የአራት መስኮች መገልገያ
የአራት መስክ መመርመሪያ ገበታ አሁን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሁኔታና በዙሪያቸው ያለውን የመንግሥቱን እንቅስቃሴ ለማጉላት በአመራር ክፍል ለመጠቀም የሚረዳ ቀላል መሣሪያ ነው። ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሥራው እንዴት እየሄደ እንደሆነ ለመገምገም ከአገልግሎት ርቀው ወደ ጸጥታ ሥፍራዎች ይወስዳቸው ነበር። ይህ ቀላል መሣሪያ እርስዎና አብረውዎ ያሉ ተባባሪ መሪዎች ይህን የኢየሱስን ሥርዓት እንድትከተሉ እና የአደራችሁን ክፍሎች ሁሉ እንድትመለከቱ ለማገዝ ነው። መገልገያውን በአቻ ለአቻ አሰልጣኝነት ውስጥ በመጠቀም እንቅስቃሴዎችን፣ ሰዎችን እና ቡድኖችን በተለያዩ መስኮች በመመደብ ይገምግሙ፣ እርስ በርሳችሁም ወደ ተግባር የሚወስዱ ነጥቦችንና ቀጣይ እርምጃዎችን ለማውጣት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ጠይቁ።
የአራት መስኮች መገልገያ ምሳሌ
ባዶ መስክ
የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፦ መንግሥቱን ለማስፋፋት ወዴት ወይም ከማን ጋር [what people groups] እቅድ አላችሁ?
የመዝራት መስክ
የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፦ የመንግሥቱን የምስራች ወዴት ወይም ከማን ጋር እያካፈላችሁ ነው? ይህን እንዴት እያደረጋችሁት ነው?
የማደግ መስክ
የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፦ ሰዎችን እንዴት እያስታጠቃችሁና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው በግልም ሆነ በተፈጥሯዊ አውታረ ግንኙነቶቻቸው ውስጥ እያሳደጋችሁ ነው?
የመከር መስክ
የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፦ አዲስ መንፈሳዊ ቤተሰቦች [simple churches] እንዴት እየተመሰረቱ ነው?
የማባዛት መስክ
የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፦ ታማኝ ሰዎችን ከማን ጋር፣ እንዴት እና መቼ እየመረጣችሁ ነው እናስ የምታስታጥቋቸው እና ለመብዛት ሃላፊነት እንዲኖራቸው የምታደርጉት እንዴት ነው?
እራሳችሁን ጠይቁ
- እነዚህን ጥያቄዎች አብራችሁ ተገናኝታችሁ መገምገም የምትችሉት ተመሳሳይ ጉጉት ያለው ማን አላችሁ?
የZúme ስልጠናን ዛሬ ይጀምሩ
ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ መጀመር ይችላሉ—የትም ቢሆኑ በራስዎ ፍጥነት ይሂዱ።
በነጻ ይመዝገቡ