መንፈሳዊ መተንፈስ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
መንፈሳዊ መተንፈስ ማለት ቀኑን ሙሉ፣ በየቀኑ እግዚአብሔርን መስማት እና መታዘዝ ነው።
ወደ ውስጥ መተንፈስ
በመንግሥቱ ውስጥ ከእግዚአብሔር በሚከተሉት መንገዶች ስንሰማ ወደ ውስጥ እንተነፍሳለን፦
- ቃሉ - መጽሐፍ ቅዱስ
- ጸሎት - ከእርሱ ጋር የምናደርገው ውይይት
- አካሉ - ቤተ ክርስቲያን፣ ሌሎች የኢየሱስ ተከታዮች
- ሥራዎቹ - ለልጆቹ እንዲያልፉባቸው የሚፈቅዳቸው ክስተቶች፣ ልምዶች እና አንዳንድ ጊዜም ስደቶችና መከራዎች
ለእያንዳንዱ የኢየሱስ ተከታይ ያለው የምሥራች ይህ ነው፤ ወደ ውስጥ ስንተነፍስ ከእግዚአብሔር እንሰማለን፣ ወደ ውጭ ስንተነፍስም የሰማነውን ስንታዘዝ እና የሰማነውን ለሌሎች ስናካፍል፣ እግዚአብሔር ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ ይናገራል።
ወደ ውጭ መተንፈስ
በመንግሥቱ ውስጥ ከእግዚአብሔር በሰማነው መሠረት ስንሠራ ወደ ውጭ እንተነፍሳለን። ወደ ውጭ የምንተነፍሰው ስንታዘዝ ነው። አንዳንድ ጊዜ ወደ ውጭ መተንፈስ ማለት ለመታዘዝ ሐሳባችንን፣ ቃላችንን ወይም ድርጊታችንን ከኢየሱስና ከፈቃዱ ጋር እንዲስማሙ መቀየር ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜም ወደ ውጭ መተንፈስ ለመታዘዝ ኢየሱስ ከእኛ ጋር ያካፈለንን ለሌሎች ማካፈል ማለት ነው - የሰጠንን ለሌሎች መስጠት - እግዚአብሔር እኛን እንደሚባርከን እነርሱም እንዲባረኩ። ለኢየሱስ ተከታይ ይህ ወደ ውስጥ መተንፈስና ወደ ውጭ መተንፈስ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህ ሕይወታችን ነው።
እራሳችሁን ጠይቁ
- የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማትና መለየት መማር ለምን አስፈላጊ ነው?
- ጌታን መስማትና ለእርሱ ምላሽ መስጠት በእርግጥ እንደ መተንፈስ ነውን? ለምን ወይስ ለምን አይደለም?
የZúme ስልጠናን ዛሬ ይጀምሩ
ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ መጀመር ይችላሉ—የትም ቢሆኑ በራስዎ ፍጥነት ይሂዱ።
በነጻ ይመዝገቡ