S.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
የኢየሱስ ተከታይ እንደመሆናችሁ መጠን፣ መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ማንበብ ይገባችኋል። ጥሩ መመሪያ በሳምንት ቢያንስ 25-30 ምዕራፎችን ማንበብ ነው። በየቀኑ የS.O.A.P.S. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ቅርጽ በመጠቀም ማስታወሻ መያዝ፣ የበለጠ እንድትረዱ፣ እንድትታዘዙ እና እንድታካፍሉ ይረዳችኋል። S.O.A.P.S. የሚወክለው፦
- Scripture : ዛሬ በተለይ ትርጉም ያላቸውን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቅሶች ጻፉ።
- Observation : በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እነዚያን ጥቅሶች ወይም ዋና ነጥቦች በራሳችሁ ቃላት እንደገና ጻፉ።
- Application : እነዚህን ትእዛዛት በራሳችሁ ሕይወት መታዘዝ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ።
- Prayer : የተማራችሁትን እና እንዴት ለመታዘዝ እንዳሰባችሁ ለእግዚአብሔር የምትናገሩትን ጸሎት ጻፉ።
- Sharing : የተማራችሁትን ወይም በተግባር የምትኖሩትን ለማን እንድታካፍሉ እግዚአብሔርን ጠይቁ።
ይህ ማንኛውም የኢየሱስ ተከታይ ሊጠቀምበት የሚችለውን ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ ለመማርና ለማስታወስ ቀላል መንገድ ነው።
S.O.A.P.S. በተግባር እንዴት እንደሚሰራ ይህ ምሳሌ ነው፦
S – “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ አይደለምና መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለም፥” ይላል እግዚአብሔር። “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ ከፍ ያለ ነው፥ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ የከፍ ያለ ነው።” ኢሳይያስ 55፥8-9
O – እኔ ሰው እንደመሆኔ፣ በማውቀውና ማድረግ በምችለው ነገር ውስን ነኝ። እግዚአብሔር ግን በምንም መንገድ አይገደብም። ሁሉንም ያያል ያውቃልም። ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል።
A – እግዚአብሔር ሁሉን ስለሚያውቅና መንገዱም ከሁሉ ስለሚበልጥ፣ በራሴ መንገድ ከመተማመን ይልቅ እርሱን ብከተል በሕይወቴ እጅግ የተሻለ ውጤት አገኛለሁ።
P – ጌታ ሆይ፣ አንተን የሚያስደስትና ሌሎችንም የሚረዳ መልካም ሕይወት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አላውቅም። የራሴ መንገድ ወደ ስህተት ይመራኛል። የራሴ ሐሳብም ወደ ጉዳት ይመራል። ከዚህ ይልቅ መንገድህንና ሐሳብህን አስተምረኝ። አንተን ስከተል ቅዱስ መንፈስህ ይምራኝ።
S – እነዚህን ጥቅሶችና ይህን ተግባራዊ ትምህርት አስፈላጊ ውሳኔዎችን ለማድረግ አቅጣጫ የሚያስፈልገው እና አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ያለው ጓደኛዬ ስቲቭ ጋር አካፍላለሁ።
እራሳችሁን ጠይቁ
- በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቴ ጊዜ ከእግዚአብሔር የምሰማውን ማካፈል ለእኔ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
- ይህን መሣሪያ አሁን ላካፍላቸው የምችላቸው በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው?
የZúme ስልጠናን ዛሬ ይጀምሩ
ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ መጀመር ይችላሉ—የትም ቢሆኑ በራስዎ ፍጥነት ይሂዱ።
በነጻ ይመዝገቡ