የደቀ መዝሙር እና የቤተክርስቲያን ቀለል ያለ ፍቺ
በክርስቶስ ውስጥ ማን መሆን እንዳለብን እና በክርስቶስ ውስጥ ከሌሎች ጋር እንዴት ግንኙነት ሊኖረን እንደሚገባ ለማወቅ፣ "ደቀ መዝሙር" እና "ቤተ ክርስቲያን" የሚሉትን ቃላት በቀላል መንገድ መግለጽ አስፈላጊ ነው።
ደቀ መዝሙር ማለት ምንድን ነው?
ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል ትርጉሙ ተከታይ ማለት ነው። ደቀ መዝሙር የእግዚአብሔር ተከታይ ነው። ኢየሱስም፣ "ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል" አለ። ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ኢየሱስ ንጉሣችን ነው። እኛም የእርሱ ዜጎች፣ ለፈቃዱ የምንገዛ ነን። ፍላጎቱ፣ ዓላማዎቹ፣ አሳቦቹ፣ ቅድሚያዎቹ እና እሴቶቹ ከሁሉ የላቁና የተሻሉ ናቸው። ቃሉም ሕግ ነው። የመንግሥቱ ሕግ ምንድን ነው? ኢየሱስ ለዜጎቹ ምን እንዲያደርጉ ይናገራል? ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን የተሰጡት የእግዚአብሔር ትእዛዛት፣ ማለትም ሕጉና ነቢያት ሁሉ፣ በእነዚህ ሁለት ነገሮች ሊጠቃለሉ እንደሚችሉ አስተማረ፤ እግዚአብሔርን ውደድ እና ሰዎችን ውደድ። ኢየሱስ እንዲሁም ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ እና ያዘዘውን ሁሉ እንዲታዘዙ እንድናስተምራቸው አዘዘን። ደቀ መዛሙርት ማድረግ ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ ማስተማርን ስለሚያካትት፣ ሐዲስ ኪዳን በዚህ አንድ ነገር ሊጠቃለል ይችላል፤ ደቀ መዛሙርት አድርጉ። ስለዚህ ደቀ መዝሙር እግዚአብሔርን የሚወድ፣ ሰዎችን የሚወድ እና ደቀ መዛሙርት የሚያደርግ የኢየሱስ ተከታይ ነው።
ቤተ ክርስቲያን ማለት ምንድን ነው?
ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሕንፃ - የምትሄዱበት ቦታ - አድርጋችሁ ማሰብ ለምዳችሁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚናገረው እንደ መሰብሰብያ - የምትካሉበት ሕዝብ - ነው። "ቤተ ክርስቲያን" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሦስት የተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላል፦
- ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን -- ከዚህ በፊት የነበሩ፣ አሁን ያሉ እና ወደፊት የሚኖሩ ሁሉም የኢየሱስ ተከታዮች
- የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያን -- በአንድ የተወሰነ አካባቢ ውስጥ ወይም በዙሪያው የሚኖሩ እና ኢየሱስን የሚከተሉ ሁሉም ሰዎች
- በቤት የሚሰበሰብ ቤተ ክርስቲያን -- ኢየሱስን የሚከተሉ እና ከእነርሱ አንዱ ወይም ከዚያ በላይ በሚኖሩበት ስፍራ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሁሉ
ቀላል አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላቸውና ንጉሣቸው ኢየሱስ የሆነ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ሌሎችን የሚወዱ እና ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ናቸው። እነዚህ ቀላል አብያተ ክርስቲያናት አንድ ላይ ተገናኝተው ከዚህ የበለጠ ትልቅ ነገር ለማድረግ ሲሠሩ፣ የከተማ ወይም የክልል ቤተ ክርስቲያን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በክልሎች ውስጥ ተሳስረው በታሪክ ሁሉ የተዘረጉ የሁሉም ቀላል አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ነው።
እራሳችሁን ጠይቁ
- ስለ ቤተ ክርስቲያን ስታስቡ፣ ወደ አእምሮአችሁ የሚመጣው ምንድን ነው?
- በቪዲዮው ውስጥ 'ቀላል ቤተክርስቲያን' ተብሎ ከተገለጸው ጋር ያ ምስል ምን ልዩነት አለው?
- የትኛው ለመባዛት ይበልጥ ቀላል ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን?
የZúme ስልጠናን ዛሬ ይጀምሩ
ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ መጀመር ይችላሉ—የትም ቢሆኑ በራስዎ ፍጥነት ይሂዱ።
በነጻ ይመዝገቡ