ ገና እንደሚገባው ሳይሰማም ሊጀምረው ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ሲከሰት፣ የእግዚአብሔር መንገዶች የሚታተሙት በልብ ላይ ነው፡፡ የእርሱ አሠራር በማኅበረሰብ እና በግለሰብ ሕይወት ውስጥ እንደ ድር ይደራል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር መንገዱን ባዘጋጀ ጊዜም፣ በመንገዳቸው የተቀበሉትን እውነት ይገልጻል፡፡ ይህም ተቋም፣ ማኅበረሰብ እንዲሁም አገር ሳይቀር ኢየሱስን ወደማመን እና መከተል የሚመጣበት መንገድ ነው፡፡ በሰው ያልተሠመረ የእድገት ሂደት አሁንም አስፈላጊ ነው፡፡ "አስፈላጊው ጉዳይ ምንድነው?" የሚለውን ከግምት ማስገባት ይገባዋል፡፡ ሂደቱ ምንም ዓይነት ይሁን፣ ተከትሎት የሚመጣው ጥያቄው አንድ ዓይነት ነው፡- ታማኝ የሆነው መልካም መሬት ማነው? ማንስ ነው የተማረውን የሚተገብር እና የእግዚአብሔርን መንገድ ላልሰሙ የሚያካፍል? ይህንን መልካም መሬት ፈልጎ ለማግኘት፣ ወደእነዚህ መልካም ልቦች መርምሮ ለመድረስ፣ ሙሉ ጊዜያችንን፣ ኃይላችንን እና ጥረታችንን ይጠይቃል፡፡ ይህም ጉዳይ ነው ልባችንን ልናፈስበት የሚገባው፡፡ እነዚህ ልቦች ናቸው ሕይወታችንን ልንገብርላቸው የሚያስፈልገው፡፡ እነዚህም ልቦች ናቸው የእግዚአብሔርን መንግሥት ድንቅ ዕድገት የሚያሳዩት፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የሰማችሁት በጣም ያስደሰታችሁ ሃሳብ ምንድነው? ለምን?
  2. በጣም አስቸጋሪው ሀሳብ ምንድን ነው?ለምን?

READ

(5 min)

ፍጥነት

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍል መባዛት ዋነኛ ጉዳይ እንደሆነ እንዲሁም በፍጥነት መብዛት ከዚያም በላይ ዋነኛ ጉዳይ እንደሆነ እንማራለን፡፡ ይህ ክፍል ስለፍጥነት የምንማርበት ነው፡፡ ፍጥነት ከጊዜ ጋር የተቆራኘ ነገር ነው፤ ማለትም ነገሮች ምን ያክል ይፈጥናሉ ወይም ይዘገያሉ የሚለውን መለኪያ ነው፡፡ ፍጥነት ዋነኛ ጉዳይ የሆነበት ምክንያት የምንነጋገረው ሁላችንም ዘላለምን ስለምናሳልፍበት ሥፍራ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ያለጊዜ ገደብ መኖሪያ ቦታ ነው፡፡ ይህም የሚወሰነው "ሕይወት" በሚባል አጭር ጊዜያችን ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ማንም እንዳይጠፋ ወድዶ እግዚአብሔር ስለእኛ ይታገሳል፡፡ ሁሉ ከገዛ መንገዱ ተመልሶ እርሱን እንዲከተለው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ጊዜ የሚሰጠን እንድንሠራ፣ እንድንሄድ፣ እንድንደርስበት ወደሚፈልገው ለመሄድም እድሜያችን አጭር እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኢየሱስን በቅርበት ለመከተል፣ እርሱ "ሕዝቤ" የሚለውን ሕዝብ በበለጠ ፍጥነት መጠጋት ይገባናል፡፡ ጊዜያችንን በራሳችን ማጥፋት የለበንም፡፡ ከዚያ ይልቅ ወደ እርሱ ለመጠጋት ፍጥነታችንን መጨመር አለብን፡ ዓለማቀፋዊዋ ቤተ ክርስቲያን፤ የኢየሱስ ተከታዮች ማኅበር በጥቅሉ፡- ከዚህ ቀደም ከነበረው ይልቅ የዓለም ሕዝብ የበዛው ክፍል ሆኗል፡፡ ሕዝበ-ክርስቲያኑ በቁጥር እንዲህ በዝቶም ታዲያ፣ ዓለም-አቀፋዊዋ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም አጠቃላይ ሕዝብ እድገት ጋር ሲነጻጸር በፍጥነት እያደገች አይደለም፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን በየትኛውም ዘመን ከሆነው ይልቅ ሕዝበ-ክርስቲያን በቁጥር የላቀ ቢሆንም፣ በዚያው ልክ እርሱን የማይከተለውም ሕዝብ ቁጥሩ የትየሌሌ በመሆኑ ዘላለምን ከኢየሱስ ውጪ ሆኖ ለማሳለፍ የተሰለፈ ነው፡፡ ይህም የሕዝብ ቁጥር ከቀደመው ዓለም ጋር ሲነጻጸር እጅግ የበዛ ነው፡፡ የሚባዙ ደቀ መዛሙርትን ማብዛት ዋነኛ ነገር ነው፡፡ በቃ ከአንድ ደቀ መዝሙር ጀምሩ፡፡ ከዚህ የጀመረው ብዜት በየ18 ወራቱ አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን ቢያፈራ (በዓመት ከመንፈቅ ማለት ነው)፣ እነዚያው ደቀ መዛሙርት ተመሳሳዩን ቢያደርጉ፣ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ 64 ደቀ መዛሙርት፤ የኢየሱስ ተከታዮች ይሆናሉ፡፡ 64 ሰዎች ከአፍቃሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ዘላለማቸውን ይኖራሉ፡፡ ከዚህም በላይ በሆነ ፍጥነት እንቅስቃሴ ቢደረግስ? ፍጥነት ጨምረው ለሥራ ቢሮጡስ? በ4 ወራት ጊዜ (18ቱ ወራት ቀርቶ ማለት ነው)፣ እነዚሁ ደቀ መዛሙርት ተመሳሳይ ተግባራትን ቢፈጽሙ፣ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ አንድ ሚሊዮን የኢየሱስ ተከታዮች ይሆናሉ፡፡ እስቲ አስቡት፣ ከ100 በታች በማፍራት ፋንታ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነውም ፍጥነት በመጨመር ብቻ ነው፡፡ ከ18 ወራት ወደ 4 ወራት በፍጥነት መቀነስ ማለት ከአራት ተኩል በላይ ፍጥነታችንን ጨመርን ማለት ነው፡፡ ይኸው ፍጥነት በእያንዳንዱ የኢየሱስ ተከታይ ላይ ቢፈጸም በ10 ዓመት ጊዜ የእግዚአብሔር ቤተሰብ 15 ሚሊዮን ጊዜ በፍጥነት ይባዛ ነበር፡፡ ከመቶ በታች እና ከቢሊዮን በላይ፤ ፍጥነት ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ታሪካችንን እና የእግዚአብሔርን ታሪክ ለአንድ ሰው በማካፈል ኢየሱስን እንዲከተል መምራት ከእግዚአብሔር ቤተሰብ እንዲቀላቀል ማድረግ ነው፡፡ ለአዲስ የኢየሱስ ተከታይ የመብዛትን ሕግ በትክክል እንዲከተል ማድረግም የእግዚብሔርን ቤተሰብ እንደ ዱር ሰደድ እሳት ተቀጣጣይ ያደርገዋል፡፡ በአኃዛዊ ፍጥነት ፣ ሊገለጽ የማይችል ፈጣን እድገት፡፡ በሊጥ ውስጥ እንዳለ እርሾ፡፡ እንደ ዙሜ፡፡ ሁሉ የሚሆነው ግን በፍጥነት ምክንያት ነው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ፍጥነት ለምን አስፈላጊ ሆነ?
  2. ከእግዚአብሔር የፍጥነት ቀዳሚነት ጋር በጥሩ ሁኔታ ለመስማማት በአስተሳሰባችሁ፣ በድርጊታችሁ ወይም በአመለካከታችሁ ምን መለወጥ ያስፈልጋችኋል?
  3. ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ልታደርጉት የምትችሉት ለውጥን ማምጣት የሚችል አንድ ነገር ምንድነው?

READ

(5 min)

ሁሌም የሁለት አብያተ ክርስቲያናት አካል

እንኳን ወደ ዙሜ ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ፣ የኢየሱስ ተከታዮች የሁለት ቤተ ክርስቲያኖች አንድ ክፍል እንደሚሆኑና እድገትን በመጨመር ታማኝ የሆነውን መንፈሳዊ ቤተሰብ በማሳደግ እንዴት ወደ ከተማ-አቀፍ የአማኞች አካልነት ለመለወጥ ድጋፍ እንደሚደረግ እንማራለን፡፡ በእግዚአብሔር ቃል እንደምናነበው፣ እርሱ ለእኛ ያለው ፍጹም ዓላማ እንደ መንፈሳዊ ቤተሰብ መኖራችን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ቤተሰብ የሚገልጸው እንደ ቤተ ክርስቲያን ሦስት መልክ ነው፡- ዓለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን፡- አምነው ያለፉ፣ አሁን ያሉና ወደፊት ገና የሚሆኑ አማኞች ጉባኤ ነው፤ አካባቢያዊ ወይም የከተማ ቤተ ክርስቲያን፡- በአንድ ከተማ ወይም በከተማው አንድ ክፍል ያሉ አማኞች ጉባኤ ማለት ነው፤ ቀላል ቤተ ክርስቲያን፡- እንደ አንድ ሕንጻ ወይም በአንድ ቤት ውስጥ ያለ የአማኞች ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ትንሽ ቡድን፤ ይህ መሠረታዊ ቤተ ክርስቲያን፣ ሕይወቱን የሚጋራ መንፈሳዊ ቤተሰብ ነው፡፡ ይህም ቤተሰብ በጋራ መሥራት ሲችል ነው ድንቅ ውጤት የሚገኘው፡፡ በዚያው ደረጃም፣ ኢየሱስ ያዘዘው ተከታዮቹ ቀጣይነት ባለው መንገድ አዳዲስ መንፈሳዊ ቤተሰቦችን እንዲመሠርቱ ነው፤ ወደ እርሱ እንዲያድጉም ነው፡፡ እርሱ ሲያዝ ግን አዳዲስ መንፈሳዊ ቤተሰቦች እንዴት መመሥረት እንደሚገባቸው እያስተማረ እና እየደገፈ ነው፡፡ ኢየሱስ የነገረን "አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" በማለት ነው፡፡ ሆኖም ታዲያ እንዴት እነዚህ ሁለት ነገሮች በአንድነት ይመጣሉ? እንዴት እኛ የቤተ ክርስቲያን አንድ አካል ሆነንም እንደገና በአዳዲስ ቤተ ክርስቲያኖች ምሥረታ ሂደት ውስጥ መሪ ተዋናይ ልንሆን እንችላለን? ሁሉን እንዴት በአንድነት ማድረግ ይቻላል? እስቲ አንድ መሠረታዊ ቤተ ክርስቲያንን አስቡ፤ አራት ቤተሰቦች ያሉበት ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ተምሳሌታዊ ጥንዶች የሚወክሉት ቤታቸውን የሚመሩ የተለያዩ ጥንዶች ናቸው፡፡ ሁሉም ጥንዶች የአንድ ቤተ ክርስቲያን አንድ ክፍል ናቸው፡፡ ይህም ሕያው የሆነ መንፈሳዊ ቤተሰባቸው ነው፡፡ ሕይወትን የሚኖሩት እንዲህ ባለ ሁኔታም ነው፡- ወንደሞች እና እህቶች በፍቅር እና በመልካም ሥራ ይበረታታሉ፡፡ እነዚሁ ጥንዶች ግን እያንዳንዳቸው አዳዲስ መንፈሳዊ ቤተሰብ የመመሥረት ሥራ ይሠራሉ፡፡ እነዚህ የሚሳተፉትም በራሳቸው ትንንሽ ቡድኖች ቤተሰብ አመሠራረት መንገድ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ አዲስ መንፈሳዊ ቤተሰብ ሲመሠረት እና ሲያድግ ግን በማሳየት እና በመደገፍ ይረዳሉ፡፡ እንዲህ አስቡ፡- አንድ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ጊዜ አራት ቤተ ክርስቲያኖችን ልትመሠርት ትነሳለች፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ባለ ሁኔታ በፍጥነት ነው ቤተሰቡን የሚያሳድገው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ፍጥነቷን የምትጨምረው እንዲህ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባለው ክፍል፣ ስለሥልጠና ዑደት ተምረናል፡- ያም ማሳየት፣ መደገፍ፣ መመልከት እና መልቀቅ ነው፡፡ ከእነዚህም ሁለቱ ምዕራፎች ማሳየት እና መደገፍ በፍጥነት የሚታልፍባቸው ናቸው፡፡ ይህም አዳዲስ የኢየሱስ ተከታዮችን ጤናማ እና አዳጊ ሆነው በእምነታቸው እንዲጎለብቱ ነው፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የመሠረተቻቸው አራት ቤተ ክርስቲያኖች ታዲያ ምን ይሆናሉ? በማሳየት እና በመደገፍ እንዲጀምሩ ከተደረጉ በኋላ፣ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ (ጥንድ) ቤተ ክርስቲያኖች በማሳየት እና በመደገፍ (የመጀመሪያውን ትውልድ) ረድተዋል፡፡ ይህ ግን ለቀጣዩም (ለሁለተኛውም) ትውልድ ጭምር ነው፡፡ እነዚህ አራት ቤተ ክርስቲያኖች (የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች ማለት ነው)፣ ጥንዶቹ (የመጀመሪያዎቹ ቤተ ክርስቲያኖች)፣ በመመልከት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ፡፡ በዚህም ዓይኖቻቸውን በእነዚህ (የመጀመሪያዎቹ ትውልድ) ቤተ ክርስቲያኖች ላይ ያጸናሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚም አዳዲሶቹን (የሁለተኛው ትውልድ ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያኖች በማሳየት እና በመደገፍ የራሳቸውን ፍሬ እንዲያፈሩም መንገድ ያሳያሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ከአንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ በላይ በአንድ ጊዜ ማሳየት እና መደገፍ አይችሉም፡፡ ሆኖም በቁጥር ብዙ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናትን ግን ማሰልጠን እና ከተጓዳኝ አማካሪዎች ጋር በማገናኘት እድገታቸው እንዲፋጠን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህም ማለት አንድ ነጠላ ቤተሰብ፤ ማለትም አንድ የታናሽ ቡድን ቤተክርስቲያን በአንድ ጊዜ የብዙ ትንንሽ ቡድኖች ቤተ ክርስቲያኖች ውልደት አካል ሊሆኑ ይችላሉ ይህም ብዙ ፍሬ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ አዳዲስ ቤተ ክርስቲያኖችን የሚያበዙ ቤተ ክርስቲያኖችን የሚያበዙ ቤተ ክርስቲያኖች እያደጉ ሲሄዱ ታዲያ ምን ይሆናሉ? እንዴት ሆነው ትሥሥራቸውን ማጠናከር የሚችሉት? እንደ መንፈሳዊ ቤተሰባዊነት እና ዝምድናቸው ቤተ ክርስቲያናዊ ሕይወታቸውን መምራት የሚገባቸው እንዴት ነው? መልሱ ይህ ነው፡- እነዚህ ቀላል ቤተ ክርስቲያኖች በአንድ ሰው አካል ውስጥ እንደሚያድገው ሁሉ ትሥሥራቸው እንደመረብ ተሰናስሎ ወደ ከተማ ወይም ክልላዊ ቤተ ክርስቲያን አካልነት ያድጋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖቹ ተዛማጅ ናቸው፡፡ መንፈሳዊ የውስጥ ሰውነቱ ሥሪተ-ንጥር አንድ ነው፡፡ ከመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቤተ ክርስቲያኖች መወለዳቸው የተሣሠረ ተፈጥሮ ያላቸው ያደርጋቸዋል፡፡ እና አሁን የበለጠ ለመሥራት በጥቂት መመሪያዎች አጋዥነት እንደ አንድ ትልቅ አካል ይመጣሉ፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. ቀጣይነት ያለው ቤተሰብ ማፍራት እና እንዲያድግ ከመክፈል ይልቅ የሚያድጉ እና የሚበዙ አዳዲስ ቤተሰቦችን የሚወልድ መንፈሳዊ ቤተሰብን ጠብቆ መኖር አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ ጽንሰ-ሐሳቦች፡-

  • ቅደም ተከተል የሌለው እድገትን ጠብቁ
  • የማባዛት ፍጥነት ጉዳዮች
  • ሁሌም የሁለት አብያተ ክርስቲያናት አካል

NEXT STEP

ታዘዙ

የ"ፍጥነት" ጽንሰ-ሀሳብን ከጓደኞቻችሁ ጋር መጋራትን ተለማመዱ፤ ጌታ በልባችሁ እና በነፍሳችሁ ውስጥ እንዲያሰርጽ ጸልዩ። ለማን እንድታካፍሉ እንደሚፈልግ ለማወቅ ጌታን ጠይቁት።

አካፍሉ

የራሳችሁን ቀላል ቤተ ክርስቲያን የፈጠራችሁ ከሆነ፣ በውስጡ ላሉ ሰዎች የ‹‹ሁልጊዜ የሁለት አብያተ ክርስቲያናት አካል››ን ንድፍ አካፍሉ። ካልጀመራችሁ፣ ለሌላ ለምታውቁት አማኝ አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 17

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 4328

ፀልዩ

(5 min)

ጸልዩ እና በቃሉ፣ በጸሎት፣ በአካሉ፣ እና በስደትና በመከራ ስለሚናገራችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት። በቡድኑ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚሰማበት ጆሮ እንዲኖረው እና የሚናገረውን እንዲታዘዝ ፀልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ, ይህንን ጽንሰ-ሐሳብ እንሰማለን እና እንነጋገራለን-

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • አመራር በአውታረ መረቦች ውስጥ
  • የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝር

READ

(5 min)

አመራር በአውታረ መረቦች ውስጥ

እንኳን ወደ Zume ሥልጠና እንደገና በሰላም መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍለ-ጊዜ፣ የትሥሥር መሪነት እንዴት አዳጊ ትንንሽ ቤተ ክርስቲያኖችን በጋራ እንዲሠሩ እንደሚያደርግ እና በዚህ እንቅስቃሴም አዳዲስ መሪዎችን በማፍራት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያቀደውን መልካሙን ዓላማውን በመፈጸም ረገድ የበለጠ ፍሬኣማ ሥራ መሥራት እንደሚያስችል እንማራለን፡፡ እንዲህ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖች ሲያድጉ እና አዳዲስ ቤተ ክርስቲያኖችን ሲመሠርቱ፣ የተመሠረቱትም ሌሎችን ቤተ ክርስቲያኖች ሲመሠርቱ፣ እነዚያም ሌሎችን ሲመሠርቱ… ምን ይሆናል? እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች እንዴት ትሥሥራቸውን ጠብቀው መጓዝ ይችላሉ? የተራዘመ-የቤተሰብ ዝምድና መስመር እንዳላቸው መንፈሳዊ ቤተሰብነታቸው ሕይወትን በጋራ መኖር የሚችሉት እንዴት ነው? መልሱ ይህ ነው፡- እነዚህ ያልተወሳሰቡ - ቀላል ቤተ ክርስቲያኖች በአዳጊ ሰውነት ውስጥ እንዳሉ ህዋሳት ናቸው፤ እርስ በእርስ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ከተማ - አቀፍ ወይም ወደ ክልል - አቀፍ ትሥሥር ያድጋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖቹ አንዳቸው ከአንዳቸው የተቆራኙ ናቸው፡፡ አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ሕዋስ ተካፍለዋል፡፡ ከአንድ የምትባዛ ቤተ ክርስቲያን በመወለዳቸው ተቆራኝተዋል፡፡ እና አሁን፣ በተወሰነ የአመራር እገዛ፣ እንደ አንድ አካል የበለጠ ሥራ ለመሥራት ተያይዘዋል፡፡ በከተማ እና በክልል ደረጃ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያሳየን አዳጊ የአማኞች ስብስብ አካል በአዳዲስ የመሪዎች ቡድኖች ይመራል - ይገለገላል፡፡ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ፣ እነዚህን መሪዎች ሽማግሌዎች እና ዲያቆናት፣ እረኞች እና የመንጋው ጠባቂዎች ይላቸዋል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንደምንመለከተው በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዓመታት በርካታ ትንንሽ የቤት ቤተ ክርስቲያኖች የነበሩ ሲሆን፣ የሚገለገሉትም ሰባት ሰዎች ባሉበት አንድ የአገልጋዮች ቡድን ወይም በዲያቆናት ነበር፡፡ እንዲሁም በኤፌሶን ከተማም በተመሳሳይ በርካታ ትንንሽ የቤት ቤተ ክርስቲያኖች እንደነበሩ እና ይገለገሉ የነበሩትም በትንሽ የሽማግሌዎች ቡድን ወይም የኢየሱስን መልካም እረኝነት ፈለግ ተከትለው ለመንጋዎቻቸው ሕይወታቸውን በሰጡ እረኞች እንደነበረም የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል፡፡ በከተማ ወይም በክልል፣ አምስት የአመራር ስጦታዎች ለቤተ ክርስቲያን ስለመሰጠቱም ቃሉ ያስነብበናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።" እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሰጡት አንድ ትንሽ ቡድን የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ሁሉ እንዲሠራ አይደለም፤ ነገር ግን የኢየሱስ ተከታዮች ተነስተው ሥራውን እንዲሠሩ እንዲያገለግሉ ለማዘጋጀት ነው፤ አማኞችም ሁሉ እንደ አንድ አካል ተነስተው በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለውን ሥራ መፈጸም እንዲችሉ ነው፡፡ በተጨማሪም በራሳቸው መንፈሳዊ ቤተሰብ ብቻ ላይ ከማተኮር ይልቅ፣ መሪዎቹ እየተገናኙ ኅብረታቸውን በማጎልበት ልክ በቤት እንዳለችው ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በጸሎት እና እርስ በእርስ በመበረታታት ሥራቸውን ይፈጽማሉ፡፡ የ3፣ 3ኛ አካሄድ በአመራር ሥልጠና እና በአቻ የአማካሪነት ስብሰባዎች ላይ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ አራቱ የምርመራ መስኮች ልክ በአካባቢ ደረጃ ለእቅድ፣ ለግምገማ እና አቅጣጫ ለማሳየት እንደሚጠቅሙ ሁሉ በከፍተኛ ደረጃም አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡ መሪዎች ሲገናኙ እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ ማኅበርም፣ ከዚያም አልፎ በትሥሥራቸውም ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ ሃሳብ ይለዋወጣሉ፡፡ የወከሏቸውን እና የሚያገለግሏቸውን መንፈሳዊ ቤተሰቦች ደህንነት ሁኔታ ያስታውቃሉ፡፡ እንዲህ ባለ ትሥሥር አገልግሎት ላይ ላሉ መሪዎች መልካም የመገናኛ ማዕከል የሚባለው ትሥሥሩ የጀመረበት ቦታ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኖች ትሥሥሩ እንቅስቃሴ የጀመረው በናዝሬት ከተማ ከሆነ፣ የከተማዋ ቤተ ክርስቲያን የምትጀመረው በዚያው በናዝሬት ነው፡፡ እንቅስቃሴያቸው ሲያድግ እና ናዝሬትን ሲያልፉ የባህር ዳርን ትሥሥር ወክለው ደግሞ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ባለተልዕኮዎችን እየላኩ በመላው አገሪቱ እና በመላው ዓለምም መንቀሳቀስ ሲጀምሩ፣ በብሔራዊ እና ዓለም ዓቀፍ ደረጃ መዘርጋት ጀመሩ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ያለው እንዲህ ነው፡- "ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።" እነዚህ የቤተ ክርስቲያኖች ትሥሥሮች ባላቸው የጋራ መንፈሳዊ ፍጥረተ-ሥሪት እና መነሻ ምክንያት ግንኙነታቸው ቀጣይነት ያለው ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቋንቋ፣ በመገናኛ ሁኔታዎች እና በሌሎች ምክንያቶች ትሥሥሩ ወደ ብዙ ትሥሥሮ ሊከፋፈል ይችላል፡፡ ይህ ግን የእድገቱ አንድ አካል እንጂ እንደ ችግር የሚቆጠር አይደለም፡፡ ያልተወሳሰቡ ቤተ ክርስቲያኖች እና እያንዳንዳቸው አማኞች ለመማር፣ ለመታዘዝ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለመከፋፈል ያላቸው ፈቃደኝነት የዚህ ታላቅ የብዜት እንቅስቃሴ መንፈሳዊ ፍጥረተ-ሥሪት(በዘር የተላለፈ ማንነት) ነው፡፡ ይህ የብዜት እንቅስቃሴ እንዲሁም እንቅስቃሴውን ለመጀመር የሚያስፈልገው ማንኛውም ግባት ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ከቤተ ክርስቲያን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከአማኝ ወደ አማኞች ስኬታማ በሆነ መንገድ መተላለፍ ከቻለ፣ ደቀ መዛሙርትን የማብዛት ግለት በእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እና የኢየሱስ ተከታይ ውስጥ የሚገኝ ነገር ይሆናል፡፡ እንቅስቃሴዎች ለእንቅስቃሴዎች መጀመር ምክንያት ሲሆኑ፣ ያ "እርሾ"ውን በሊጡ - በከተማው ወይም በክፍለ-ግዛት (በክልል መንግሥት) ወይም በአገር ደረጃ ሲሠራ ማየት ጀመርን ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር የምትሆነው፡፡ በዚህም መልኩ ነው አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት የማድረግ ታላቁን ተልዕኮኣችንን ልንፈጽም የምንችለው፡፡

ተወያዩ

(10 min)

  1. የቀላል አብያተ ክርስቲያናት አውታረ መረቦች በጥልቅ እና በግል ግንኙነቶች ሲተሳሰሩ የሚገኙ ጥቅሞች አሉ? ወደ አእምሮአችሁ የሚመጡት አንዳንድ ምሳሌዎች ምንድን ናቸው?

READ

(5 min)

የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝር

Zume ግብዓት የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝር ኢየሱስ እንዲህ አለ-- ‹‹ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት - የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም፤›› የእኛን ፍላጎቶች ለእግዚአብሔር ፈቃድ ስንል ለመተው ፈቃደኞች ስንሆን የእግዚአብሔር ቤተሰብ በተሻለ ሁኔታ እንደሚያድግ ጌታ ኢየሱስ ደጋግሞ አሳይቶናል። የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝሩ እንደ የስልጠና ዑደት ወይም የ100 ዝርዝራቸው ባሉ የተለያዩ የZume ግብዓት ክፍሎች በመጠቀም ሌሎችን በምታግዙበት ወቅት ለመመሪያ ልትጠቀሙበት የምትችሉበት ቀላል መሳሪያ ነው። በሌሎች ሰዎች ውስጥ ምን ክህሎቶች እያዳበሩ እያያችሁ ነው? የትኞቹ ዘርፎች መዳበር አለባቸው? የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝር ማግኘታችሁ በምትሄዱበት ቦታ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ የኢየሱስ ተከታዮችን ወደ መሪዎች ስታሳድጉ ትኩረት እንድትሰጡና እንድትሳተፉ ይረዳችኋል። አዎ፣ ይህ ጊዜና ጥረትን ይጠይቃል። አዎ፣ መስዋዕቶችን እና ምርጫዎቻችንን ለእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ ስንል መተው ማለት ነው። እና አዎ፣ ከሁሉም በላይ ዋጋ ያለው ነው። የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝሩ በህይወት ታላቁ ውጥን -- የእግዚአብሔር ስራ ውስጥ እንድትቆዩ የሚያግዝ ከZume ግብዓት የተገኘ ቀላል መሳሪያ ነው።

ልምምድ

(20 min)

Coaching Checklist

የQR ኮዱን ቃኙት ወይም አንድ ወረቀት አዘጋጁ።

መስመር 1ን ተጠቅማችሁ ራሳችሁን ገምግሙና በአሰልጣኝነት ማረጋገጫ ዝርዝር ላይ ተዛማጅ አምዶችን ምልክት አድርጉ።

ተወያዩ

(10 min)

  1. የትኞቹ መገልገያዎች እና ፅንሰ-ሀሳቦች በሚገባ ማሰልጠን እንደምትችሉ ተሰማችሁ?
  2. በሚገባ ለማሰልጠን ምን አይነት መገልገያዎች እና ፅንሰ-ሀሳቦች እንደሚያስቸግራችሁ ተሰማችሁ?
  3. ከማረጋገጫ ዝርዝሩ ውስጥ መጨመር ወይም መቀነስ የምትፈልጓቸው መገልገያዎች ወይም ፅንሰ-ሀሳቦች አሉ? ለምን?

ልምምድ

(5 min)

Get a Coach

አሰልጣኝ ወይም አማካሪ ከሌለዎት፣ የQR ኮድን ቃኙ እና አሁኑኑ እንዲመቻችልዎ ጠይቁ።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው ሀሳብ፡-

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • አመራር በአውታረ መረቦች ውስጥ
  • የማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝር

NEXT STEP

ታዘዙ

ለራሳችሁ አንድ ቀጣይ እርምጃ ለዩ፣ ይህም እርምጃ ሞዴል ማድረግ፣ ማገዝ፣ መመልከት ወይም መተው ሊሆን የሚችል ሲሆን በማሰልጠኛ ማረጋገጫ ዝርዝሩ ውስጥ ከገመገሙት ደቀ መዝሙር ጋር መውሰድ ይኖርባቸዋል።

አካፍሉ

‹‹በአውታረ መረቦች ውስጥ ያለ አመራር›› የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ ለሌላ ሰው አካፍሉ። ከዚያ ለሌላ ሰው እንዲያካፍልም አሰልጥኑት።

ክፍለ ጊዜ 18

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 6548

ፀልዩ

(5 min)

መንገዱ የእኛ መንገድ ስላልሆነ ሀሳቡም ሀሳባችን ስላልሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑት እና ጸልዩ። ለእያንዳንዱ የቡድናችሁ አባል የክርስቶስን ሃሳብ እንዲሰጥ - ሁልጊዜ በአባቱ ስራ ላይ እንዲያተኩር ጸልዩ። የጋራ ጊዜያችሁን እንዲመራ እና እስካሁን ካለው የተሻለውን ክፍለ ጊዜ እንዲያደርግላችሁ መንፈስ ቅዱስን ጠይቁ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና እነዚህን መሳሪያዎች ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን፡-

  • የአራት መስኮች መገልገያ
  • አጠቃላይ ማጓደን

አራት መስኮች እና አጠቃላይ ማጓደን እያደገ የሚሄድ የንቅናቄ ጥረትን ለማገልገል የተነደፉ መገልገያዎች ናቸው።

ማስታወሻ፦ እነዚህን መገልገያዎች በአካባቢያችሁ እንድትተገብሩ የሚረዷችሁ የZúme አሰልጣኞች ይገኛሉ።

አራት መስኮች

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሥራው እንዴት እየተከናወነ እንዳለ እንዲገመግሙ ከአገልግሎት ወደ ጸጥ ወዳለ ቦታ ወስዷቸው ነበር።

አራት መስኮች አሁን ያሉትን ጥረቶች እና በዙሪያው ስላለው የመንግሥቱ እንቅስቃሴ ለማሰላሰል በአመራር ክፍል ጥቅም ላይ ይውላል። የትኛውም መስክ ችላ እንዳይባል በተለይም መሪዎች ጥረቶችን ሚዛናዊ እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል።

ቀጣዮቹን ሁለት ተንሸራታቾች ገምግሙ፦ የመስክ መግለጫዎች እና የአራት መስኮች ምሳሌ

የመስክ መግለጫዎች

ተወያዩ

(10 min)

  1. በዙሪያችሁ ያለውን ባዶ መስክ ለዩ። ምንም የወንጌል እንቅስቃሴ የሌላቸው ከእናንተ ጋር የተገናኙ ማህበረሰቦች ወይም የሰዎች ቡድኖች የትኞቹ ናቸው?
  2. አንደኛው እርሻ ችላ ከተባለ የረጅም ጊዜ እድገቱ ላይ ተፅዕኖ የሚደርሰው እንዴት ነው? ምሳሌዎችን ስጡ።
  3. የትኞቹ የZúme መገልገያዎች በየትኛው መስክ ሊያግዙ ይችላሉ?

ፀልዩ

(5 min)

ከእግዚአብሔር ለመስማት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ እናም እናንተም ወይም ቡድናችሁ ባደረጋችሁት የአራት መስክ ውይይት ላይ በመመርኮዝ እናንተ ወይም ቡድናችሁ ልትወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎች ካሉ ጠይቁ።

አጠቃላይ ማጓደን

የትውልድ ማጓደን (የትውልድ ማጓደን ወይም የዘረ ግንድ ማጓደን በመባል የሚታወቀው) በንቅናቄ ላይ ያሉ መሪዎች በዙሪያቸው ያለውን እድገት እንዲረዱ የሚያግዛቸው ሌላኛው ቀላል መገልገያ መሣሪያ ነው።

የትውልድ አመጣጥ ካርታ በነጠላ ወረቀት ወይም በበርካታ ወረቀቶች ላይ ሊሳል ይችላል። ይህ ካርታ የማባዛት ግቦች የት እንዳሉና ስልጠና ሊያስፈልግ እንደሚችል ለማሳየት ይረዳል። የንቅናቄው ጤናማነት ጉዳይ የመሪዎች ከፍተኛ ስጋት ሲሆን ጤናማነቱን ለመለካት ፍሬያማነት ዋና መንገድ ነው።

በቀጣዩ ስላይድ ላይ ያለውን ምሳሌ ተመልከቱ።

ተወያዩ

(10 min)

በሚከተሉት ላይ ለመወያየት የአጠቃላይ ማጓደን ምሳሌን ተጠቀሙ፦

  1. ማባዛትን የሚያዩት መሪዎች የትኞቹ ናቸው?
  2. ቀጥሎ የትኞቹ ቡድኖች ይበዛሉ ብላችሁ ትጠብቃላችሁ?
  3. ሌሎች መሪዎችን ለመርዳት እና ለማጠናከር ማገዝ የሚችሉት የትኞቹ መሪዎች ናቸው?
  4. በየትኛውም ትውልዶች ውስጥ ደካማ የተጠያቂነት ንድፍ ትመለከታላችሁን?

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰሙ መሳሪያዎች፡-

  • የአራት መስኮች መገልገያ
  • አጠቃላይ ማጓደን

NEXT STEP

ታዘዙ

በእያንዳንዱ የZúme የስልጠና ንጥሎች ውስጥ ይሂዱ እና እያንዳንዳቸው ከየትኛው መስክ(ዎች) ጋር እንደሚዛመዱ በመወሰን የአራት መስኮችን ገበታ ከንጥሎቹ ጋር ሰይሙ።

አካፍሉ

የአጠቃላይ ማጓደን መገልገያውንን እንደ ራዕይ የማምጣት ልምምድ ከምታውቁት ሌላ አማኝ ጋር አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 19

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 7657

ፀልዩ

(5 min)

ስለ ክርስቶስ አካል እግዚአብሄርን ጸልዩ እና አመስግኑት። ወደ ኢየሱስ በምትቀርቡበት ጊዜ በእያንዳንዱ የቡድናችሁ አባል መካከል እድገቱን ለመቀጠል የጋራ ፍቅርና ማበረታቻ ለማግኘት ጸልዩ።

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የአቻ ማማከር ቡድኖች

READ

(5 min)

የአቻ ማማከር

Zume ግብዓት የአቻ ማማከር ቡድኖች ኢየሱስ እንዲህ አለ - ‹‹አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።›› የአቻ ማማከር ቡድን የ3/3 ቡድኖችን የሚመራ እና የሚጀምሩ ሰዎችን ያቀፈ ነው። ይህም የ3/3 አሠራር የሚከተል ሲሆን፣ በአካባቢያችሁ ያለውን የእግዚአብሔርን ስራ መንፈሳዊ ጤንነት መርምሮ በመረዳትና በመጠበቅ ረገድ ጠንካራ ስልት ነው፡፡ የአቻ ማማከር ቡድኖች የሚጠቀሙት እያንዳንዱን የኢየሱስን ተከታዮች በማማከር የመሪ-ለመሪ የማማከርን አሠራር ሲሆን፣ ቡድኖቹ የሚሠሩት አነስ አነስ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር፣ ከመንፈሳዊ አገልግሎት ተቋማት ጋር ወይም በመላው ዓለም ከሚሠራ ቀለል ያለ ዓለም-አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ትሥሥር ጋር ነው። የአቻ ማማከር ቡድኖች ከቅዱሳት መጽሐፍት የኢየሱስን የአገልግሎት ምሳሌ ይከተላሉ፣ እርስ በርሳቸው ጥያቄዎችን ይጠያየቃሉ እናም ግብረ መልስ ይስጣጣሉ -- ሁሉም የሚጠቀሙት ሁሉ የ3/3 ቡድን መሠረታዊ ጊዜ ሰሌዳን መዋቅር ነው። የነዚህ ቡድኖች ዓላማ መፍረድ አይደለም - አንዱን ከፍ ማድረግና ሌላውን ሰው ማዋረድ አይደለም። ኢየሱስ እንዲህ አለ - ‹‹እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።›› በዚህ ፋንታ፣ የአቻ ማማከር ቡድን አላማ በጸሎት፣ በመታዘዝ፣ በትግበራ እና በኃላፊነት እንዲያድጉ ለማገዝ ቀላል ቅርጸት ለኢየሱስ ተከታዮች ማቅረብ ነው። ይህም በሌላ አነጋገር -- ‹‹እርስ በርስ መዋደድ›› ነው። የሚሆነው እንዲህ ነው፦ ወደኋላ ተመልከቱ በመጀመሪያው ሲሶ ወቅት - በመሰረታዊ 3/3 ቡድን ውስጥ እንደምታደርጉት ሁሉ በጸሎትና በመተሳሰብ ጊዜ አሳልፉት። በመቀጠልም የቡድኑን ራዕይ በመመልከት አሳልፉ - ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናነብ፣ ስንጸልይ፣ እግዚአብሔርን ታምነን ስንታዘዝ እና መሠረታዊ ግንኙነቶችን ስንኖር፣ በየግላችን ምን ያህል ተስጥተን በኢየሱስ እንኖራለን? በመጨረሻም በዚህ የመጀመሪያ ሲሶ ወቅት እያንዳንዱን ሰው የድርጊት መርሃ ግብሮች እና በመጨረሻው ክፍለ-ጊዜ ቃል የገባውን ቁርጠኝነቶች ቡድኑ ገምግሞ ምላሽ እንዲሰጥ አድርጉ። ወደላይ ተመልከቱ የቡድኑ መካከለኛ ሲሶ ጊዜ የሚያልፈው በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በውይይት እና በጸሎት የእግዚአብሔርን ጥበብ እና ምሪትን በመፈለግ ነው። እግዚአብሔር በቃሉ ፈቃዱን እና መንገዱን እንዲያስተምራችሁ አጠር ባለ እና ቀላል ጸሎት ጠይቁ። ቆይታችሁን እግዚአብሔር እንዲመራላችሁ መንፈስ ቅዱስን ጠይቁ። የቡድኑ አባላት በእግዚአብሔር ቃል፣ በጸሎት ወይም በሌሎች ተከታዮች በኩል በአመራር ላይ ስላለባቸው ድርሻ ከጌታ ዘንድ የተማሩትን ነገር ማካፈል አለባቸው። ቡድኑ በሚከተሉት ቀላል ጥያቄዎች ላይ እንዲወያይ አድርጉ፦ አንድ- በአራቱ መስኮች ስእላዊ መግለጫ እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ ናችሁ? ሁለት- በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ያለው ምንድን ነው? ከባባዶቹ ተግዳሮቶቻችሁ ምንድን ናቸው? ሶስት- ወቅታዊ የትውልድ ካርታችሁን ከልሱ። አራት- እንቅፋት ሆነባችሁ ወይም ለመረዳት ከባድ የሆነባችሁ ነገር ምን ነበር? አምስት- እግዚአብሔር በቅርቡ ያሳያችሁ ነገር ምንድነው? ስድስት- ከቆዩ መሪዎች ወይም ከሌሎች ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎች እና ግብረ መልስ አሉ? ወደፊት ተመልከት የቡድኑ የመጨረሻ ሲሶ ጊዜ የሚያልፈው እያንዳንዳችን የተማርነውን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እና መታዘዝ እንደምንችል ለማወቅ በመፈለግ ነው። ሁሉም ሰው የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ መንፈስ ቅዱስ እንዲጠቁመው እየጠየቃችሁ ከቡድኑ ውስጥ ካሉት ሁሉ ጋር የጥሞና ጸሎት ጊዜን አሳልፉ፦ ሰባት- በሚቀጥለው ጊዜ አብረን ከመሆናችን በፊት ምን የድርጊት መርሃ ግብሮችን ወይም ግቦችን እንድፈጽም እግዚአብሔር ይፈልጋል? (በስራህ ላይ ለማተኮር እገዛ እንድታገኝ የአራቱን መስኮች ተጠቀም) ስምንት- በዚህ ሥራ ላይ አማካሪዬ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ሊያግዙኝ የሚችሉት እንዴት ነው? በመጨረሻም በቡድን ሆናችሁ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገሩበትን ጊዜ አሳልፉ። እያንዳንዱ አባል ቡድኑ ባልተሰበሰበበት ጊዜ የሚገኛቸውን ሰዎችን ልብ በሙሉ እግዚአብሔር እንዲያዘጋጅ ለመፀለይ እና ለመጠየቅ ይችል ዘንድ ቡድኑ እንዲጸልይ አድርጉ። እያንዳንዱ የቡድኑ አባል በዚህ ክፍለ-ጊዜ እግዚአብሔር ያስተማረውን የሚተገብርበትን እና የሚታዘዝበትን ድፍረትና ጥንካሬ እንዲሰጠው ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ። ልምድ ያለው የቆየ መሪ ለወጣት መሪው መጸለይ ካለበት፣ ለመፀለይ ትክክለኛው ጊዜ ይህ ነው። እነዚህ ቡድኖች በአብዛኛውን በርቀት ስለሚገናኙ፣ የጌታን እራት ለመውሰድ ወይም ማዕድን ለመጋራት የመቻል ዕድላቸው አነስተኛ ነው፣ ሆኖም ስለ ጤና እና ቤተሰብ እና ጓደኞች የምታውቁበትን ጊዜ መመደባችሁን አረጋግጡ። ምንም እንኳን ጌታ ኢየሱስ በጣም ወሳኝ የሆኑትን ሥራዎች ቢፈጽምም፣ ለሚወዳቸው ሰዎች ሁልጊዜ፣ ከጊዜ ጋር ማመጣጠኑን ደጋግሞ አሳይቶናል። የአቻ ማማከር ቡድን ጠንካራ መሪዎችን ለማጎልበት በZume Toolkit የተዘጋጀ ቀላልና ስልታዊ የሆነ መገልገያ ነው።

ልምምድ

(45 min)

የአቻ ማማከር ቡድኖች

የQR ኮድን ቃኙ።

በሁለት ወይም በሦስት አነስተኛ ቡድኖች ተመደቡ። በ3/3 ቅርፀት የተዘጋጀውን የአቻ አማካሪ ቡድን ዝርዝርን ተጠቀሙ።

በቡድኑ ውስጥ አንድ ሰው "ተመካሪ" እንዲሆን ምረጡና ሌሎች አባላት በተጠቆሙት የጥያቄዎች ዝርዝር ውስጥ እንደ አቻ አማካሪዎች እንዲሰሩ አድርጉ።

የአቻ ማማከር ቡድንን ለመምራት የሚረዳ ቀላል ቅርጸት፦

ወደኋላ ተመልከቱ - 1/3ኛ ጊዜያችሁ

በመጀመሪያው ሲሶ ወቅት - በመሠረታዊ 3/3 ቡድን ውስጥ እንደምታደርጉት ሁሉ በጸሎትና በመተሳሰብ ጊዜ አሳልፉት። በመቀጠልም የቡድኑን ራዕይ እና በሚከተሉት የቀደሙት ቁርጠኝነቶች ውስጥ ያለን ታማኝነት በመመልከት አሳልፉ፦ በክርስቶስ መኖር ህይወት ውስጥ ምን ደረጃ ላይ ናችሁ? [ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ጸሎት፣ እምነት፣ መታዘዝ፣ ቁልፍ ግንኙነቶች?] የእርስዎ ቡድናችሁ ካለፈው ክፍለ ጊዜ የድርጊት ዕቅዶቻችሁን አጠናቅቋልን?

ወደላይ ተመልከቱ - 1/3ኛ ጊዜያችሁ

ቡድኑ በሚከተሉት ቀላል ጥያቄዎች ላይ እንዲወያይ አድርጉ፦

  • በአራቱ መስኮች ስእላዊ መግለጫ እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ ናችሁ?
  • በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ያለው ምንድን ነው? ከባባዶቹ ተግዳሮቶቻችሁ ምንድን ናቸው?
  • ወቅታዊ የትውልድ ካርታችሁን ከልሱ።
  • ምን እንቅፋት ሆነባችሁ ወይም ለመረዳት ከባድ የሆነባችሁ ነገር ምን ነበር?
  • እግዚአብሔር በቅርቡ ያሳያችሁ ነገር ምንድነው?
  • ልምድ ካካበቱ መሪዎች ወይም ሌሎች ተሳታፊዎች የሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎች አሉ?

ወደላይ ተመልከቱ - 1/3ኛ ጊዜያችሁ

ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሁሉም ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልሱ እንዲያሳያቸው መንፈስ ቅዱስን እየጠየቃችሁ በጸጥታ ጸሎት ጊዜ አሳልፉ፦

  • ከቀጣዩ የጋራ ጊዜያችን በፊት ምን የድርጊት መርሃ ግብሮችን ወይም ግቦችን እንድናከናውን እግዚአብሔር ይፈልጋል? [በስራህ ላይ ለማተኮር እገዛ እንድታገኝ የአራቱን መስኮች ተጠቀም]
  • በዚህ ሥራ ላይ አማካሪዬ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ሊያግዙኝ የሚችሉት እንዴት ነው?

በመጨረሻም በቡድን ሆናችሁ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገሩበትን ጊዜ አሳልፉ። እያንዳንዱ አባል በቡድኑ እንዲጸልይለት ያድርጉ፣ ከዚያም ቡድኑ በሚለያይበት ጊዜ የሚደርሳቸውን ሰዎች ሁሉ ልብ እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔርን ጠይቁ። እያንዳንዱ የቡድኑ አባል በዚህ ክፍለ ጊዜ እግዚአብሔር ያስተማረውን ተግባር ላይ በማዋል እንዲታዘዝ ድፍረት እና ጥንካሬ እንዲሰጠው ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ። ልምድ ያለው መሪ በዋናነት ለወጣት መሪ መጸለይ ካስፈለገው፣ ለዚያ ጸሎት አመቺው ጊዜ አሁን ነው። እነዚህ ቡድኖች ብዙ ጊዜ የሚገናኙት በርቀት በመሆኑ የተነሳ የጌታን እራት ለማክበር ወይም ምግብ ለማካፈል ባትችሉም ስለ ጤና እና ቤተሰብና ጓደኞች ለመፈተሽ በቂ ጊዜ መመደባችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

ይከልሱ

(1 min)

በዚህ ክፍለ ጊዜ የተሰማው መገልገያ፦

  • የአቻ ማማከር ቡድኖች

NEXT STEP

ታዘዙ

ከZúme ማሰልጠኛ ቡድን ጋር አባላቶቹ ከስልጠናው መደምደሚያ በኋላ ለመገናኘት ፈቃደኛ እንደሆኑ ወይም እንዳልሆኑ ለማወቅ እንደ የአቻ አማካሪ ቡድን ተወያዩ።

አካፍሉ

በ100 ዝርዝራችሁ ውስጥ ለሁለት አማኞች የ‹‹አቻ ማመከር ቡድን›› ጽንሰ-ሀሳብ አካፍሉ።

ክፍለ ጊዜ 20

መግባት

(1 min)

ሁሉንም ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲገቡ አድርጉ።

Or six.zume.training/checkin and use code: 2767

ፀልዩ

(5 min)

በእኛ ውስጥ ያለውን በጎ ስራውን ለመፈፀም ታማኝ ለሆነው እግዚአብሔር ጸልዩ እናም አመስግኑ።

በእናንተ ውስጥ እና በእናንተ በኩል ሊያደርግ ለሚፈልጋቸው ታላላቅ ነገሮች ለቡድናችሁ ግልፅ ሃሳቦች እና ክፍት ልቦችን እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁት።

የጋራ ጊዜያችሁን መንፈስ ቅዱስ እንዲመራችሁ ጠይቁት እና ስለ ታማኝነቱም አመስግኑት። እሱ ያሻግራችኋል!

ወደኋላ ተመልከቱ

(5 min)

ከመጀመራችሁ በፊት ወደኋላ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በቡድናችሁ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የተማረውን እንዲለማመድ ተገፋፍቷል።

ቡድናችሁ በዚህ ሳምንት እንዴት እንዳደረገ ለማየት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።

ተበረታቱ…

ላታውቁት ትችላላችሁ፣ አሁን ግን በአለም ዙሪያ ካሉ መጋቢዎች እና ሚስዮናውያን በላቀ የሚበዙ ደቀ መዛሙርትን ስለማፍራት ቀላል አብያተ ክርስቲያናትን ስለማቋቋም የበለጠ የተግባር ስልጠና አግኝታችኋል!

የZúme ስልጠና ገና ጅማሬ ብቻ ነው! በዚህ ክፍለ ጊዜ ወቅት፣ ለድህረ ስልጠና ለሚሆነው ነገር እቅድ እናዘጋጃለን።

ማጠቃለያ

(1 min)

እና ይህንን መሳሪያ ወደ መሳሪያችን እንጨምራለን-

  • የሶስት-ወር እቅድ

የሶስት-ወር እቅድ

እግዚአብሔር በመጽሃፍ ቅዱሱ ላይ ‹‹ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ›› ይላል እግዚአብሔር፤ ‹‹ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም›› ይላል።

እግዚአብሔር እቅዶችን ያወጣል ስለዚህም እኛንም እቅድ እንድናወጣ ይጠብቅብናል።

የሶስት ወር እቅድ ማለት ትኩረታችሁን እና ጥረቶቻችሁን እንድታስቀጥሉ እና የሚበዙ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ከእግዚአብሔር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች ጋር ተስማማታችሁ እንድትቆዩ እገዛ ለማግኘት ልትጠቀሙበት የምትችሉበት መገልገያ ነው።

ቀጣዩ ስላይድ የሶስት ወር እቅድዎን እንዴት እንደሚያዘጋጁ ያሳይዎታል። የመስመር ላይ መገልገያውን እንዲጠቀሙ እንመክራለን።

ልምምድ

(30 min)

Three Month Plan

የQR ኮድን ቃኙ።

አንብቡ - ለእያንዳንዱ ንጥል ነገር ቃል መግባት የግድ አይጠበቅባችሁም፤ ይልቁንም እነዚህ ለዕቅዳችሁ ማበረታቻዎች ይሆናሉ ተብለው የታሰቡ ናቸው። (5 ደቂቃ)

አዳምጡ - በተቻለ መጠን በጥሞና ለመሆን ጊዜ ወስዳችሁ እግዚአብሔር ለመግለጥ የወደደውን አዳምጡ። (10 ደቂቃ)

እቅዳችሁን መዝግቡ - ቁርጠኝነቶችን በወረቀት ላይ ፃፉ ወይም የእናንተን መልስ ለማስቀመጥ የመስመር ላይ መገልገያውን ተጠቀሙ። (15 ደቂቃ)

ተወያዩ

(10 min)

  1. የሶስት ወር ዕቅዶቻችሁን አንዳችሁ ለሌላው ተካፈሉ።
  2. በየሳምንቱ ከእናንተ ጋር ለመመዝገብ ፈቃደኛ የሆነ የስልጠና አጋር(ዎች) አግኙ። ለእሱም ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ቃል ግቡ።

ልምምድ

(0 min)

ማህበረሰቡን ይቀላቀሉ

የZúme የስልጠና የተወሰነው ክፍል እያበቃ ነው፣ ይሁንና የመገልግያዎች እና ጽንሰ-ሐሳቦች ልምምድ እንደቀጠለ ነው።

ብቻዎን አያድርጉት። ለማበረታታትና በመንፈሳዊ ለማደግ ማህበረሰብ ያግኙ።

የQR ኮድን በመጠቀም የZúme ማህበረሰብን ይቀላቀሉ።

Zúme Training — To saturate the world with multiplying disciples in our generation.