concept

እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል

ይህን ገጽ ያጋሩ

ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደ ተጀመረች አስበው ያውቃሉ? በመጀመሪያ ማንም ሙያተኛ አልነበረም። ተገረማችሁ? ጥሩ ነው፤ እግዚአብሔር ሙያተኞችን የማያስፈልገው ዕቅድ ነበረው። እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል። የመጀመሪያውን የቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ ለመጀመር እንዲሁ አደረገ። ዛሬም እንዲሁ ያደርጋል። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ሌሎችን ስለ ኢየሱስ እንዲነግሯቸው ተራ ሰዎችን ወደ ዓለም ዙሪያ ላከች። ተራ ሰዎችንም በገዢዎች፣ በጄኔራሎች፣ በአለቆችና በነገሥታት ፊት እንዲቆሙ ላከች። ተራ ሰዎችን የታመሙትን እንዲፈውሱ፣ የተራቡትን እንዲመግቡ፣ ሙታንን እንዲያስነሱ፣ እና ሁሉንም የእግዚአብሔር ትእዛዛት ለዓለም ሰዎች ሁሉ እንዲያስተምሩ ላከች። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ዓለምን እንዲለውጡ ተራ ሰዎችን ላከች። እነርሱም አደረጉት።

የእኛ ሕልም ኢየሱስ የተናገረውን ማድረግ ነው -- በዓለም ዙሪያ ያሉ ተራ ሰዎች በእግዚአብሔር መንግሥት ትልቅ ተጽዕኖ ለማምጣት ትንንሽ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ መርዳት! ኢየሱስ ለተከታዮቹ የሰጣቸው የመጨረሻ መመሪያዎች ቀላል ነበሩ። እንዲህ አለ -- ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል። ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝሁአችሁንም ሁሉ እንዲታዘዙ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። የኢየሱስ ትእዛዝ ቀላል ነበር - ደቀ መዛሙርት አድርጉ።

ይህን እንዴት ማድረግ እንዳለብን የሰጠው መመሪያ ቀላል ነበር፦

  • ወደምትሄዱበት ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤
  • በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤
  • ያዘዘውን ሁሉ እንዲታዘዙ በማስተማር ደቀ መዛሙርት አድርጉ።

እንግዲህ ደቀ መዝሙር ለማድረግ ያሉት ደረጃዎች ምንድናቸው?

  • ወደምንሄድበት ሁሉ እና በመንገድ ላይ ሳለን ሁልጊዜ ደቀ መዛሙርት እናደርጋለን።
  • አንድ ሰው ኢየሱስን ለመከተል ሲወስን - መጠመቅ አለበት።
  • እያደጉ ሲሄዱ - እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ እንዴት መታዘዝ እንዳለበት ልናስተምር ይገባል።

ከያዘዘው ነገሮች አንዱ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ስለሆነ፣ ይህ ማለት ኢየሱስን የሚከተል እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር እሱም ደግሞ ደቀ መዛሙርት ማድረግ እንዴት እንደሚችል መማር አለበት ማለት ነው።

እራሳችሁን ጠይቁ

  • ኢየሱስ ሁሉም ተከታዮቹ ለታላቁ ተልዕኮ እንዲታዘዙ ካሰበ፣ ለምንድነው ጥቂቶች ብቻ ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉት?
    • እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል የሚለው ሀሳብ ከተማራችሁት ወይም የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው ብላችሁ ከገመታችሁት የተለየ ነው?

የZúme ስልጠናን ዛሬ ይጀምሩ

ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ መጀመር ይችላሉ—የትም ቢሆኑ በራስዎ ፍጥነት ይሂዱ።

በነጻ ይመዝገቡ